ለወትሮው ከገዢው ፓርቲ አካባቢ የተለመደው የተሃድሶ ትርጉም ለየት ያለ ነበር። “ኢህአዴግ” ስብሰባዎችን ያደርግና ሲጨርስ “የተሃድሶ ሰኣት!” ይባልና በዚያን ጊዜ የማእድ አገልግሎትና የተለያዩ መጠጦች የኪነት ትርኢት የሚቀርብበት ሰኣት ተሃድሶ ይባላል። ለአንድ የገዠው ፓርቲ አባል ተሃድሶ ሲባል ቶሎ ወደ ህሊናው የሚመጣው ነገር ድግስ ይመስላል። ከስብሰባ በኋላ ዘና ማለት። ይሁን እንጂ በቅርቡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጥልቀት በመታደስ ላይ ነን ሲሉ የገለፁ ሲሆን ይህ ተሃድሶ በአእምሮ መታደስን-መለወጥን የሚያሳይ እንደሆነ ተገልፃልናል። ይሁን ይሏል። መቼስ የተሃድሶ ትርጉም ከድግስ አልፎ እውነተኛ ትርጉሙን ከያዘና በአእምሮ መታደስን ከጨመረ አንዳንድ ለውጥ የናፈቀው ቢጓጓ አይፈረድም ይሆናል። በመሆኑም ተሃድሶ ከተለመደው ትርጉም አልፎ በአእምሮ መለወጥን መታደስን ሪፎርሜሽንን ካመጣ ግሩም ነበር። እንግዲህ ጠቅላይ ሚንስትሩ በጥልቅ ተሃድሶ ላይ ሰነበትን ካሉ ለውጥ ያለ ልክ የናፈቀው ሰው በጥልቀት በመታደስ ላይ ከከረመ ፓርቲ የሚጠብቀው ጥልቀት ያለው ጉዳይ አለ። አንድ ድርጅት በጥልቀት ልታደስ ካለ ጥልቅ ችግሮች ገጥመውታል ማለት ነው። የችግሩን ጥልቀት ተገንዝቧል ማለት ነው። ይህ ፓርቲ የገጠመውን ጥልቅ ችግር ተረድቶ ለመውጣት ቆርጧል ማለት ነው። እናም ለውጥ ናፋቂው ህዝብ የሚጠብቀው ጉዳይ መውጣት (exodus) ነው። ገዢው ፓርቲ እንደ ፓርቲም እንደ ግለሰብም በምን በምን ጉዳዮች ላይ መውጣት exodus ሊያውጅ ይገባል? በሚለው ላይ ትንሽ እንወያይ።
ከብዙ ዓመታት በፊት አንድ ጲላጦስ የሚባል ዳኛ ነበር። ይህ ዳኛ ተሰሚነት የነበረው አንቱ የተባለ ዳኛ ነበር። ታዲያ አንድ ቀን አንድ ለሙያው ያለውን አርበኝነት የሚፈትን ሰዓት መጣበት። አንድ ንፁህ ሰው በሃሰት ተከሶ ወደዚህ ዳኛ መጣ። በዚህ ንፁህ ሰው ላይ ህዝብን የሚያወናብድ ስራ ተሰርቶ አገር ተሸብሯል። ጲላጦስ ግን ሁሉን ያውቅ ነበርና በዚህ ሰው ላይ ለመፍረድ አንጀቱ አልቻለም። ይሁን እንጂ የቆረጠና የወጣ ዳኛ አልነበረም። ከዚያም ከዚህም ሳይጠየቅ ይህን ፈተና ለመወጣት የጣረ ብልጣብልጥ ዳኛ ነበር። እናም ለካህናቱና ለተከታዮቻቸው እኔ ከዚህ ሰው ምንም ጥፋት አላየሁም ነገር ግን እናንተ ካላችሁ የፈለጋችሁትን አድርጉ አላቸው። ይህ ብቻ ሳይሆን ለበኣል አንድ ወንጀለኛ ይለቀቅ ዘንድ አሳብ አቀረበና በርባን የተባለውን ወንበዴ ለቀቀ። በርግጥ ኢየሱስን የሰቀለው የእስራኤል ህዝብ ወይም አይሁዳውያን ሁሉ አይደሉም። የተወሰኑ ካህናት ያወናበዷቸው ሰዎች ነበሩ። ጲላጦስ ይህን ያውቃል። ነገር ግን ሙያውን ህሊናውን ሰብሮ ከስራው መቆየትን መረጠ። ነገር ግን ከዚያ ሰው እዳ ነፃ ነኝ ብሎ እጁን መታጠቡ ከተጠያቂነት ነፃ አያወጣውም። ይህ ዳኛ አልወጣም። እጁን ታጠበ እንጂ ከህሊና ክስ ነፃ አይሆንም። ህሊናው አይታጠብለትም። እጁን ቢታጠብም ከፍርሃት የተነሳ ወንጀለኛ ለቆ ንፁህን ሰው አሳልፎ ሰጥቷልና በአእምሮ አይታደስም። ይህ ዳኛ መውጣት ነበረበት። መውጣት እንደ ብርቱካን ሚዴቅሳ ነው። መውጣት ደረጃው ከፍ ያለ ነው። በጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ ከገቡ ካድሬዎች መሃል ድርጅቱ ከህዝብ ጋር መራመድ ያልቻለ መሆኑን የተረዱ ነገር ግን በፍርሃት ውስጥ ሆነው ያሉ አባላት ሁሉ ምን አልባት በዚህ ጥልቅ ተሃድሶ ውስጥ እጃቸውን መታጠብ አይበቃም። እምቢኝ ያሉ የወጡ ካድሬዎች ሲኖሩ ነው ለውጥ የሚመጣው። እነ ዶክተር መረራን፣ እነ እስክንድርን የመሳሰሉ ንፁህ ሰዎች ጉዳይ በጥልቀት ለመታደስ ለወሰነ ፓርቲ በርግጥ ለመታደስ ከልብ ፈቃደኛ ይሁን አይሁን ማሳያ ነው። ካድሬዎች በነዚህና በሌሎች ንፁሃን እስራት ላይ እጅ ከመታጠብ አልፈው ሊወጡ ይገባል። በመሆኑም ከጥልቅ ተሃድሶ ባሻገር የሚጠበቀው ነገር ከፍ ያለ እርምጃና ውሳኔ ነው። እንደ ጲላጦስ ያሉ ካድሬዎች የራሳቸውን ሥራ ከማቆየት ያለፈ ጥቅም አያመጡም። ህዝብ የሚሻው የፓለቲካ ኮሚትመንት ነው። በመሆኑም ከዚህ ጥልቅ ተሃድሶ ህዝብ የሚጠብቀው እጅ መታጠብን ሳይሆን እንደ ብርቱካን ሚዴቅሳ የውሳኔ ሰው እንድትሆኑ ነው። ያን ጊዜ ነው የጥልቅ ተሃድሶ ትርጉም የሚኖረው። ጲላጦስን አለመሆን ነው። በነገራችን ላይ ዳኛ ጲላጦስ በመጨረሻ ራሱን እንዳጠፋ ተመራማሪዎች ፅፈዋል።
- የፓለቲካ ኮሚትመንት ለማምጣት መውጣት

- ለብሄራዊ መግባባት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት መውጣት
- ይቅርታ ለመጠየቅ መውጣት
- የባህርይ ለውጥ ለማምጣት መውጣት
No comments:
Post a Comment