Monday, February 13, 2017

“ሳይከሰሱ የታሰሩት ሁለት ጋዜጠኞች እና አንድ ፖለቲከኛ ድንገት በተጠራ ስብሰባ ላይ በፖሊስ ኃላፊዎች ጠንካራ ትችቶችን ሰነዘሩ



****

“እኛ የታሠርነውም ሆነ በሀገሪቷ ላይ የታሠረው ቋጠሮ የሚፈታው ነፃነት የመጣ ቀን ብቻ ነው!” ~ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ

“ኢህአዴግ እና ኮማንድ ፖስቱ ብቻ፡- ለሀገር ተቆርቋሪ አድርጋችሁ አትንገሩን እኛም ስለሀገራችን ጉዳይ ያገባናል ፣ያንገበግበናል!” ~ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

“ፍቱን ወይም ስቀሉን፣ የግፍ እስረኞች ነን!” ~ ፖለቲከኛ አቶ ዳንኤል ሺበሺ

ማክሰኞ ጥር 30 ቀን 2009 “አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ”ን ተከትሎ በቦሌ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ውስጥ በኮማንድ ፖስቱ ታስረው የሚገኙ ወደ 240 የሚጠጉ እስረኞችን “ኮማንድ ፖስቱ እናንተን እንድናነጋግራችሁ እና ሐሳባችሁን ተቀብለን እንድናስተላልፍለት ልኮናል” ያሉ ሁለት የመምሪያው ዋና ሳጅን መርማሪዎች እና ሁለት ኢንስፔክተሮች አነጋገሯቸው ነበር፡፡ ያለ ክስ ተይዘው የሰነበቱት ተሰብሳቢዎቹ እስረኞችም በስብሰባው መዝጊያ ላይ የተሰማቸውን እርካታ በፉጨት እና በደማቅ ጭብጨባ ገልጸዋል፡፡

No comments:

Post a Comment