Thursday, January 19, 2017

ያልታደሰው የገዥው ቡድን አስተሳሰብ!!! (ሰማያዊ ፓርቲ)


   

ያልታደሰው የገዥው ቡድን አስተሳሰብ!!! (ሰማያዊ ፓርቲ)
ትናንትጥር 09 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 10፡55 ሰዓት ከ”ኢህአዲግ” ፅ/ቤት ለሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ተደውሎ “ኢህአዴግ ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ሊያካሂደው ባቀደው የውይይት መድረክ ላይ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው የሚሳተፉ ሁለት ተወካዮች ፓርቲው እንዲያሳውቃቸው” በጠየቁት መሰረት አቶ ስለሺፈይሳና አቶ ይድነቃቸው አዲስ ፓርቲውን ወክለው እንዲሳተፉ ስማቸው በተሳታፊዎች ዝርዝርእንዲመዘገብ አደረጉ፡፡ ኢህአዲግ ውይይቶችን ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ እንጂ ችግሮችን ለመፍታት እንደማያካሂደቸው የታወቀ ቢሆንም በቦታው ተገኝቶ የተባለውን ሰምቶ ኢህአዲግ እንደሚያወራው “በጥልቅ” ታድሷል ወይስ አዚያው ነው የሚለውን ለማወቅ በስብሰባው የቀረቡ ሃሳቦች መመዘኛ ስለሚሆኑ በስብሰባው መገኘቱ ጠቃሚ ነገር ነው በሚል በስብሰባው ለመገኘት ተወስኖ ነበር፡፡

ስብሰባው በዛሬው ዕለት ጥር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተካሄደ ሲሆን በውይይቱ ከኢህአዲግ ተወካዮችም ሆነ ኢህአዴግ ቀለብ እየሰፈረላቸው በተቃዋሚ ፓርቲ ስም ከተቀመጡ “ፓርቲዎች” የተነሱት ሃሳቦች የሚያስገርሙ ነበሩ፡፡ በገዥው ቡድን የተበላሸ የፖለቲካ አስተሳሰብ ምክንያት በተፈጠረ ችግር በሐገራችን ብዙመከራ፣ እስር፣ ድብደባ፣ የንብረት ውድመትና ሞት ተከስቶ እያለና “በአስቸኳይጊዜአዋጅ” ሥም የዜጎች ሰብአዊናዲሞክራሲያዊ መብቶች መጨፍለቁ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለዜጎች ከሰማይ እንደወረደላቸው መና ለማሳየት ፕሮፓጋንዳ ሲነፋበት ሲሰማ በአግራሞት ያስደምማል፡፡
በስብሰባዉ የተገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች ኢህአዴግ ባለፉት 26 ዓመታት ሲያራምደው በቆየው የአስመሳይ ፖለቲካ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ እያወሳሰባቸው እንደሄደና ውይይትም ይደረግ ከተባላ ድምፃቸው እንዲሰማ የሚፈልጉ ሁሉ እንዲሳተፉ ተደርጎ ችግሮችን የሚፈታበት ውይይት እንዲደረግ ከመጠየቃቸውም ባሻገር ኢህአዲግ ስብሰባውን ሊያካሂድ ከፈለገው መንፈስ በተለየና ግልፅነት በተሞላበት መንገድ እንዲካሄድ አሳስበዋል፡፡


ይህ ዓይነቱ ጠንካራና ለሕዝብ ወገንተኝነት ያለው ሐሳብ በእውነት እንዲንሸራሸር የማይፈልገው ኢህአዲግ ውይይቱ ለሻይ እረፍት ከተበተነ በኋላ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮች በስብሰባው እንዲቀጥሉ አልፈልገም፡፡ ሥብሰባውን ይመሩ ከነበሩት የኢህአዲግ ተወካዮች አንዱ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከሻይ እረፍት ተመልሰው የስብሰባ ቦታቸውን ይዘው የነበሩ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮችን በመጥራት በስብሰባው እንዳይቀጥሉ ነግረዋቸዋል፡፡ ተወካዮችም በነገሩ ግራ ተጋብተው ምክንያቱን እንዲያስረዷቸው አጥብቀው በመጠየቃቸው “ፓርቲውን በህግ የምንወክል ሌሎች ሰዎች አኛ ነን” እያሉን ስለሆነ “ህጋዊ አመራር ነን” የሚሉትን ለመተካት እንዳሰቡ አስረዱአቸው፡፡ ፓርቲውን በህጋዊ እንወክላለን የሚሉ ግለሰቦች አካሂደነዋል የሚሉትን የጠቅላላ ጉባኤ ሪፖርት ለምርጫ ቦርድ አቅርበው በቦርዱም ገና እየታዬ መሆኑና ምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሳይሰጥ እንዴት ሌሎችን ህጋዊነት ትቀበላላችሁ? የሰማያዊ ፓርቲ ሕጋዊ ተወካዊ ኢንጅነር ይልቃል የሚመራው መሆኑን አውቃችሁ በትናንትናው እለት ጥሪ አድርጋችሁልን ከተገኘን በኋላ እንዲህ ዓይነት ሃሳብ ይዛችሁ መምጣታችሁ በስብሰባው ያቀረብነውን ሃሳብ ከመጥላት ውጭና ለእናንተ የሚመቸችሁን ቡድን እውቅና እየሰጣችሁ ለመሄድ ከምታደርጉት አካሄድ ውጭ ተቀባይት የለውም በማለት ጠንካራ ሃሳብ በማቅረባቸው ውጥረት ውስጥ የገቡት አቶ ሺፈራው ሽጉጤ “የምርጫ ቦርድ ፀሐፊ አቶ ነጋ ዱፊሳ “ቦርዱ ውሳኔ አስተላልፎ ሕጋዊ አመራሮች ሌሎች ናቸው” ብሎኛል የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡
በስብሰባው የተገኙት የሰማያዊ ፓርቲ ተወካዮችም የሚያምኑበትን ሃሳብ አስቀድመው ከማስተላለፋቸውም በላይ ከዚህ ቀጥሎ በሚካሄደው የስብሰባ መዝጊያ ውይይት ላይ መሳተፍ አለመሳተፍ የሚጨምረው ነገር ስለሌለና የተባለውም የምርጫ ቦርድ ውሳኔ በእውነት ተላልፏል ወይስ እኛን ከስብሰባ ለማስወጣት የተቀነባበረ የሐሰት መረጃ ነው የሚለውን ማጣራቱ ይሻላል በማለት ስብሰባውን ለቀው ወጥተዋል፡፡


ይህ አሳፋሪ ድርጊት አንድ ነገር አሳይቶን አልፏል፡፡ ኢህአዴግ አሁንም ጠንካራ ሃሳብ የሚየቀርቡ ወገኖችን እንደማይፈልግና ለሱ አገዛዝ ይመቹኛል ያላቸውን ፓርቲ አፍራሾች ወደራሱ በማስጠጋት ለፖለቲካ ፍጆታው እንደሚጠቀምባቸው የኢህአዲግን ያልተቀየረ አቋም አረጋግጦልናል፡፡

No comments:

Post a Comment