Tuesday, February 7, 2017

ባለፈው ዓመት ከ4 ሺህ በላይ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል ተባለ



ባለፈው ዓመት ከ4 ሺህ በላይ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል ተባለ
ትራፊክ አደጋ
ባለፈው ዓመት ከ4 ሺህ በላይ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ሕይወታቸውን አጥተዋል ተባለ – በ2008 ዓመተ ምህረት ከ4 ሺህ በላይ ዜጎች በትራፊክ አደጋ ምክንያት ሕይወታቸው ማለፉን የትራንስፖርት ሚኒስቴርን ጠቅሶ የዘገበው ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው።
የትራንስፖርት ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ “ከትራፊክ አደጋ የፀዳ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሃገራዊ ህዳሴ” በሚል መሪ ቃል የትራፊክ ደህንነት ሀገራዊ ንቅናቄ በይፋ መጀመሩን አስመልከተው ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውም ተዘግቧል፡፡
ሚኒስትሩ በሀገሪቱ በጥንቃቄ ጉድለት ሳቢያ እየደረሰ ያለው የትራፊክ አደጋ ከዓመት ዓመት እየጨመረ ነው ብለዋል።
አደጋው በአንድ ዓመት ብቻ ከ10 ሺህ በላይ ዜጎችን ለአካል ጉዳት ዳርጓልም ነው ያሉት።
ከሚደርሱ አደጋዎችም 85 በመቶ በአሽከርካሪዎች የጥንቃቄ ጉድለት ምክንያት የሚደርሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በ2008 ዓ.ም የሞት አደጋ ከደረሰባቸው ዜጎች ውስጥ 147ቱ መንጃ ፈቃድ ሳይኖራቸው ሲያሽከረክሩ በነበሩ ሰዎች አደጋ የደረሰባቸው መሆናቸውን አንስተዋል።
ችግሩን ለመቅረፍም አሁን ላይ እድሜን፣ ልምድን እና የትምህርት ዝግጅትን መሰረት ያደረገ ሕግ ለማፅደቅ በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።
ረቂቅ ሕጉ ፀድቆ ወደ ስራ ሲገባ አደጋን በመቀነስ ረገድ አስተዋፅኦ እንደሚኖረውም ማስረዳታቸውም በኤፍቢሲ ዘገባ ተመልክቷል።

No comments:

Post a Comment