Monday, February 13, 2017

ሰበር የመረጃ ግብአት – ነቢዩ ሲራክ


ጅዳ ውስጥ አንድ የኢራቅ አውሮፕላን ከእሳት ቃጠሎ አደጋ ተረፈ !
=========================================
* በውስጡ የነበሩይ 356 ተሳፋሪዎችን ይዞ ነበር
* አንድም ጉዳት የደረሰበት ሰው የለም

የጸሎት ተጓዦችን የያዘውና ንብረትነቱ የኢራቅ የሆነ እውሮፕላን ጀዳ በሚገኘው የንጉስ አብድልአዚዝ አለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ በማረፍ ላይ እንዳለ በጎማው ላይ ጭስ የቀላቀለ እሳት ተከስቶ በአየር ማረፊያው የእሳት አደጋ ብርጌድ ባደረጉት ፈጣን ርብርብ ቃጠሎው በቁጥጥር መዋሉ ታውቋል። ትናንት ማለዳ ከኢራቅ ተነስቶ ጅዳ ሲገባ በጎማው ላይ ጭስ መመልከቱን ምድር ላይ ለሚገኙ የአየር መንገዱ መቆጣጠሪያ ሰራተኞች ሪፖርት ባደረገው አብራሪ አማካኝነት አውሮፕላኑ አንዳረፈ እሳቱን ለማጥፋት የሳውዲ እሳት አደጋ ቡድን እሳቱን ሊቆጣጠረው መቻሉ ተጠቁሟል ። መሬት ላይ እንዳረፈ ዘመናዊ የእሳት መከላከያ መሳሪያ የታጠቀው የእሳት አደጋ ብርጌድ በአውሮፕላን ውስጥ የነበሩትን 356 ተሳፋሪዎች አንድም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከአየር መንገዱ ሰራተኞች ጋር በመተባበር ወደ እንግዳ መቀበያ ማረፊያ መወሰዳቸው ታውቋል።
ወደ እስልምና ቅዱስ ቦታዎች መካና መዲና ለጸሎት የሚመጡና ጸሎታቸውን አደርሰው የሚመለሱ ምዕመናንን በማስተናገድ በኩል ጅዳ የሚገኘው የንጉስ አብደልአዚዝ አየር ማረፊያ ዋና መግቢያና መውጫ በር ሲሆን ከመላው አለም ወደ ሳውዲ የሚመጡ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ምዕመናንን በአመት በማስተናገድ የሚተካከለው የለም ።
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 5 ቀን 2009 ዓም

No comments:

Post a Comment