Friday, February 10, 2017

የግብፁ አልሲሲ ከነጩ ቤተ መንግስት ወታደራዊ የፖለቲካና ሰብዓዊ እርዳታ ካለገደብ ተፈቅዶላቸዋል።



http://img-s-msn-com.akamaized.net/tenant/amp/entityid/AAmJIHZ.img?h=486&w=728&m=6&q=60&o=f&l=f&x=336&y=201
Minilik Salsawi : የግብፁ አልሲሲ ከነጩ ቤተ መንግስት በትራምፕ አዲስ ዜና የሚያበስር ቀጥታ የወዳጅነት ስልክ ተደወለላቸው። ወታደራዊ የፖለቲካና ሰብዓዊ እርዳታ ካለገደብ ተፈቅዶላቸዋል። ግብጽ በበላይነት የኣፍሪካን ጉዳዮች በተለይ ሽብርተኝነትን እንድትዋጋና አምባገነኖችን የመተካካት ስራ እንድትሰራ በሩ ተከፍቶላታል። አልሲሲ በትራምፕ a “fantastic guy” ተብለዋል።

የግብጹ መሪ የትራምፕን ለፕሬዝዳንትነት ማሸነፍ ሲሰማ ከኣለም ላይ እንኳን ደስ ኣሎት ያሉ የመጀመሪያው መሪ ናቸው። ለግብጽ ፌሽታ ሲሆን ወያኔ ደምብሯል።ትራምፕ ለግብጹ መሪ አልሲሲ የወዳጅነት ስልክ መደወላቸውንና የወታደራዊና ፖለቲካዊ እርዳታ ካለገደብ መፍቀዳቸውን ተከትሎ የወያኔ አገዛዝ በገንዘብ በገዛቸው አሜሪካውያን ቅጥረኞቹ በኩል በነጩ ቤተ መንግስታና በሪፑብሊካን ሴናተሮች ኣከባቢ የትራምፕን ቡራኬ ለማግኘት የሎቢ ስራ መጀመሩን በዲሲ የኢትዮጵያ ዲፕሎማት ምንጮች ገልጸዋል

No comments:

Post a Comment