Wednesday, January 18, 2017

ጎንደር ውጥረት ውስጥ ናት።



ጎንደር ውጥረት ውስጥ ናት።ወያኔ በሰሜን ኢትዮጵያ ለመስፋፋት ያለመው እቅድ መክሽፍ ከጀመረ ጀምሮ በጎንደር ክፍለሃገር ነዋሪዎች ላይ ከንፈሩን በመንከሱ ስልጣን ከተቆጣጠረበት ጊዜ ጀምሮ በተለያየ መልኩ ሲፈጽም የነበረው የዘር ማጽዳት ወንጀል በኣማራ ክልል በተለይ በጎንደርና ጎጃም የተነሳውን ሕዝባዊ እምቢተኝነት ተከትሎ በከፍተኛ ደረጃ በኣዲስ መልክ የዘር ማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም ሽርጉድ በማልት ላይ ይገኛል። በክልሉ የተነሳው ሕዝባዊ ተቃውሞ በኮማንድ ፖስት ታጅቦ የተፈጸመው መንግስታዊ ሽብር ግድያና ኣፈና እስር ኣልበቃኝም ያለው ወያኔ በጎንደር የሚደረገውን ጥምቀት በዓል ኣከባበር ላይ በደብረዘይት የእሬቻ በዓል የፈጸመውን ጭፍጨፋ ሊደግም ኣሰፍስፎ ይገኛል።
ዛሬ ጎንደር የነበራት ድባብ ረጭና ጭር ያለ መሆኑን በአካባቢው ያሉ ወጣቶች ገልጠውልኛል በተመሳሳይ የህዝቡንም አንድነት ሲነግሩኝ በደስታ ነው ይሄ በእንዲህ እንዳለ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት ተከባና መናሀሪያ ሆና መዋሎንም አልሸሸጉኝም ይሄ በእንዲህ እንዳለ በዛሬው ቀን በከተማዋ ላይ ገዱ አንዳርጋቸውና በረከት ስሞኦን የተባሉ የስርአቱ ሎሌዋች መግባታቸውንና በግዳጅ ከበርሃ የቀረውን ገበሬ ባልተመረቀ አዳራሽ ሰብስበው ሻይ ሲግቱት ውለው ያ ፍሬ ተመልሰው መሄዳቸውም አልተደበቀም በተረፈ ግን ለዚህ ጥምቀት በአል አስመልክቶ ወጣቱን ለመጨረስ ጎንደር ላይ በሁሉም ህንፃዋች ላይ አልሞ ተኮሽ መመደቡና ይሄ ስርአት ወጣት ከመጨረስ ወደ ሆላ እንደማይል በመገንዘብ ምዕመኑ ራሱን ይጠብቅ ሲሉ መልክታቸውን አስተላልፈዋል ባለው መረጃ መሰረት ጎንገር ላይ የጎንደር ህዝብ የወንድሞቻችን ደም ሳይደርቅ በወንድሞቻችን ደም ላይ ታቦተ ህጉን ይዘው እንደማይወጡ እና ወጣቱም በዚህ በአል ተሳታፊ አለመሆኑን በአንድ ድምፅ ለቃሉ ታማኝ የሆነው ጎንደሬ ለማሳየት ዝግጅቱን ጨርሶል

No comments:

Post a Comment