ገዢው ፓርቲ ሕወሃት/ኢሕአዴግ ከተቃዋሚዎች ጋር ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንወያይ በሚል ያቀረበውን ጥሪ ተከትሎ በአገር ዉስጥ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲዎች (ሰማያዊ፣ መድረክ፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ኦራፓ …) ለዉይይት ዝግጁነታቸውን ገልጸው ከሁለት ሳምንታት በፊት ለአንድ ቀን መነጋገራቸው ይታወቃል። በወቅቱ ተቃዋሚዎቹ በዚህ ዉይይትና ድርድር ኢሕአዴግ ስብሰባውን መምራት የለበትም፣ ሌላ ሶስተኛ አካል መኖር አለበት የሚል አቋም በመያዛቸውና ገዢው ፓርቲም ያንን በመቀሉ ፣ ሶስተኛ አካል ማን ይሁን በሚለው ላይ ሁሉም ሐሳቦች ይዘው ከመጡ በኋላ በሌላ ጊዜ ዉይይት እንዲቀጥል ተወስኖ ነበር።
በዚህ መሰረት ቃዋሚ ፓርቲዎች ድርድር የሚካሄድበትን ስነ-ስርዓት አስመልክቶ አማራጭ ሃሳባቸውን በጋራ ተመካክረው በአንድ ደብዳቤ አስገብተዋል ። 7 ገፅ ያለው ደብዳቤ የእጩ አደራዳሪዎች ስም ጥቆማና የአደራዳሪዎችን ሚና ፣ የእጩ ተዛቢዎችን ጥቆማና የታዛቢን ሚና ፣ የስብሰባ ስነ-ስርዓትንና የዲሲፕሊን እርምጃ አወሳሰድ ፣ ከሚዲየ የሚኖርን ግንኙነትና ውጤት እንዴት ለህዝቡ ይገለፅና ልዩ ልዩ ጉዳዮች የሚልን ያካተተ ነው ።
በጋራ ደብዳቤ የጻፉትም በጋራ ተሰባብሰው የመከሩት ድርጅቶች አምስት ሲሆኑ፣ ስድስት አገር አቀፍና በኢትዮጵያ አንድነት የሚያምኑ ፣ ተመሳሳይ ፕሮግራሞች ያሏቸው ድርጅቶች ናቸው። እነርሱም የሰማያዊ ፓርቲ፣ መኢአድ፣ ኢዴፓ፣ ኢራፓ(የኢትዮዮጵያ ራእይ ፓርቲ)፣ መኢዴፓ(መላው ኢትዮጵያ ዴሞክራቲክ ፓርቲ) እና ኢብአፓ(የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) ናቸው።

No comments:
Post a Comment