Wednesday, February 15, 2017

ተስፋዬ ገብረእባብ በአዲሱ የጥላቻ መዝሙሩ የተዋህዶን እምነትንም እየሰደበ ነው -ሸንቁጥ አየለ



ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይጠብቃት እንጅ የጠላቶቿስ ድምጽ ከልጆቿ ድምጽ ጎልቶ እየተሰማ ነዉ
ሸንቁጥ አየለ
faye- ሰሞኑን አማራ እና ኦሮሞን ካላፋጀ አልተኛም ያለዉ የጸረ-ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በተስፋዬ ገብረአብ ላይ አድሮ በጣም ሲለፈልፍ ብሰማዉ ኤርትራ ምድር አንድ መስቀል የያዙ ንጹህ የተዋህዶ አባት ቢነሱልን ምን ነበር ብዬ አሰብኩ::
– ተስፋዬ ገብረእባብ በዚህኛዉ የጥላቻ ዜማዉ የኦርቶዶክስ ሀይማኖትንም አብሮ ተሳድቧል::ይሄ ሻቢያ እና ወያኔ ላይ የሰፈረ ርኩስ መንፈስ በጸሎት ጭምር ካልተባረረ የኢትዮጵያን ህዝብ ፈጽሞ አጫርሶ : ኢትዮጵያ የም…ትባል ሀገርንም አጥፍቶ ግቡን ካልመታ የሚቆም አልሆነውም::
-ተስፋዬ ገብሬእባብ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገር ማንም ባለቤት እና ጠባቂ እንደሌላት እና ሁሉም ወገን ይሄን የኢትዮጵያዊነት ጉዳይ እንደገፋዉ ያዉቃል::ሆኖም የሱ ግብ እስከመጨረሻዉ ድረስ ኢትዮጵያዊነትን ማንም የማይፈልገዉ እና የተጠላ ማድረግ ነዉና የኢትዮጵያ ብሄረሰቦችን እየነጣጣለ እና አንዱን እየሰደበ አንዱን የደገፈ እየመሰለ ኢትዮጵያዊነትን ስሩን የመነቃቀል ጥረቱን ቀጥሏላ::
-የሻቢያ መንፈስ: የወያኔ መንፈስ: እንዲሁም ማናኛዉም የጸረ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ መገለጫዉ አንድ ነዉ::ሀሰት እና ጥላቻን በኢትዮጵያ ህዝብ መሃከል መርጨት ነዉ:: ሌላዉ ቀርቶ በማንም ሀገር ከተደረገዉ ዉህደት በላይ በኦሮሞ ህዝብ እና በአማራ ህዝብ መሃከል ከ20 ሚሊዮን በላይ ዉህድ ዜጎች እንደተገኙ እና ይሄ ሁለት ታላላቅ ህዝብ በከፍተኛ መስተጋብር ዉስጥ እንደሆነ እነ ተስፋዬ ገብረእባብ ያዉቁታል::ግን የሚሰብኩት ስብከት አማራ እና ኦሮሞ የማይዋደዱ ሀይሎች ናቸዉ በማለት በሁለቱ ህዝቦች መሃከል የማያባራ ጦርነት እንዲቀሰቀስ ነዉ::
– በኦሮሞ እና በአማራ መሃከል ያለዉን ዉህደት: የስነ መልከዓምድር አንድነት: የስነልቦናና : የማህበራዊ: የተቋማት : የመንፈሳዊ እና የባህል ቅርርብ ብሎም የመጻኢ ጊዜ የጋራ ህልዉና ትሥስር ማንሳት አይፈልጉም::እነሱ የሚፈልጉት በተረት ተረት የታሹ በደል እና ግፍ በህዝቦች ልብ ዉስጥ እየረጮ ህዝቦች እርስ በርሳቸዉ ለሌላ በደል እና ግፍ እንዲፈላለጉ ማድረግ ነዉ::
