Thursday, February 16, 2017

በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መግቢያና መውጫ አጣን ሲሉ አማረሩ። ኤምባሲው ለሕወሓት በዓል የዜጎችን ስብሰባ ሰረዘ።( ቆንጂት ስጦታው

   
በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን መግቢያና መውጫ አጣን ሲሉ አማረሩ።
ኤምባሲው ለሕወሓት በዓል የዜጎችን ስብሰባ ሰረዘ።
mereja.com sudan ethiopia
ቆንጂት ስጦታው (መረጃ ኮም) – በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ሕጋዊነት ይዘን እየኖርን የሱዳን የጸጥታ ሃይሎች መግቢያና መውጫ አሳጥተውናል ሲሉ አማረሩ። ኢትዮጵያያኑ ጉዳዩን ወደ ኤምባሲ ይዝን ብንሄድም ክሱዳን ባልስልጣናት ጋር እንወያይበታልን ለፊታችን አርብ የስብስባ ቀጠሮ ይዘን እንነጋገራለን ቢለንም የስብሰባ ቀጠሮውን ሰርዞ የሕወሓት ምስረታ ቧል ላይ እንድትገኙልን ካልሆነ ቤታጩ እንድታሳልፉ ሲል ከዜጎች ጉዳይ በፊት ለፓርቲ ጭፈራ ቅድሚያ በመስጠት ኣሹፎብናል ሲሉ ተናግረዋል።
በሱዳን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የመኖሪያ ፈቃድ በማውጣት በሕጋዊ መንገድ የሚኖሩ ሲሆን በተለያየ ጊዜ በሱዳን የጸጥታ ኋይሎች ከፍተኛ መንገላታት አስር እና ዘረፋ ይድረግባቸዋል ይህ ሁሉ ችግር ኤምባሲው እያዌቀ ምንም አይነት ትብብር ለዜጎች እንደማያደርግ ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። በኣሁን ወቅት የሱዳን መንግስት በሃገሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ለኣንድ መታወቂያ የ2030 የሱዳን ፓውንድ ወይም 6000 ብር የጠዬቀ ሲሆን ይህ በሱዳን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አቅም በላይ መሆኑ እየታወቀ ኤምባሲው ዜጎቹን ወክሎ እንዲደራደር ቢጠየቅም እስካሁን ምንም እርምጃ እንዳለወሰድ ሲታወቅ የሱዳን መንግስት ይህንን የዘረፋ መመሪያውን ከ ማርች ።።።።። ጀምሮ እንደሚተገብረው መመሪያ አውጥቷል።
ኢትዮጵያውያኑ እንደሚሉት የመኖሪያ ፈቃዳችን በሱዳን የጸጥታ ኋይሎች ይነጠቃል ይቀደዳል። ገንዘባችን ይዘረፋል። ካለምንም ምክንያት ሕጋዊ ሆነ ሳለን እንታሰራለን እንገላታለን ያሉ ሲሆን ኤምባሲው ይህ ሁሉ እንደሚሆን እያወቀ መሻሻሎች እንዲኖሩ ያደረገው ጥረት የለም ሲሉ ይናገራሉ።ኢትዮጵያውያኑ የዲያስፖራው ማህበረሰብ ከሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጋር በመሆን ጫና እንዲያደርግ ተማጽነዋል።

No comments:

Post a Comment