÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷÷
የኢህኣዴግ መሪዎች በኤርትራና በሻዕብያ ያላቸው ፍቅር ገና ኣልወጣላቸውም። ግብኣተ መሬት እስኪ ገቡ ፍቅራቸው የሚወጣላቸውም ኣይመስሉም።
ሰሞኑ ሃይለማርያም ደሳለኝ ኤርትራን በተመላከተ የተለመደው የሸፍጥ ንግግር ኣድርገዋል።
“የኤርትራ ጉዳይ ትግራይ ክልል ክፉኛ እየጎዳ ስላለ የተለየ ሶስተኛ ኣማራጭ እየፈለግን ነው።” ጠ/ም/ ሃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮ- ኤርትራ ግንኙነት ኣስመልክተው የሰጡት ሓሳብ።
ከዚህ የፊት ባዶ ጭሆት ሁነው የቀሩት ንግግሮች ኣድርገው ነበር።
” የማያዳግም እርምጃ ”
” ተመጣጣኝ እርምጃ ” የሚሉት ፍኮራዎችና ቀረርቶዎች ተናግረው ነበር። እነዚህ ንግግሮች እንደጠበቅናቸው በሻዕብያና ኤርትራ ምንም ተፅእኖና ለውጥ እንዳላመጡ ታዝበናል።
ኣሁን ኤርትራና ሻዕብያ በተመለከተ “ሶስተኛ ኣማራጭ እየፈለግን ነው” ብለው ቀልደዋል። “ሲሰርቀኝ ያየሁት ሲጨምርልኝ ኣላምነውም” እንደሚባለው ከዚህ በፊት ዘራፍ ዘራፍ ብለው ወፍም ማባረር እንዳልቻሉ ኣይተናልና ኣሁንም ምንም ለውጥ እንደማናይ እምን ነው።
ስብሓትና ኢሳያስ
ህወሓትና ሻዕብያ ዕጣፈንታቸው ኣንድ ዓይነት ናቸው። ይሄ ነገር ጠንቅቀው ስለሚያውቁ እርስ በራሳቸው መቼም ኣይጨካከኑም።
ምናልባት ህወሓቶች ባድመን ለሻዕብያ ኣስረክበው እታረቃለው ሊሉን ይችላሉ። ይሄ ውሳኔም ተግባራዊ ከሆነ የኢህኣዴግ መንግስት ግብኣተ መሬት የሚከት ይሆናል።
70 ሺ ኢትዮጵያውያን ውድ ሂወታቸው የከፈሉበት መሬት ለኢህኣዴግ ስልጣን ማራዘምያ ተብሎ ተቆርሶ ለማንም ኣይሰጥም።
የጠቅላይ ምኒስትሩ የተለመደ ጭሆት የሰሙ ኣንዳንድ ወገኖች ባልተለመደ ሁኔታ በደስታ ሲፈነጩ ኣይተናል።
“ሶስተኛው ኣማራጭ” ምን እንደሆነ ሳያውቁ፣ ኣማራጩ ተግባራዊ ይሁን ኣይሁን ሳያረጋግጡ የሚሸልሉና የሚዘሉ ወገኖች ኣጋጥመውናል።
ይሄ የተለመደ ባዶ ጭሆት ተከትለው ያልተለመደ ፈንጠዝያ የሚያሰሙ ወገኖች ስንመለከት “ፈስ ያለበት ዝላይ ኣይችልም” ከማለት ምን ልንላቸው እንችላለን።
ኣቶ ሃይለማርያም ሶስተኛው ኣማራጭ ስላሉት ጉዳይ እኔ በበኩሌ ኣላምኖትም።
ምክንያቱ
ሀ) “የማያዳግም እርምጃ ”
ለ) “ተመጣጣኝ እርምጃ ” የሚሉ ፍኮራዎችዎ ውሃ በልቷቸው ሲቀር ኣያቻለውና ነው።
የኢህኣዴግ ፊተውራሪው ህወሓት በሻዕብያ ፍቅር ቅልጥ ያለና ምንም ቢሆንም በሻዕብያ እንደማይጨክን ኣውቃለው።
ሁለተኛው ፎቶ የባድመ ሰማእታት የመቃብር ቦታ ነው።
No comments:
Post a Comment