Thursday, February 9, 2017

የዞን ዘጠኝ ጉዳይ ለሰባተኛ ጊዜ ተቀጠረ



የዞን ዘጠኝ ጉዳይ ለሰባተኛ ጊዜ ተቀጠረ
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት በኢንተርቴት አምደኞቹ በእነ ሶሊያና ሽመልስና በአቃቤ ሕግ መካከል ባለው ክርክር ላይ ውሳኔ ለመስጠት መዝገቡን ለሰባተኛ ጊዜ ቀጠረ፡፡
ዛሬ ውሳኔ መስጠት ያልቻለው በጉዳዩ ውስብስብነት ሳቢያ እያንዳንዱ የችሎቱ ዳኛ እንዲመረምረው ሲባል ጊዜ በመውሰዱ እንደሆነ ፍርድ ቤቱ ገልጿል፡፡
የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኛ ሰሚ ችሎት በአቤት ባይ አቃቢ ሕግና በመልስ ሰጪዎቹ የኢንተርኔት አምደኞቹ ሶሊያና ሽመለስ፣ በፍቃዱ ሃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፉ ብርሃኔ እና አቤል ዋበላ መካከል ባለው ክርክር ላይ ዛሬ ውሳኔ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቅ የነበረ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ከውሳኔ እንዳልደረሰ አስታወቀ፡፡

No comments:

Post a Comment