Monday, February 13, 2017

የመንግስት ባለስልጣናት የምክር ቤት አባላትና ዳኞች ከችግር የራቀ ኑሮ እንዲኖሩና ለጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ አዋጅ ፀደቀ

   


በተለያዩ ምክንያቶች ከኃላፊነታቸው እንዲነሱ የሚደርጉትን የመንግስት ባለስልጣናት ልዩ ጥቅም የሚያስከብረው አዋጅ ፀደቀ፡፡
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሰሞኑን ያፀደቀው ይኸው አዋጅ ቁጥር 10003/2009 በተለያዩ ምክንያቶች ከኃለፊነታቸው የሚነሱ የሀገርና የመንግስት መሪዎች፣ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት የምክር ቤት አባላትና ዳኞች ከችግር የራቀ ኑሮ እንዲኖሩና ለጥቃት ተጋላጭ እንዳይሆኑ ለማድረግ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
አዲስ የፀደቀው የማሻሻያ አዋጅ ከኃላፊነታቸው የሚነሱ የመንግስት ባለስልጣናት የመቋቋሚያ አበል፣ የሥራ ሰንብት ክፍያ፣ የቤት አበል እና የተሸከርካሪ አገልግሎት የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ በተሻሻለው አዋጅ መሰረት ከኃላፊነታቸው የሚነሱት የመንግስት ባለስልጣናት እንዲያሰልጥን ደረጃቸውና እርከናቸው የመኖሪያ ቤት፣ የመቋቋሚያ አበል፣ የስራ ስንብትና የተሸከርካሪ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡
ከኃላፊነታቸው የሚነሱ ባለስልናቱን ልዩ ጥቅም የሚያስከብር የተሻሻለው አዋጅ ለአገሪቱም ሆነ ለባለስልጣናቱ ጠቃሚ መሆኑን የገለፀው የማሻሻያ አዋጁ ተግባራዊ በሚደርግበት ጊዜ ተጨማሪ ወጪዎችን ማስከተሉ አይቀሬ ጉዳይ ቢሆንም መጪው ዲሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ለመጠበቅ የሚወጣ ወጪ በመሆኑ መከፈል ያለበት ወጪ መሆኑን አመልክቷል፡፡
የተሻሻለው አዋጅ የሌሎች አገራትን ተሞክሮ መሰረት አድርጎ የተሰራ መሆኑን አገሪቱ በአሁኑ ወቅት ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ተግባራዊ እየሆኑ ያሉ የአገርና የመንግስት መሪዎች ጥቅማጥቅሞች በሙሉ እንዲሻሻሉ ማድረጉ አስፈላጊ ሆኖ አለመገኘቱ የማሻሻያ አዋጁ በፀደቀበት ወቅት ተገልጿል፡፡

No comments:

Post a Comment