Tuesday, January 24, 2017

“ድሃ ተበደለ፤ ፍርድ ተጓደለ” ኢህአዴግ የማይቀርፈው ሙስና — አክሎግ ቢራራ (ዶር)


አክሎግ ቢራራ (ዶር)
“ድርጅታዊ ምዝበራ” ብየ የሰየምኩትን መጽሃፍ ስጽፍ ከሁሉም በላይ ያሳሰቡኝና ያስጨነቁኝ አስኳል ጉዳዮች ሶስት ናቸው፤
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
ዶ/ር አክሎግ ቢራራ
አንድ፤ አብዛኛው በድህነት፤ በረሃብ፤ በበሽታ፤ በሰብአዊ መብቶት ረገጣ፤ በአስተዳደር ብልሽት የሚሰቃየው ከ90 በመቶ በላይ የሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ አሰቃቂ ደረጃ ላይ መድረሱ ነው።
አክሎግ ቢራራ (ዶር)
ሁለት፤ አስደናቂ እድገት ታሳያለች በምትባለው የምግ ጥገኛዋ ኢትዮጵያ፤ መብቱ ተገፎ፤ የስራ እድል አጥቶ፤ በአገሩ በኢትዮጵያ እየኖረ ፈጥሮና ስርቶ ራሱን የማሻሻል እድሉ ዝግ የሆነበት ከ70 በመቶ በላይ የሚገመተው የደርግና “የኢህአዴግ አዲስ ትውልድ” በገዢው ፓርቲ መገለልና መብቶቹ ሁሉ መታፈን ነው። የዚህ ተተኪ ትውልድ እጣው ለመብቱ ሲከራከር ግድያ፤ አፈናና እንዲሰወር መደረግ ነው። ባለፈው ዓመት ስንት ወጣት እንደሞተ ባይታወቅም ከሁለት ሽህ በላይ እንደሚገመት የውስጥ ተመልካቾች ይናገራሉ። ከ110,000  ያላነሰ ኦሮሞና አማራ ወጣት እንደታሰረ ይገመታል። ገዢው ፓርቲ መሰረታዊ ችግሮችን ለመፍታት ፈቃደኛ ስላልሆነና ብቃትም ስለሌለው መፍትሄው ማፈን፤ ማሰር፤ መግደል፤ እንዲሰወርና እንዲሰደድ ማስገደድ ሆኗል። በዚህ አይነት ሂደት እስር ቤቶችን ካላስፋፋ በስተቀር ያሉት እስር ቤቶች አይበቁም።
ሶስት፤ አንድ ስርዓት በሙስና የተበከለ ከሆነ ሰላምና እርጋታ አይኖርም። በዜጎች መካከል ያለው የገቢና የኑሮ ልዩነት እየተባባሰ ይሄዳል። ይህ አሰቃቂ ሁኔታ ቀስ በቀስ ለአገር መፈራረስ ዋና መንስኤ ይሆናል። ኪራይ ሰብሳቢነትና ሙስና መዋቅራዊ ሲሆን የሚያስከትለውን አደጋ በመረጃ ተደግፋ ያቀረበችው ደራሲ ሳራህ ቸየዝ “Thieves of State: why corruption threatens global security,” በሚለው መጽሃፏ አፍጋኒስታን፤ ግብጽ፤ ሶሪያ፤ ኢራቅ፤ ናይጀሪያና ሌሎች ተመሳሳይ አገሮች እንዴት በመፈራረስ ላይ እንዳሉ ታሳያለች። ዋናው ነጥቧ የፓርቲና የመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለሕዝብ ያለባቸውን አደራና ሃላፊነት ትተውና ረስተው፤ ራሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ስላከበሩ አገሮቻቸው የጦርነት አውድማ ሆነዋል የሚል ነው። የሞባረክ መንግሥት የወደቀበት ዋና ምክንያት ሕዝቡን አፍኖ፤ ስልጣኑን ተጠቅሞ፤ ራሱን፤ ቤተሰቦቹን፤ ወዳጆቹንና ደጋፊዎቹን፤ ጀኔራሎቹን ጨምሮ ስላከበረ ነው የሚል ድምዳሜ አቅርባለች። በሙስና የተበከለ አምባገነን መንግሥት የመሳሪያ የበላይነትም ቢኖረው በሕዝብ አመጽ እንደሚወድቅ አሳይታለች። የሙስና አደጋው ለአገር መፈራረስ ግብአት እንደሚሆን መረጃዎችን አቅርባለች።

No comments:

Post a Comment