ወጣቱ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ የማንነት ኮሚቴ አባል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ | መርዝ ተሰጥቶት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬ አለ፤| ሙሉቀን ተስፋው
ወጣት አብድልረዚቅ ሞሳ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት ጥያቄን አንግበው ከሚንቀሳቀሱ የዐማራ ተወላጆች ግምባር ቀደም ይጠቀሳል። በአዲ ረመጥ፣ በኹመራ፣ በመቀሌና በሌሎችም ቦታዎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል በሕግ አግባብ ለመጨረስ ብዙ ለፍቷል።ወጣት አብድልረዚቅ ሞሳ የወያኔ አገዛዝ ሊይዘው በፈለገ ጊዜ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ ከጊዜው እስር ቢያመልጥም የገጠመውን የጤና እክል በሚገባ እንዳይታከም ሆኗል። ሕመሙ ሲጠና ከሁለት ወራት በፊት በድብቅ ባሕር ዳር ታክሞ ወደ አዲረመጥ ተመለሰ። ሆኖም ሕመሙ ተባብሶበት ዛሬ የካቲት 12 ቀን 2009 ዓ.ም ከሰዐት በኋላ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
መረጃውን ያደረሱን ሰዎች እንደሚሉት የሕመሙ መንስኤ ወያኔዎች መርዝ ሰጥተውት ሊሆን እንደሚችል ጥርጣሬያቸውን ገልጸዋል። ወጣት አብድልረዚቅ በ30ዎቹ መጀመሪያ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት እንደነበር ለማወቅ ችለናል።
ለወዳጅ ዘመዶቹና ቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን!!
No comments:
Post a Comment