Friday, February 10, 2017

በፍኖተ ሰላም ተማሪዎች በግዳጅ ስብሰባ ተቀመጡ። በርካቶች ስብሰባውን ረግጠው ወጥተዋል።


በዛሬው እለት ማለትም የካቲት በ2/06/2009ዓም በዳሞት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርት አለ በሚል ሰበብ ተማሪዎችን በመንግስት ጣልቃ ገብነት ከትምህርት ነክ ርዕስ ውጭ ተማሪዎችን ሲያደነዝዙ አምሽተዋል፡፡ ይህ ሰብሰባ የተደረገው 9፡00-10፡30 በትምህርት ቤቱ ካድሬ ር/መምህር አቶ የስጋት ደሴ አይናለም አስተባባሪ አስገዳጅነት ነው፡፡የስብሰባው ርዕስ የመንግስትን በጎ ስራ ለተማሪዎች ማስረፅና የመከላከያ ምልመላን ለአገር አስፈላጊነት ስለመግለፅ ነው፡፡ ከስብሰባው መጨረሻም ቢራ፣ለስለሳና ዳቦ ለተማሪዎች ጋብዘዋል፡፡ አብዛኛው ተማሪዎች ስብሰባውን ረግጠው ሄደዋል፡፡ትንሽ ተማሪዎች ብቻ እስከ ስብሰባው ማብቂያ ድረስ ቆይቷል፡፡
ነፍስ የማያውቁ የአማራ ልጆችን ወያኔ እንዳይበላብን መረጃው ይዳረስ፡፡
አማራ ንቃ!!!
የአማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!!

No comments:

Post a Comment