Friday, February 10, 2017

አራት ኪሎ የወረደው ባለ ሁለት ጎኑ ሰይፍ እና የአቡነ ጳውሎስ ፍጻሜ

  



              አቡነ ጳውሎስ የዚህ ዘመን አርዮስ ሆነው ገና በጠዋቱ በቤተክርስቲያን ላይ ተሹመውባት ሁለት አስርተ አመታት ሙሉ የተከሉትን እሾህ ከቤተክርስቲያን ለመንቀል ምን ያህል የመንገድ እርቀትና የስንት ትውልድ ሰማእትነት እንደሚጠይቅ በሰውኛ ግምት አስልቶ መድረስ አይቻልም። አቡኑ ከመሞታቸው ትንሽ ቀደም ብሎ ለአመታዊ የህክምና ምርመራ ወደ ደቡብ አፍሪካ ያቀናሉ። ሰውየው ከድሎት የመጣ የስኳር በሽታ እንዳለባቸው ነገር ግን የለመዱት የቅምጥል ኑሮ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዳያደርጉ እንቅፋት እንደሆነባቸው ዳር ላይ የቆመው ሁሉ
የሚታዘበው ነው። ነጩ ሃኪም ከጠቅላላ ምርመራ ቦሃላ አንድ ምክር ቢጤ ጣል ያደርግላቸዋል።”ስኳሩን መቆጣጠር አልቻሉም፤ በዚያ ላይ እግርዎት አካባቢ እብጠት ያሳያል፤ ይህ ነገር በሂደት ወደ ጋንግሪን እንዳይሄድ ከወዲሁ ቢቆረጡት ጥሩ ነው” ሲል እንቅጩን ይነግራቸዋል። ሰውየው አሻፈረኝ ብለው ጥለው ወጡ። በቅርብ የተከተሉዋቸው ሰዎች “ምነው ብጹእ አባታችን ለጤናዎት የሚረዳ ከሆነ የሃኪምን ምክር ቢቀበሉት ምናለ” ቢሏቸው መልሳቸው አጭር ነበር። “እግሬን ተቆርጨ የአማራ መሳቂያ ልሆንላችሁ ነው እንዴ” የምትል ከሆዳቸው ተጨምቃ የወጣች አነጋገር ነበረች።

            ከጥቂት ወራት ቦሃላ የእመቤታችን ወርሃ ነሃሴ ጾም ስትገባ እንደልማዳቸው ለማስቀደስ በእኩለ ቀን ጎራ ይላሉ። ትንሽ ደከም ብሎንኛል አሉና ቁጭ ብለው አስቀደሱ። ነገር ግን ቅዳሴው ከማለቁ ሰውየው በላብ መጠመቅ ያዙ፤ ሰማይ መሬቱን መለየት ሲሳናቸው ከፊሉ ወደ ሃኪም ለመውሰድ ሲዘጋጅ ከፊሉ ሰውየው ከፈሰሱበት ማፈስ ጀመረ። ጉዞ ወደ ባልቻ ሆስፒታል ሆነና ሃኪም ቤት ሲደርሱ ሰውነታቸው እንደ ከበሮ ተነፋፍቶ ነበር። ሃኪሞቹ ተገቢውን እርዳታ መስጠታቸው ቢቀር ችግራቸው ምን እንደሆነ እንኩዋን በቅጡ ሳይገባቸው የሰውየው ፍጻሜ ሆነ። ያ ሁሉ ምድራዊ ክብር፣ ዝና፣ ገንዘብ፣ እግር አጣቢ፣ ቅኔ አወዳሽና አንጋሽ እንዲሁም የጠገበ አጃቢ ጀስታፖ ሁሉ ተደምሮ ነፍስቸውን የሚቀጥል አልነበረምና በጥቂት ሰዓት ውስጥ አሳዛኝ ታሪክ ሆነው አለፉ።

No comments:

Post a Comment