መንግስት የደሴን ሙስሊሞች ለማሰርና ለማንገላታት በ2005 ሰኔ 27/2005 ሸህ ይማምን ገድሉዋቸው ሲያበቃ መንግስት በቅርቡ በሞት ያጣነው ወንድም ሙባረክ ይመር እና ለሌሎች 13 ሙስሊሞችን በማሰር በማዕከላዊ በከፍተኛ ሁኔታ በቶርቸር በማሰቃየት በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 አንቀጵ 3 እና1 እንዲሁም አንቀጵ 6 እና 7 በመወንጀል በሽብርተኝነት ሃይማኖታዊ መንግስ ለማቁዋቁዋም አሰፀራቹሃ እና መንግስት ራሱ ገድሉዋቸው ሲያበቃ በዚህ መዝገብ የተከሰሱትን 4 ወጣቶች ሙስሊሞችን ሼህ ኑሩ ይማምን ገድላቹሃል፣በደሴ እና በአማራ ክልል ሲካሄዱ በነበሩ የአንድነት እና ሰደቃ መድረኮች ላይ ተሳትፋቹሃል በማለት ነበር የከሰሳቸው።
ከ3አመት በላይ በደሴ ግዝያዊ ማቆያ፣በማዕከላዊ፣በቂሊንጦ በግፍ የታሰሩት እና ከ3 አመት በላይም ያለ ፍትህ ሲንከራተቱ የቆዩት በሳለፍነው በታህሳስ 27 በዋለው ችሎት በአህመድ እንድሪስ መዝገብ የተከሰሱት እና ሼህ ኑር ይማምን ግድያ በቀጠታ ተሳትፋችሃል የተባሉትን ጀግናው ይመር ሞላ እና ሌሎችን 4 ተከሳሾች የካንጋሮ ፍርድ ቤት ከፍተኛ የእስር ቅጣት በሚያስበይነው አንቀጵ 4 ጥፋተኛ እንዳላቸው ሚታወቅ ሲሆን ቀሪዎቹ 9 ንፁሃን ወጣቶች በአንቀጵ 7/1 እና በዝቅተኛ አንቀጵ መፍረዱ ሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በህውሃት ደህንቶች የሚሾፈረው የካንጋሮ ፍርድ ቤት ከደህንነቶች ተፅፎ የሚተላለፍላቸውን ፍርድ በችሎት በመገኘት ያነባሉ ተብሎ ሲጠበቅ የነበረ ሲሆን በደህንነት ሚመራው የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የህክምና ማስረጃ በመከልከሉ እንዲያቀርብ በማዘዝ ችሎቱ ለጥር 18 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቱዋል::
በዚሁ መዝገብ ተከሶ ተከሳሾቹን ሼህ ኑሩ ይማምን ለመግደል የፋይናንስ ድጋፍ አድርገሃል ተብሎ ተከሶ የነበረው እና ልክ የዛሬ አመት በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በተመረዘ መርፌ ህይወቱ ያለፈው ጀግናው ሙባረክ ይመር ልክ በዛሬዋ ዕለት ወደ አኬራ ከሄድ አመት መሙላቱን ታውቁዋል።
በዚህ መዝገብ ተከሶ ተጨማሪ ክስ የቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አቃጥላቹሃል ተብለው ተከሰው የነበሩት ጀግናው ኡመር ሃሰን በጀግንነት ከመቀመጫው በመነሳት ችሎቱን ያነቃነቀ ተቃውሞ ያሰማ ሲሆን የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ከሌሎች ታሳሪ በተለየ መልኩ ጫና በኛ ሙስሊሞች ላይ እያደረገብን ይገኛል እኛ ታስረን እዚ ምንመላለሰው ሰው ገድለን ሳይሆን ህገ መንግስታዊ የሃይማኖት መብታችንን በመጠየቃችን ነው በማረሚያ ቤቱ እየደረሰበት ያለውን በደል እና ቤተሰብ እያገኘ እንዳልሆን በመግለፅ ተቃውሞ ያሰማ ሲሆን ዳኛው ማረሚያ ቤቱ ምላሹን እንዲያቀርብ በማዘዝ ችሎቱን አጠናቀዋል።
በዛሬው ዕለት የኢቢሲ ጋዜጠኞች ፍርድ ቤት ያልተገኙ ሲሆን ይህም የካንጋሮ ፍርድ ቤት ውሳኔውን በዛሬው ዕለት እንደማያስተላልፍ ቀድሞ መረጃው ከደህንነቶች እንደሚደርሰው ማሳያ ነው።
በአህመድ ኢድሪስ የክስ መዝገብ የተከሰሱት ሙስሊሞች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው
1. አህመድ ኢድሪስ ገበየሁ
2. አንዋር ኡመር ሰዒድ
3. ሷሊህ መሀመድ አብዱ
4.ሼህ አደም አራጋው አህመድ
5. አብዱራህማን እሸቱ መሀመድ
6. ኢብራሒም ሙሔ ይማም
7. ዑመር ሁሴን አህመድ(ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን አቃጥለሃል ተብሎ ተጨማሪ ክስ የተመሰረተበት)
8. ይመር ሁሴን ሞላ
9. ሙባረክ ይመር አየለ(በዛሬው ዕለት ጥር 9 ወደ አኬራ ከሄደ አመት የሞላው ጀግና)
10. እስማኤል ሀሰን ይመር
11. ከማል ሁሴን አህመድ
12. አብዱ ሀሰን መሀመድ
13. አህመድ ጀማል ሰይድ
14. ሙሀመድ ዩሱፍ መሀመድ ናቸው።
በዛሬው ዕለት ተወዳጁ ኡስታዝ ባህሩ ኡመር ጨምሮ በመስከረም 1 በምህረት የተፈቱት ኡስታዞች፣በቅርብ የተፈቱት ጀግናው ኤልያስ ከድር እና በሱ መዝገብ ተከሰው የተፈቱት ጀግኖች እንዲሁም እጅግ ከፍተኛ የሆነ ህዝበ ሙስሊም በፍርድ ቤት በመገኘት አጋርነቱን ማሳየቱ ታውቁዋል በሚቀጥለው ሳምንት ጥር 18ም በፍርድ ቤት በመገኘት አጋርነቱን እንዲያሳይ ጥሪ ቀርቡዋል!! BBN

No comments:
Post a Comment