Friday, February 17, 2017

በሱዳን ካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፖሊስ እንደተክበበ ነው ፤ ስድሳ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል። (ቆንጂት ስጦታው)

    


VIDEO : በሱዳን ካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ በፖሊስ እንደተክበበ ነው ፤ ስድሳ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን ታስረዋል። (ቆንጂት ስጦታው)
ቆንጂት ስጦታው፡መረጃ ኮም ፦ከካርቱም የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች ምንጮች የሚወጡ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤምባሲና ተቃውሞ ሊያሰሙ ኤምባሲው ደጅ ላይ በተሰበሰቡ ኢትዮጵያውያን መካከል በተነሳ ችግር ምክንያት ስድሳ የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን መታሰራቸው ተጠቁሟል።
ሰሞኑን የሱዳን መንግስት በሕጋዊነት በሃገሩ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ከ አቅም በላይ ክፍያ በመጠየቅ ይመኖሪያ ፍቃድ እንዲያወጡ ያወጣውን ሕግ በመቃወም ኤምባሲው እንዲደራደርላቸው ጠይቀው ስምምነት ላይ የተደረሰ ቢሆንም ኤምባሲው ከዜጎች ጉዳይ በፊት ለሕወሓት አርባ ሁለተኛ አመት ቅድሚያ በመስጠት የዜጎችን የውይይት ስብስባ በመሰረዙ ምክንያት ኢትዮጵያውያኑ ለተቃውሞ ኤምባሲው በመሔዳቸው ኤምባሲው የሱዳን ፖሊሶችን በመጥራት ኢትዮጵያውያኑን በማስከበብ ማሳፍሱ ታውቋል።
የታፈሱ ኢትዮጵያውያን ኣማራት ሻራዋህድ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ ከታሰሩ በኋላ ማምሻውን በሁለት አይሱዙ ተጭነው ሰጃና ወደሚገኝ ጣቢያ መወሰዳቸውን ለኤምባሲው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ተናግረዋል።ኤምባሲው በከፍተኛ ጥበቃ ስራ የሚገኝ ሲሆን የሕወሓት በዓልን እጅግ በቀዘቀዘ ስሜት በዝግ መከበሩን ዲፕሎማቶቹ ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment