Monday, February 20, 2017

የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በትግራይ ተወላጆችና በኤርትራውያን ፍጥጫ ውጥረት ውስጥ ሲሆን የ አርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ለግድብ ግንባታ ተወሰዱ። (ቆንጂት ስጦታው)



የሕወሓት የደህንነት ቢሮ በትግራይ ተወላጆችና በኤርትራውያን ፍጥጫ ውጥረት ውስጥ ሲሆን የ አርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ለግድብ ግንባታ ተወሰዱ። (ቆንጂት ስጦታው – መረጃኮም )
ከ አዲስ አበባና አስመራ የተላኩ መረጃዎች በሕወሓት የደህንነት ቢሮ ውስጥ በትግራይ ተወላጆችና በኤርትራውያን መካከል በተነሳው ፍጥጫ የሕወሓት ባለስልጣናት ውጥረት ውስጥ የገቡ ሲሆን የትግራይ ተወላጆችን ኣንስቶ ወደ ክልሎች በተለይ ወደ ትግራይ መድቦ በ አንድ ለመጠርነፍ አና በመሃል ሃገር ያለውን የደህንነትና የስለላ ቡድን በ ኤርትራውያን ለመተካት የተደረገው ሙከራ ከባድ ችግር እንደገጠመው የደህንነት ምንጮች ለመረጃ ዶት ኮም የላኩት መረጃ ይጠቁማል። በኣስመራ በመቀሌና በ አዲስ አበባ በተከታታይ ከ ኤርትራ ለመጡ ሁሉ የኣማርኛና የኦሮሚኛ ቋንቋ ትምህርት ይሰጣል የሚሉት ምንጮች ሕወሓት በትግራይ ተወላጆች ላይ ያለው እምነት እየሟሸሸ ስለሆነ ቁልፍ የደህንነትና የስለላ ስራዎችን በ ኤርትራውያን እየተካ እንደሚገኝ ታውቋል።የኢሳያስ የስጋ ዘመድ የሆነው የማነ ጃማይካ የኣንበሳውን ድርሻ ይዞ ኤርትራውያንን ለደህንነት ቢሮው ይመለምላል ይቀጥራል።
የ አርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች ከግድብ ግንባታ ከ አስመራ ሰማኒያ ኣምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኝ ስፍራ መጓጓዝ መቀጠላቸውን በቦታው የሚገኙ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ከምጽዋ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ሰሜናዊ ቀይ ባህር ግዛት በወያኔ ድጋፍ ለሚገነባው ግድብ በምጽዋ ዶጋሊ ኣሉላ ኣባነጋ ከተወጉበት ኣከባቢ ጊንዳ አቅራቢያ ጋህቴላይ በሚባል የግድብ ግንባታ ስራ ላይ እንደሚገኙ ሲታወቅ በቦታው አይቶ ኢሳያስ ኣፈወርቂ ተገኝተው መጎብኘታቸውን ምንጮቹ ይናገራሉ።
ይህ በወያኔ ርዳታና ድጋፍ በኣርበኞች ግንባር ታጋዮች የጉልበት ሰራተኝነት የሚገነባው ግድብ በከፍተኛ ጥበቃ ስር የሚገኝ ሲሆን ጉዳዩ የማይመለከታቸው ኤርትራውያን በቦታው መግባት ኣይደለም ማለፍ እንደማይችሉ የሻዕቢያ ምንጮቻችን ለእረፍት ከመጡበት አስመራ የላኩት መረጃ ይጠቁማል። ግድቡ ከተጀመረ ሶስት ወር ሆኖታል።የ ኣርበኞች ግንቦት ሰባት ታጋዮች በሙሉ መሳሪያቸውን አስቀምጠው በጉልበት ስራ በሚሳተፉበት በዚሁ የጋህቴላይ ግድብ ስራ ላይ በበላይነት የሚቆጣጠሩት አዲስ አበባና መቀሌ ዩንቨርስቲ ሰልጥነው የመጡ ኢንጂነሮችና ፎርማኖች መሆናቸውን ምንጮቹ ሳይገልጹ ኣላለፉም። ተጨማሪ መረጃዎች ይለቀቃሉ ይጠብቁ ።

No comments:

Post a Comment