Wednesday, January 4, 2017

ኦህዴድ በዳዴ (OPDO) ዘውዱ ታደሰ


ኦህዴድ በዳዴ (OPDO) ዘውዱ ታደሰ
ኦህዴድ ኢህአዴግ በአቶ መለስ ዜናዊ ተጠፍጥፎ የተሰራ በኦሮሚያ የህውሓት ምስለኔ እንደ ማለት እምደሆነ እሚያውቀው ያውቀዋል ።
እንደዚህም ሆኖ ከዚህ ቀደም በOPDO ውስጥ ጥሩ ጥሩ ስብዕና ያላቸው ለምን ብለው እሚጠይቁ ግራቀኝ ማየት የሚችሉ ሰወች በመካለለኛ አመራር ላይ እንደነበሩ በስራ አጋጣሚ አይቻቸዋለው ።
* ገሚሶቹ በድፍረት በየመድረኩ ላይ የህውሓት ጣልቃ ገብነት ይቁም እስከማለት እርቀት የሄድም እንዳሉ ታዝባለው እንደነዚህ አይነቶቹ መልካም እና ቅን ሰወች ዛሬ በየምክንያቱ ለእስር ተዳርገዋል ገሚሶቹም ሀገር ለቀው ኮብልለዋል ህውሓት ስጋት የሆኑባትን ሰወች እንዴት አድርጋ ከገበያ እንደምታሶጣቸው ታውቃለች ለዚህም አድርባዬችን በስለላ መረባቸው ውስጥ በመክተት አከሌ ይሄን አለ እንትና እኮ አይወዳችሁም እያሉ በየቀኑ ሪፓርት ለህውሓት ቱባ ባለስልጣናት ቀለብ ሰፍሪዎቻቸው የሚያቀብሉ የኦሮሞ ተወላጆች ሚና ቀላል እሚባል አይደለም በዚህም ምክንያት ከምንም ተነስተው ከቀበሌ ስራ አስኪያጅነት ዛሬ የዞን አስተዳዳሪ የሆኑ ምስለኔዎች ታማኞችን ስም መጥቀስ እንችላለን ።
* ኦህዴድ ውስጥ አሁንም ምርጥ አመራሮች ነበሩ በተለይ መካከለኛ አመራሩ አካባቢ ፍፁም ጥላቻን ያነገቡ ህውሓትን እሚጠየፍ ወጣት አመራሮች ከኦሮሞ ፕሮቴስት ጋር በተገናኘ በተለይ #ከቢሾፍቱ_ሆራርሰዲ ጋር በተያያዘ በተነሳው ተቋውሞ ኢህአዴግ ወርዳል በሚል የተሳሳተ ግንዛቤ በመውሰድ የመንግስትን መሳሪያ ለአካባቢው ወጣቶች ከግምጃ ቤት እያወጡ ያስታጠቁ እንዲሁም አብረው እሳት የለኮሱ የመንግስት አመራሮች ወታደራዊ አዛዦች እንደነበሩ ምንም ጥርጥር የለውም ህዝቡም ይሁን አመራሩ እንዳሰበው ሳይሆን ቀረና ህውሓትም እንደ እባብ አፈር ልሳ በመከላከያ ሰራዊታቸው ታግዘው ስልጣናቸውን አስጠብቀው የተነሳውን የህዝብ ማዕበል ጋፕ ማድረግ ችለዋል ። በዚህም ለውጥ ፈላጊው ህብረተሰብ እና እጁ ያለበት አመራር በከፍተኛ ሁኔታ ተደናግጦ ቆይታል ።
~ በዚህም ምክንያት እንታደስ ጥልቅ ተሀድሶ በማለት አመራሩን ለ15 ቀናት በገልማ_አባገዳ በመጥራት እነ አቶ በከር ሻሌ ወይንም (obo ገ/ መድህን) ከህውሓት አለቆቻቸው የተሰጣቸውን መመሪያ ወደ በታች አመራሩ ሲተፍቱ ከርመዋል በዚህም ጥፉተኛ የተባሉ አመራሮች እንዳሉ እና በሁከት ውስጥ እጃቸው እንዳለ የሚጠረጠሩ አመራሮች ስለመኖራቸው አስረግጠው በመናገራቸው ብዙ የድርጅት አመራሮች ወደ ግብፅ ካይሮ ጨርቄን ማቄን ሳይሉ ግምገማው ሳያልቅ ወተዋል ።
~ ይህ ግምገማ ተሀድሶዐችን እታች መውረድ አለበት በማለት እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ አባላትን ወደ ማወያየት ቢሄዱም የህዝቡ ምላሽ አጥጋቢ ሳይሆን ቀርታል በዚህም ግራ የተጋቡት የOPDO አመራሮች ቡወዛ ወደሚሉት ስልት በመምጣት በክልሉ ያለውን አመራር ሙሉ በሙሉ በአዲስ አመራር መቀየርን መፍትሄ ይሆናል ብለው ወስደዋል በዚህም ይህ ነው እማይባል ነባር አመራር በአየር ላይ ተንሳፎ ደሞዝ ብቻ እየወሰደ ነገ ምን እንደሚፈጠር እየቆዘመ በንዴት እና በእልህ ቂም ቃጥሮ እቤቱ ተቀምጣል ።
~አሁን ኦህዴድ ጥርስ የሌለው ውሻ ሆናል ሙሉ በሙሉ በህውሓት ተፅዕኖ ስር ወድቃል የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለህውሓት አለቆቻቸው የመታዘዝነት ስራ እንጂ እሚሰሩት በራሳቸው እሚወስኑት ውሳኔ የለም የከተማ ከንቲቫ እንካን የመሾም ስልጣን እንደሌላቸው ተነግራቸዋል ኦህዴድ እግሩ ተቆርጦ ዳዴ ማለት ጀምራል ቢያንስ እንካን እንደበፊቱ በአንፃራዊ ነፃነት ውስጥ የሚደረግ ውይይት እራሱ የለም ማለት ነው የእነ አቶ ለማ መገርሳም ይሁን የአቶ በከር ሻሌ ስራ ያገሩን በሬ ባገር ሰርዶ እንዲባል እንጂ ምንም በራሳቸው እሚሰሩት ስንዝር ነገር የለም ።
ይህ ጥርነፍ ምን ያህል እርቀት ይወስዳል የሚለውን አብረን እናየዋለን ግን ይህ አሰራር ህዉሓትንም ይሁን መሪ ድርጅቱን ኢህአዴግ ከውስጥ ተቋውሞ እንዲነሳበት ሊያደርግ እንደሚችል ያሰጋል ።

No comments:

Post a Comment