Tuesday, February 7, 2017

አቶ አብርሃ ደስታ የዓረና ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ

አቶ አብርሃ ደስታ የዓረና ሊቀመንበር ሆነው ተመረጡ – የዓረና ፓርቲ አራተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በባለፈው ቅዳሜ እና እሁድ ጥር 27 እና ጥር 28 በመቀሌ ከተማ ውስጥ ሲካሄድ ዓረና ትግራይ ለሉዓላዊነትና ለዲሞክራሲ ሃያ አምስት የማዕከላዊ ኮሚቴ አሥራ አንድ የሥራ አስፈፃሚ አባላትን በመምረጥ መጠናቀቁ ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ፓርቲው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህር እና የፖለቲካ ሳይንስ ምሁር የሆኑትን አቶ አብርሃ ደስታን በሊቀመንበርነት እንደመረጠም ተዘግቧል፡፡
አቶ አብርሃ ደስታ ፓርቲው በአራተኛ ጉባኤው በምን ጉዳይ ላይ አተኩሮ እንደተወያየ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ሀሳብ ዋናው ጉዳይ የሀገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ነው ያሉት ሲሆን በሀገሪቱ ያጋጠመው የፖለቲካ አለመረጋጋት መንስኤው ምንድነው? እንዲሁም መፍትሄውስ ምንድነው?  በሚለው ጉዳይ ላይ መወያየታቸውን አስረድተው የተወሰኑ ዝርዝር ጉዳዮች ላይም ተወያይተው ውሳኔ እንዳሰለፉ ተናግረዋል፡፡
ስለ ኢትዮጵያ አንድነት እና ስለ ሀገራዊ ፓርቲ ምስረታም ተወያይተናል ብለዋል፡፡
የተቃዋሚ ፓርቲ አባል መሆን የትግል መንገድ ስለሆነ አንድ ሰው ሃላፊነት ሲሰጠው መቀበል እንደሚገባው እና በተሰጣቸው ሃላፊነትም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

No comments:

Post a Comment