Monday, January 23, 2017

ከድርድር እና ከውይይት በፊት ሰማያዊ ፓርቲ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አሳሳቢ ጉዳዮች እንዳሉት ገለጸ ። (ይድነቃቸው ከበደ)

   


ከድርድር እና ከውይይት በፊት ሰማያዊ ፓርቲ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አሳሳቢ ጉዳዮች እንዳሉት ገለጸ ።
—- በአገራችን ለወራት የቀጠለው ህዝባዊ ተቃውሞ እና እሱን ተከትሎ በተፈጠረው አለመረጋጋት ፤ ገዢው ምንግስት በደረሰበት ውስጣዊና ውጫዊ ተጽእኖ እንዲሁም ግፊት ምክንያት ለድርድር እና ለውይይት ዝግጁ ነኝ ማለቱ የሚታወቅ ነው። – በዚህም መሰረት በስልጣን ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ/ ሕውሓት ገዢው መንግስት ፤ በአገር ውስጥ ከሚገኙ አገር አቀፍ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ፣በአዲስ አበባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የመንግስት ተጠሪ የመሰብሰቢይ አዳራሽ ውስጥ የመጀመሪያ የመክፈቻ በስብሰባ ማካሄዳቸው ለማወቅ ትችሏል። – ይሁን እንጂ በባለፈው ሳምንት የሰማያዊ ፓርቲ የውጪ ጉዳይ ኃላፊ መምህር አበበ አካሉ ፣ለአዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደገለጹት ከሆነ፤ በአውሮፓ ህብረት የህበረቱ የፓለቲካ የፕሬስና የኤንፎርሚሽን ኃላፊ ከሆኑት ሚስተር ሳንድ ዌድ እና ከባልደረቦቻቸው ጋር ባደረጉት ንግግር ፤ “መንግስት ከተቃዊሞች ጋር እወያያለው ቢልም ለመወያየት የተመረጡ ሽማግሌዎች ገፍቶ ድርድሩ ማቆሙን “የገለጹ ሲሆን ፤ በዛሬው እለት አቶ የሺዋስ አሰፋ በሦስተኛ ወገን ይደረግ የነበረው ጥረት ለምን እንደተቋረጠ ጥያቄ በመጠየቅ ፤ ወደፊትም የሦስተኛ አካልት በዚህ ውይይቱና ድርድር ሊኖራቸው የሚችል አሰተዋአዖኦ በተመለከተ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል ። – በተካሄደው የውይይትና የድርድር የመክፈቻ ስነ-ስርዓት፣ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ የሺዋስ አሰፋ የፓርቲያቸውን አቋም አስመልክቶ እንደገለጹት ከሆነ፣ ድርድር እና ውይይት አስፈላጊ መሆኑን በማመላከት ፤ ድርድሩ እና ውይይት ከመካሄዱ በፊት ፓርቲያቸውን የሚያሳስበው ጉዳይ እንዳለ የገለጹ ሲሆን፣ – አቶ የሺዋስ አሰፋ ” በፓርቲያችን በኩል ለመወያየትና ለመደራደር ዝግጁ ነን። የመወያያ እና የመደራደሪያ ሃሳቦቻችንን አዘጋጅተናል ። ነገር ግን ወደ ድርድር እና ውይይት ከመግባታችን በፊት ሰማያዊ ፓርቲ ቅድሚያ የሚሰጣቸው አሳሳቢ ጉዳዮች አሉን ” በማለት በስብሰባው ላይ መግለፃቸውን ለማወቅ ተችሏል ። – ሰማያዊ ፓርቲ ቅድሚ የሚሰጣቸው ጉዳዮችን በተመለከተ ፦ – 1ኛ. ገዥው ፓርቲ የእውነት ተወያይቶና ድርድር አድርጎ በአገራችን የተረጋጋ የፓለቲካ ስርዓት እንዲኖር የሚፈልግ ከሆነ፣ በዚህ ድርድር እና ውይይት ላይ ገደብ ሳይበጅለት የሚመለከታቸው ሁሉ መሳተፍ እንዳለባቸው ። – 2ኛ. የዜጎች መሠረታዊ የነፃነት መብት የሚገድበው የአስቸኳይ አዋጅ ተደንግጎ እያለ ውይይትና ድርድር ማካሄድ የማይቻል መሆኑ፣ – 3ኛ. ከአስቸኳይ አዋጁ ጋር በተያያዘ ታፍሰው በተለያየ እስር ቤት ውስጥ የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ እስረኞች እንዲፈቱ። – 4ኛ.የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋች እንዲሁም ጋዜጠኞች ፤በሙያቸው እና በአመለካከታቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ ዜጎች መፈታት እንዳለባቸው ፣ ሰማያዊ ፓርቲ ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን ገልጸዋል ። – ይሁን እንጂ ፓርቲው ቅድሚያ ስጥቶ ያስቀመጠው ሃሳብ አስመልክቶ ፤ የእለቱ የመደርክ መሪ የነበሩት አቶ ሽፍራው ሽጉጤ ” ወደ ነጥቦቹ ሳንገባ በስብሰባው ስነ-ስርዓት ላይ ብቻ ሃሳብ ስጡ ፣ፓርቲው አለኝ የሚላቸው ሃሳቦች በቀጣይ በጽሑፍ ማቅረብ ይችላል”የሚል ምላሽ ሰጥተዋል ። ሆኖም ግን በጽሑፍ አዘጋጅተናል አሁኑኑ ማቅረብ እንቻላለን በማለት አቶ የሺዋስ መልስ የሰጡ ሲሆን። የመድረኩ መሪ የሰጡት ምላሽ፣ በቀጣይ 15 ቀናት ውስጥ ሁሉም ፓርቲ አለኝ የሚለውን ሃሳብ በጽሑፍ ማቅረብ ይችላል የሚል መልስ መስጠታቸው ለማወቅ ተችሏል ። – ከዚህ ጋር በተያያዘ ሰማያዊ ፓርቲ ፣ ከመኢአድ እና ከመድረክ ፓርቲዎች ጋር፤ በገዢው መንግስት አማካኝነት የተጠርውን ውይይትና ድርድርን አስመልክቶ ፤ቀጣይ ምን መሆን እንዳለበት የጋራ ምክክር ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል ። —— (ይድነቃቸው ከበደ)

No comments:

Post a Comment