Thursday, February 9, 2017

ለአዲስ አበባ መጤ ኦሮሞዎች ናቸው – ሰርጸ ደስታ



ፀጋዬ አራርሳ
ሰሞኑን አንድ ዶ/ር ጸጋዬ አራርሳ የተባሉ ግለሰብ በፎረም 65 ላይ አዲስ አበባን አስመልክቶ የተናገሩት ንግግር ብዙዎች ያደመጣችሁት መሰለኝ፡፡ እኔም ለማደመጥ መከርኩ ነው የሚባለው እንጂ አደመጥኩ ለማለት ይቸግራኛል፡፡ ምክነያቱም ግለሰቡ ሲያወሩ አለማቋረጥ ብቻም ሳይሆን የሚያወሩት ሁሉ ምሁር ነኝ ከሚል ሰው እጅግ ስለከበደኝ ነው፡፡ ጸጋዬ በብዙ ነገር ጥላቻ ያመረቀዘ የሚመስል ንግግር ከዚህም በፊት ሲናገሩ ሰምተናል፡፡ በዚህ ቃለምልልስ የሰማሁባቸውን ያህል ግን ሐበሻ ያሏቸውን ሕዝቦች እንደሚጠሉ አልገመትኩም፡፡ ግለሰቡ እንዲህ ማንነታቸው በይፋ ለሕዝብ ማሰወቃቸው እንደ ጥሮ ነገር ብቆጥረውም ለደጋፊዎቻቸውና ለራሳቸውም እጅግ አዘንኩ፡፡ የሄን ላቆየው ወደተነሳሁበት ነጥብ ልመለሰ፡፡
የኦሮሞ አክቲቪስት ነን የሚሉና የኦሮሞን ሕዝብ ማንነቱን አጥቶ የባዘነ ያደረጉት በኦሮሞ ሕዝብ የሚነግዱ የተወሰኑ ቡድን አባላት የኢትዮጵያን ታሪክ 100ዓመት ብለው ሙጭጭ የሚሉበት ምክነያት ግልጽ ነበር፡፡ ከዚህ ከዘለለ እነሱ ለተነሱበት ዓላማ የሚመች ታሪክ የለም፡፡ እና ሌላው ይቅርና የኦሮሞ ሕዝብ ከደቡብ ወደ ሰሜን የተንቀሳቀሰበትን ታሪክ እንኳን  እንዲነሳባቸው አይፈልጉም፡፡ ይህ የሆነው የዛሬ 400ዓመት ገደማ ነው፡፡ እረ እንደውም ገና 400ዓመትም አልሞላውም፡፡ ከ400ዓመት በፊት እንኳንስ አዲስ አበባ አርሲና ባሌም የሌሎች ሕዝቦች መኖሪያ ነበር፡፡ አዲስ አበባና አካባቢዋም ያኔ የሌሎች ሕዝቦች መኖሪያ ነበር፡፡ ሊሆን የሚችለው ደግሞ ጸጋዬና መሰሎቹ ሐበሻ ብለው እጅግ የሚጠሏቸ የሸዋ ነበር ሕዝቦች ጉራጌ፣አማርኛ ተናጋሪው ሸው የመሳሰሉት ናቸው፡፡ ለአዲስ አበባና አካባቢዋ መጤ ከተባለ ከሌላ ቦታ የመጣው ኦሮምኛ ተናጋሪው ነው፡፡ ይህ እንግዲህ ታሪክ በውል የሚያውቀው እውነት ነው፡፡ የዛሬ 100ዓመት የነበሩ ሰዎች እኮ የዚያ ቦታ ነባር አያቶቻቸውን ያውቃሉ እኮ፡፡ ይህ ማለት ዛሬ አዲስ አበባና ዙሪያዋ የሚኖራው ኦሮምኛ ሕዝብ ነባር አደለም ለማለትመ አይቻልም፡፡ አብዛኛው ወደ ኦሮምኛ ተናጋሪነት የተቀየረ ነውና፡፡  ጥላቻ ያመረቀዘ ልብ ሕሊና አይገዛውምና ማንም የፈለገውን ቢል እውነት ከእውነትነቷ ሌላ ነገር የላትም፡፡  ለመሆኑ ግን እኖርበታለሁ በሙሉት አገር ጸጋዬ ስለአቦርጅናሎች ምን ያስባሉ;
