Thursday, February 16, 2017

ከብዙ ማጉላላት በኋላ ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ እና ሰማያዊ አመራሮች እውቅና ሰጠ – የሚሊዮኖች ድምጽ

    


16780430_617476631771460_1370417707_n 16780023_617476731771450_1559704480_n
መኢአድ እና ሰማያዊ በአገር ቤት ሰላማዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ናቸው። የመኢአድ ሊቀመንበር ዶር በዛብህ ደምሴ ናቸው። ዶር በዛብህ አንጋፋ የመኢአድ አመራር ሆነው ለብዙ አመታት አገልግለዋል። በቅንጅት ጊዜ የቅንጅት ብሄራዊ ምክር ቤት አባልም ነበሩ።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ከአንጋፍ ወጣት ፖለቲከኞች መካከል አንዱ የሆነውና ከነሃብታሙ አያሌው ጋር ለሁለት አመት ታስሮ የነበረው የሺዋስ አሰፋ ነው።
እነዚህ ሁለት ድርጅቶች በምርጫ 2007 ተካፍለው ነበር። ያኔ የድርጅቱ መሪ አቶ አበባው መሐሪና ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ነበሩ። ድርጅቶቹ ጠቅላላ ጉብዬ አድርገው አዲስ አመራር መርጠዋል። አቶ አበባው የጉባየዉን ዉሳኔ ተቀብለው ከሃላፊነታቸው በጸጋ ነው የቀቀኡ ሲሆን፣ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ግን ምርጫ ቦርድ ድረስ ሄዶ በመክሰስ፣ ጉብዬዉን ለ15 ቀናት እንዲራዘም በማድረግ፣ የጠቅላላ ጉብዬዉን ዉሳኔ ለመቀበል ፋደኛ አልሆኑም። አሁንም ከተወሰኑ አባላት ጋር በመሆኑ አዲሱን የሰማያዊ አመራር በ”ወያኔነት” ለመክሰስ እየሞከሩ ነው። ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት አንድ ቀን ወህኒ አድረው የማያውቁ ሲሆን፣ ለሁለት አመታ የታሰረዉን የሺዋስ አሰፋ፣ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ምክንያት ለወራት የታሰሩ የድርጅቱ የዉጭ ጉዳይ ሃላፊ አቶ አበባ አካሉ፣ የሴቶች ጉዳይ ሃላፊ ብሌን መስፍን፣ የድርጅቱ የምክር ቤት ሰብሳቢ ይድነቃቸው ከበደ የመሳስሉ በርካታ ለትግሉ ዋጋ የከፈሉ ታጋዮች ያሉበትን የሰማያዊ አመርር፣ እርሳቸውን አባላት ከሃላፊነት ስላስነሷቸው ብቻ “ወያኔዎች ናቸው” ብሎ ማስወራታቸው ብዙዎችን አስገርሟል።
እነዚህ ሁለት ድርጅቶች፣ ባደረጉት ጠቅላላ ጉባዬ፣ ምርጫ ቦርድ፣ በሕጉ መሰረት ተወካዮችን ልኮ፣ ኮረም መሙላቱን አረጋግጧል። ጉብዬውም የተደረገው በድርጅቶቹ ደንቡ መሰረት፣ አሰራሩ በመከተል መሆኑን አጣርቶ፣ በምርጫ ቦርድ በሕጉ መሰረት፣ ለአዲሱ አመራር እውቅና መስጠት ነበረበት። ሆኖም ግን ምርጫ ቦርድ ያንን ለማድረግ ፍቃደኛ ሳይሆን ለብዙ ወራት ቆይቷል። ድርጅቶቹ የተለያዩ ደብዳቤ ቢጽፉም፣ ምላሽ ለመስጠት ፋደኛ ሳይሆን፣ የተለያዩ ምክንያቶች እየሰጠ፣ ሲያጉላላቸው ቆይቷል።
ሆኖም ከብዙ የደብዳቤዎች መላላክ በኋላ ምርጫ ቦርድ ለመኢአድ እና ለሰማያዊ አዲስ አመራሮች እውቅና ሰጥቷል።
መኢአድ የፖለቲክ ፕሮግራም አሻሻያዎች አድርጎ የነበረ ሲሆን፣ ከአንድነት ፓርቲ ጋር ዉህደት ለመፈጸም በነበረበት ወቅት በጋራ ያጸደቁትን ፖሮግራም፣ ፕሮግራሙ አድርጎ ማጸደቁም ይታወሳል።
በተያያዘ ዜና መኢአድ እና ሰማያዊ አብረው ለመስራት እንደወሰኑ የደረሰን መረጃ ይጠቁማል። በመኢአድ እና በሰማያዊ አመራሮች መካከል ጠንካራ የሆነ መተሳሰር እንዳለ የተረዳን ሲሆን፣ ድርጅቶቹን በይፋ ግንባር ሊፈጠሩ እንደሚችሉ ለማወቅ ችለናል።የቀድሞ የአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ለዚህ ለሰማያዊ እና መኢአድ ስብስብ ድጋፍ እንደሚሰጡና ይሄንን ስብስብስ በመቀላቀል ጠንካራ፣ አገር አቀፍ፣ አማራጭ የሚሆን ኢትዮጵያዊ ሃይል ለመመስረት የሚቻልበት ሁኔታም ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል።
ከብዙ መጉላላት በኋላ ምርጫ ለሰማያዊ የተጻፋ የምርጫ ቦርድ ደብዳቤ

No comments:

Post a Comment