– በዚህም እነሱ አንዴ የአንዱ ደጋፊ ሌላ ጊዜ የሌላዉ ነጻ አዉጭ መወሸቂያ በመምሰል በህዝብ ላይ ሲቀልዱ ሊኖሩ ነዉ::የአረብ እና የጣሊያን የባንዳነት ስነ ልቦና ጨዋታን የተካነዉ የሻቢያ ስትራቴጅስት የቱንም ያህል ቢቀላምድ ኢትዮጵያ ጸንታ ማንነቷን ማስጠበቋ አይቀርም::
-ተስፋዬ ገብረአብ አዲስ የተንኮል ዜማ የለቀቀዉ ምን የስትራቴጅ ለዉጥ ከሻቢያ ጓዳ ታስቦ ነዉ? ብሎ መጠዬቅ ግን መልካም ነዉ? ነዉ ወይስ አዲስ መጽሀፍ ጽፎ እንደለመደዉ ይሄ የማይረባ እና ሲሰድቡት የጠላቶቹን ስድብ እየገዛ የሚያነብ አሽክላ ሁላ ምናምንቴ ተረት ተረት ጽሁፍ እንዲያነብለት ቅድሚያ መንገድ እየጠረገ ነዉ? ወደፊት በደራሲነት እና በጸሃፊነት ስም የሰዉ ልጆችን ልብ በማሻከር እና ልዩነት በመዝራት የተጠመደዉን ርኩስ መንፈስ አከርካሪ ለመስበር በተስፋዬ ገብረእባብ ላይ እና በሌሎችም ጸረ ኢትዮጵያዉያን ላይ ያደረዉን ጸረ ኢትዮጵያዊ መንፈስ አስለፍልፎ የሚያባርር ካህን ከክርስቶስ ዘንድ ይሰጠን ይሆን?
-ከጠላቶቻችን ኪስ ዉስጥ መድሃኒት ለህዝባችን ፍለጋ እንደማይቻል ግን ያዉ የሰሞኑን የተስፋዬን ንግግር አድምጦ መልሱን ማግኘት ነዉ::የተስፋዬ ትልም ኢትዮጵያን ነገም የጨለመ ሀገር ማድረግ እንጅ ነጻ እና ህዝቦች የሚግባቡባት ሀገር ማድረግ አይደለም:: ከሻቢያም ሆነ ከወያኔ ሀይላት ፍቅር እና አንድነት ወይም የነጻነት መንፈስ መጠበቅ በራሱ እነዚህ ሀይሎች ላይ ስለሰፈረዉ እርኩስ መንፈስ በደንብ አለመረዳት ነዉ:: የረከሰ እና የወደቀ መንፈስ ካላቸዉ ጸረ ኢትዮጵያዉያን ሀይላት ቋት ዉስጥ ለኢትዮጵያ ድህነት የሚሆን ምንም አይነት ነገር የለም::
-ዋናዉ ማጠቃለያዉ ግን ኢትዮጵያዉያን ፖለቲከኞች እርበርሳችሁ ያለባችሁን የሀሳብ ልዩነት ቁጭ ብላችሁ ብትነጋገሩ ለሁሉም ወገን የምትመች ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን መፍጠር ትችላላችሁ::በተለይም የአማራ እና የኦሮሞ ምሁራን እንዲሁም ደግሞ ፖለቲከኞች ከፍተኛ የሆነ የኢትዮጵያን ህዝብ የማዳን ሀላፊነት የወደቀባችሁ ይመስለኛል::ያላሰለሰ ስራ ማከናወን አለባችሁ:: ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀገሪቱ መራራ ዉድቀት እና የእርስ ጦርነት ዉስጥ ከመዉደቋ በፊት እየተቀራረበ በመነጋገር የጋራ መፍቴሄዎችን ቢያፈላልግ መልካም ነዉ::አብሮነት ይሰበክ::የጋራ መጻኢ ዘመን ይታቀድ::ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ በሁሉም ልብ ዉስጥ ትታሰብ::ሁሉም ኢትዮጵያዊ የኢትዮጵያን መጻኢ በራሱ ቁጥጥር ስር ለማድረግ ይስራ::ጠላቶቻችን የሚያነሷቸዉን የጥላቻ ሀሳቦች በፍቅር እና በመቻቻል ብሎም በእዉነተኛ የሀሳብ መግባባት እንዲሰናሰኑ ይሁኑ::ይቻላል እና::
ኢትዮጵያን እግዚአብሄር ይጠብቃት !

No comments:

Post a Comment