Saturday, February 11, 2017

የትኛዉ የሀወሃት ባለስልጣን ነዉ ድግሪ ያልሸመተዉ? የጋምቤላ ክልል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተገኘባቸውን 9 የክልሉ ስራ አስፈፃሚዎችን ከኃላፊነት አገደ

   


የትኛዉ የሀወሃት ባለስልጣን ነዉ ድግሪ ያልሸመተዉ? የጋምቤላ ክልል ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የተገኘባቸውን 9 የክልሉ ስራ አስፈፃሚዎችን ከኃላፊነት አገደ
የኮሚሽኑ ኃላፊ ኮሚሽነር ኡሞድ ኡጁሉ፥ የጋምቤላ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ባካሄደው የጥልቅ ተሃድሶ መድረክ በክልሉ ብቁ አመራሮችን ለመለየት እንዲቻል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የተወሰደ እርምጃ ነው።
ኮሚሽኑ ይህን ተከትሎ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ባካሄደው የማጣራት ስራ ከ201 የክልሉ ከፍተኛ ስራ አስፈፃሚዎች ዘጠኙ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው ተገኝተዋል።
በመሆኑም ኮሚሽኑ እነዚህ ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ይዘው የተገኙ ከፍተኛ የክልሉ አመራሮች የትምህርትቢሮ ኃላፊውን ጨምሮ ከስራቸው እንዲባረሩ መደርጉን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ከኃላፊነታቸው የተነሱት የክልሉ የስራ ኃላፊዎች
1. ኚሙሉ ኦጋኒ፦ የክልሉ ዋና ኦዲት መስሪያ ቤቱ ምክትል ኦዲተር
2. ጋትዊች ዋር፦ የክልሉ የኮንስትራክስን ቢሮ ኃላፊ
3. ፖል ጆክ፦ የክልሉ መገናኛ ብዙኃን መረጃ ነፃነት ኤጀንሲ ዳይሬክተር
4. ሳይመን ጋትልዋክ፦ የክልሉ መስተዳደር የአስተዳደርና ማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ
5. ቱት ጆክ፦ የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
6. ቾል ኮር፦ የክልሉ መስተዳደር ምክር ቤት የመሰረተ ልማት አማካሪ
7. ሜሪ ኛንዌር ዶክ፦ በጤናና ጤና ነክ ሴቶች ኤጄንሲ የሴቶች ዩኒት አስተባባሪ
8. ኙዌች ጋችሉል፦ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ፅ/ቤት የሴቶች ዩኒት ኃላፊ
9. ኛዬር ሉልዴንግ፦ በክልሉ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የመንገድ ዩኒት አስተባባሪ ናቸው።
በዚህ የወንጀል ድርጊት የተሳተፉት ግለሰቦች ወደፊት በህግ እንደሚጠየቁ የጋምቤላ ክልል የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽነሩ አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ተናግረዋል።
በቀጣይም ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ የስራ አስፈፃሚዎች እና ባለሙያዎች ሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የማጣራት ስራው ተጠናክሮ ቀጥሏል።
እስከአሁንም የ328 ግለሰቦች የትምህርት ማስረጃ ማጣሪያ እየተደረገ መሆኑን ኮሚሽነሩ ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment