(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ በቦረና እና በጉጂ ዞኖች በዛሬው ዕለት በ3 ግምባሮች በነጻነት ኃይሎች እና በሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የሶማሊያ ልዩ ኃይል መካከል እየተደረገ ባለው ውጊያ አንድ ሃምሳ አለቃን ጨምሮ 6 የልዩ ኃይል አባላት መገደላቸው ተሰማ::
ምንጮች እንዳስታወቁት በሕዝብ ላይ እንዲተኩስ በሕዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ መንግስት ጦር እየመራ የተላከው የሃምሳ አለቃ መሐመድ ድያድ መሐመድ በነጻነት ኃይሎች የተገደለ ሲሆን እርምጃ ከተወሰደበት በኋላም መንግስት የሰጠው የመታወቂያ ካርዱ ለሕዝብ ተበትኗል:: ከርሱ ጋር አብረውም 6 የልዩ ኃይል አባላት የተገደሉ ሲሆን ከ40 የማያንሱ የአጋዚ የሶማሊያ ልዩ ኃይሎችም መቁሰላቸውን ምንጮች ዘግበዋል::
እንደምንጮች ዘገባ በቦረና እና በጉጂ ያሉት የነጻነት ኃይሎች ከሕዝብ ጋር በመሆን እየወሰዱ ባለው እርምጃ መትረየስን ጨምሮ ሌሎች የጦር መሳሪያዎችንም ማርከዋል:: በአካባቢው ሙትና ቁስለኛ የሆኑ የሕወሓት ወታደሮችንም የመከላከያ ሰራዊቱ መኪኖች በመልቀም ላይ መሆናቸው ተሰምቷል::
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በ3 ግምባሮች እየተደረገ ያለው ውጊያ ቀጥሏል:: ዘ-ሐበሻ ተከታትላ ለመዘገብ ትሞክራለች::
No comments:
Post a Comment