ሌላው ተናጋሪው ጸጋዬ ሐበሻ የሚባለውን ሕዝብ ምን ያህክል እንሚጠሊት ነበር የራሳቸው አንደበት የጭንቅላታቸውን ማንነት ያሳበቀባቸው፡፡ የሐበሻ ጉዳይ ከተነሳ ደግሞ ኦሮሞም ሐበሻ እንደሆነ እኔ አሳምሬ አውቃለሁ፡፡ ሐበሻ በደም የሚነበብ ነገድ እንጂ ቋንቋም ባሕልም አደለም፡፡ መላዋ ኢትዮጵያ ደግሞ የሐበሻ ምድር ነች፡፡ ሐበሾች ከሌሎች ሕዝቦች ይለያሉ፡፡ ዘመናዊው የመለዘር ጥናት እንደሚያሳየን ሐበሻ በውል የራሱ የሆኑ ሁለት ነገዶች እነዳሉት  እናያለን፡፡ አንዱ አሁን በኢትዮጵያ ምድር የሚኖረው አሪ የተባለው ሕዝብ ሲሆን ሌላው በመቀላቀል ሊሆን ይችላል በሁሉም ጎልቶ የሚታይ ግን ብቻውን የማይታይ ኬንያ ውስጥ ካሉት ማሳዮች ጋር የምንጋራው አንድ ነገድ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ነገዶች ኢትዮጵያዊ መሠረት የላቸው ሆኖ ሐበሻ በተጨማሪ ከመካከኛው ምስራቅ አገራት ከሚኖሩ ላቫንት ከተባሉት ጋር ከ40-50 የሚሆንውን ደሙን ይጋራል፡፡ ሐበሻ የሚባለው ሕዝብ ከመሠረቱ ድብልቅ ማለት ነው፡፡ በእርግጥም ይህን ማንነቱን ዛሬ ሳይንስ በማያሻማ ሁኔታ የሳየዋል፡፡ ይህ ነው የሐበሻ ማንነት፡፡ ከዛ በተረፈ ሐበሻ ተብለው የሚታወቁት አገራት ሰሜን ሱዳን፣የመን፣ ሶማሊያ፣ ጂቡቲና፣ ኤርትራ ውስጥ የሚኖሩትን ሕዝቦች ሑሉ ነው፡፡ ለእነዚህ ሕዝቦች ሁሉ መሠረታዊ አባት ተብለው የሚታመኑ ደግሞ ኢትዮጵያ የምትባለው ምድር ይኖሩ የነበሩ ናቸው፡፡ አሪ አንዱ መሆኑ ተረጋግጧል ሌላው ስለተደባለቀ በትክክል እስካሁን ባይታወቀውም ወደፊት ተካተው በሚጠኑ ሕዝቦች ሊታወቅ ይችላል፡፡ እነዚህ አባቶች ከሌሎች አፍሪካውያንም ፍጹም ልዩ የዘር ሀረግ ያላቸው ናቸው፡፡  ጋዬ ሐበሻ እንዳልሆኑ ማረጋገጫ ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ያ ከሆነ ደግሞ በማያገባቸው ሕዝብና አገር ላይ ሊውም በጥላቻ የመናገር መብት ሊኖራቸው አይችልም፡፡ እናቴ ኦሮሞ አደሉም ይላሉ ደግሞ እዛው፡፡ እኔም ያገባሁት ኦሮሞ ካልሆነች ሴት ነው ይላሉ፡፡ ይህን ስሰማ አስደንጋጭ ነው የሆነብኝ ጭራሽ፡፡ ለጸጋዬ ከኦሮሞ ሌላ ሕዝብ አይመቻቸውም፡፡ እናቱን ወይም አባቱን የሚጠላ ደግሞ ….   