(ዘ-ሐበሻ) ሕወሓት መራሹ መንግስት ባስታጠቃቸው የሶማሊ ክልል ልዩ ኃይል እና በነፃነት ኃይሎች መካከል በምስራቅ ሐረርጌ ላለፉት 2 ቀናት ካለማቋረጥ እየተደረገ ባለው ውጊያ በጉርሱም ወረዳ በተደረገ ውጊያ አንድ የልዩ ኃይል አዛዥ መገደሉ ተሰማ::
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ እንደዘገበው ከሆነ የልዩ ኃይሉ አዛዡ በተጨማሪ በሕወሓት አጋዚ ከሚመራው ጦር በርካታ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል:: በተለይም ኢላለም ጥቃ በተባለው አካባቢ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት የሕወሓት አጋዚ ሠራዊት ኃይሉን በማጠናከር ማምሻውን በምስራቅ ሐረርጌ አካባቢ ባሉ 10 ከተሞች መሰማራቱ ተዘግቧል::
የሕወሓት ጀነራሎች የሚመሩትና በምስራቅ ሐረርጌ የሰፈረው የአጋዚ ጦር የሶማሊ ክልል ተወላጆችን በብዛኛው አስታጥቆ ያሰፈረ ሲሆን በሁለት ቀናት በፈጀው ውጊያ የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች እና የጉርሱም ወረዳ የሚኒሻ አባላት ከነጻነት ኃይሎች ጋር ተቀላቅለው ይህን የአጋዚ ሠራዊት ሊመክቱ ቢሞክሩም አጋዚዎቹ እንዳስጣሏቸው ኦኤምኤን ዘግቧል::
በምስራቅ ሐረርጌ ጉርሱም ያለው ውጥረት አሁንም እንዳየለ ይገኛል:
No comments:
Post a Comment