ጸጋዬ ጥላቻንና ነገርን በማንበብ ጊዜ ከሚያጠፉ ጥቂት ስለ ማንነት ቢያነቡ መልካም በሆነላቸው፡፡ ከዚህ በፊት የሚከተለውን የሐበሻን ማንነት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳየውን የዘመናችን ሳይንስ የጥናት ውጤት እንዲያነቡ ጋብዤያቸው ነበር፡፡ ያኔም ኢትዮጵያዊ የሚባል ማንነት የለም ስላሉ ነው፡፡ በቅርብም ለብዙ ሰዎች የሄንኑ ጋብዤ ነበር፡፡ የፈረንጅ ሥምና የኢንጊሊዘኛ ጀርገን ቃላት  ምሁር ከመምሰል ተጨባጭ እውነትንና ጥበብን ቢጋፈጧት እላለሁ፡፡ በድጋሜ ሊኒኩ ይሄውልዎ ያንብቡት፡፡ በዛውም ብዙ ነገር ያውቁበታል፡፡
ሌላው የጸጋዬና መሰል ቡድናቸው ከሚጠላው አንዱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነትን ነው፡፡ ታሪክ ይህች የዚች ቤተክርስቲያን እምነት ተከታዮች ከማንም በፊት ቅድሚያ በዚያች አገር እንደነበራቸው ሊክደው አይችልም፡፡ ዛሬ ጸጋዬ ሌሎችን መጤ በሚሉበት አካባቢና ዙሪያ ያሉ የኦርቶዶክስ ቤትክርስቲያናት እኮ በሺዎች በሚቆጠሩ ዓመታት በእነዛ ቦታዎች ነበሩ፡፡ እንደው ለምልክት የዙቋላ አቦንና የአዳዲ ማሪያምን ማሰብ በቂ ነው፡፡ እነ ወንጪና የዝዋይ ሐይቆችስ ዛሬም ድረስ ምን እየተናገሩ ነው;
ሌላው ስለአዲስ አበባ ሁሉንም ነገር የሚያውቁት ሆነው ተናግረዋል፡፡ እንደውም ስትመሠረት ጀምሮ የነበሩ ያህል ነበር የሚያወሩት፡፡ አባቴ እጄን እየጎተተ አሳይቶኛል ይላሉ፡፡ ያ መብታቸው ነው፡፡ ለሚኒሊክ ያላቸውን ጥላቻ የሚገልጹበት ቢያጡ የሚኒሊክን ቤተመንግስት ምሽግ እንጂ ቤተመንግስት አይመስልም ይላሉ፡፡ እንደ አንድ ምሁር ይቅርና አንድ ራሱን እንዳወቀ ሰው ጥሩ አደለም፡፡ ጥሩ ያልሆነው ደግሞ ለአደማጭ ብቻ ሳይሆን ለተናጋሪው ነው፡፡ እኔ ዋናውን ቤተመንግስተ አላውቀውም፡፡ ብዙ ሕዝብ ሟቹ ጠ/ሚኒስቴር በሞቱ ጊዜ እድሉን አግኝቶ ገብቶ ነበር፡፡ እኔ ለቅሶ ስላልሄድሁ አላየሁትም፡፡ የሚኒሊክን ቤተመግስት ግን ተጋብዤ ገብቼ ለማየት እድሉ ገጥሞኛል፡፡ ቤተመንግስቱ ውስጡ ከማማሩም በላይ የተሠራበት ቦታ ጸጋዬ እንዳሉት ለምሽግነት ሳይሆን ለመዝናኛነት ታስቦ ነው የሚመስለው፡፡ ተስፋዬ ወታደር ስላልሆኑ ምሽግ እንዴት ያለ ቦታ እንደሚሰራ ባይገባቸው አይደንቅም፡፡ ቤተመንግስቱ ግን ታስቦ የተሠራው የፍል ውሃን ለመጠቀም ነው፡፡ አካባቢውም በወቅቱ ጫካ እንጂ ሰውም ያለበት አልመሰለኝም፡፡ እኔ ጸጋዬና መሠሎቻቸው እጅግ የሚጠሉት ታሪክ ስለሆነ የፈለጉትን ይበሉ እንጂ እውነታው ይሄ ነው፡፡ አሁን ላይ እንኳን ብዙዎች የሚያደንቁት የሚኒሊክን ነው እንጂ ዋናውን ቤተመንግስት አደለም፡፡ እኔ ሁለቱንም ባለማየቴ አላወዳድርኩም፡፡
ሌላው ያሳዘነኝ የጋዘጠኛው አጠያየቅ ነው፡፡ ይሄ ለነገሩ የብዙ ጋዜጠኞች ችግር ነው፡፡ አንድን ጉዳይ አንስተው ለማወያየት ሲሞክሩ ትንሽ እንኳን ዝግጅት አያደርጉም፡፡ ሲሆን ሲሆን ጠለቅ ያለ እውቀት በኖራቸው፡፡ ብዙዎች በዛ ደረጃ አደሉም፡፡ ጸጋዬን ያናገረው ጋዜጠኛም ያየሁበት በሚጠይቀው ጉዳይ ጠለቅ ያለ ዕውቀት እንደሌለው ነው፡፡ ከዚህ ሌላ አብዛኞቹ ጋዜጠኞች ተጠያቂውን ላለማስቀየም ይሁን ሌላ ባይገባኝም ተጠያቂው ተሳስቶም ይሁን አውቆ የተሳሳተ ነገር ሲናገር አያርሙም፡፡ ለሁሉም የታዋቂውን የኤስቢኤስ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃን አጠያየቅ ቢያደምጡ እላለሁ፡፡ ካሳሁን በሚጠይቃቸው ጉዳዮች ካለው የጠለቀ ግንዛቤ ባሻገር ተጠያቂዎች መስመር ሲስቱ አጣርቶ ይጠይቃቸዋል ሆን ብለውም ከሆነ ሕዝብ ይሄንኑ ማንነታቸውን ያውቅ ዘንድ ከተጠያቂው አንደበት ራሱ ለሕዝብ ያስነብባቸዋል፡፡ ጸጋዬንም ማንነታቸውን ለሕዝብ በይፋ ያጋለጠው ይሄው ጋዜጠኛ እንደሆነ እናስታውሳለን፡፡ ከዚያ በፊት ጸጋዬ ምሁር በሚል የኢትዮጵያ ጉዳይ በተነሳበት ሁሉ ዋና ተናጋሪ እንግዳ ሆነው በየሚዲያው ይቀርቡ እንደነበር አንዘነጋም፡፡ በኢትዮጵያዊነት የማያምን ግለሰብ ዋና የኢትዮጵያ ጉዳይ ተንታኝና መፍትሔ ሰጭ ሲሆን ተመልከቱ፡፡
ሌላው ጋዜጠኞች ነን የምትሉ ቢቻል በአንድ ላይ ካልሆነ ደግሞ በተለያየ ጊዜም ቢሆን የተለያየ አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ማናገርን ለመዱ፡፡ ይሄንንም ካሳሁንን አብነት አድርጉት፡፡
ሌላው በተለይ የኦሮሞ ሕዝብ እነዚህን አክቲቪስት ነን እያሉ ከማንነቱ ባዶ እያደረጉት ያሉት የሕዝብና የአገር ጠላት ሆነው የተነሱትን ሊዋጋቸው ይገባል ባይ ነኝ፡፡ እነዚህ ቡድኖች በተለይ የኦሮሞን ሕዝብ ከኢትዮጵያዊነት ተሳትፎው ባዶ እያደረጉት ብቻም ሳይሆን ከአጎራባቾቹ ሁሉ ጠላት ሆኖ እንዲታይ እያደረጉት ነው፡፡ ቡድኖቹ በኦሮሞ ሕዝብ የሚነግዱ የኦሮሞን ሕዝብ እንወክላለን በሚል ጥላቻን በሕዝቦች መካከል ተፈጥሮ ሕዝቡ እርስ በእርሱ ሲባላ ማየትን የሚናፍቁ ናቸው፡፡ እንደው እንበልና ዛሬ ኦሮሞ እየተባለ የሚጠራው ሕዝብ የሚኖረበት ቦታ ሁሉ ይዞ ለብጫው ቢገነጠል በማግስቱ ምን እንደሚመስል አስቡት፡፡ በዚህ ላይ እነዚህ ጠላቶቹ ገዥ ቢሆኑ፡፡ ዛሬ የምናያት ሱማሌ በአንጻሩ ያኔ አሁን ያለችበት ሁኔታ ሰላም የሰፈነባት ያስብላታል፡፡  ወንጀልን በሕዝብ ሥም በይፋ እየተገበሩም ነው፡፡ በቅርቡ በኢሳት ቲቪ ቀርበው የተናገሩትን ፕ/ር ላሬቦን የኦሮሞን ሕዝብ ሰድበሀል በሚል ዘመቻ ከፍተው ሰንብተው ነበር፡፡ ፕ/ሩ የተናገሩት የዚያን ያህል ባልተጋነንም ነበር፡፡ ችግሩ እነዚህ ቡድኖች በአገኙት አጋጣሚ ጥላቻንና በቀለኝነትን ስለሚያስቡ እንጂ፡፡ ከዚህ በፊትም የጀርመን ድምጽ ጋዜጠኛውን ሊውም ምሁራኖችን ስለኦሮሞ ሕዝብ እንዲናገሩ ባወያየ ሁከት መፍጠራቸው አይዘነጋም፡፡ በቃ እነሱ ኦሮሞን ወክለው የትኛውንም ወንጀል ሳይቀር መብት ያላቸው ነው የሚመስላቸው፡፡ አንዳንዶቹ በሚኖሩበት አገር ወንጀል ሊሆን የሚችል ንግግርን መናገራቸውን አንዘነጋም፡፡ የሰውን አንገት በሚጫ እቀጥፋለሁ እያለ የሚናገር ግለሰብ ሥርዓት በአለበት አገር የሚጠይቀው ስላለኖረ እንጂ ይልቅ ከሥራ አደለም ወይህኒ ሊያሶርድ የሚችል ምን አልባትም በጽንፈኛ አሸባሪነት በተጠየቀ፡፡ ዲያስፖራው ከነፈሰው ጋር እየነፈሰ ከሕዝብና አገር ጠላቶች ጋር እየተንጋጋ ብዙ ጊዜ በድሎናል፡፡ ከዚህ በኋላ ዕድል አንሰጣቸውም፡፡ እናውቃለን የሚሉትን ታሪክ እንዲናገሩ ሲጋበዙ በየሚዲያው ምሁር ሆነው የምናያቸው በጥላቻና በበቀል ነው፡፡  ሕዝብ ሁሉ ግልጽ እንዲሆንለት የምንፈልገው ይሄ ቡድን ልዩ ሴራ የየዘ አይሲስን ወክሎ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀስ አካል በመሪ ተዋናይነት የሚመራው ቡድን ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የኦሮሞን ሕዝብ እንደመሣሪያ ሊጠቀምበት ነው የፈለገው፡፡ ዙሩን ከአከረሩት ማክረሩ ለማን እንደሚጠብቅበት ቆይተን እናየዋለን፡፡ ይህ ቡድን ለኦሮሞ ሕዝብ በእውነት የሚታገሉ ቡድኖች እንዳይመጡ ተጠንቅቆ ከሚሰሩት ነው፡፡ የእነመረራና በቀለ ቡድን ለዚህ ቡድን እጅግ ያስፈራዋል፡፡ አሁን ላይም ያለብት ትልቁ ችግር ሕዝብ ፊቱን ወድ እውነተኛ ታጋዮቹተ መመለሱ ነው፡፡
 
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይጠብቅ!
 
አሜን!
ሰርጸ ደስታ

No comments:

Post a Comment