Monday, February 20, 2017

የወያኔዋ ኢትዮጵያ — የሞቱላት መቃብራቸው የሚፈነቀልባት፤ የገደሏት ግን ሀውልታቸው አገር የሚያጣብብባት ምድር



አቻምየለህ ታምሩ
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፫ኛ ፓትርያርክ ነበሩ። ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ተክለ ኃይማኖት በዘመናቸው የነበረው ወታደራዊ መንግስት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን አሳልፈው እንዲሰጡ በርካታ ውትወታና ጫና ቢያደረግባቸውም ለምንም አይነት ጫና ሳይንበረከኩ የተሰጣቸውን የቤተ ክርስትያን አደራ ተወጥተው አልፈዋል።
በመጨረሻም በኃይል ቤተ ክርስትያኗን በፖለቲካው ስር ለማድረግ ደርግ እርምጃ ሲጀምር የርሃብ አድማ በማድረግ፤ ገፍቶ ሲመጣም «ሬሳዬን ተራምዳችሁ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያንን ትደፍራላችሁ» በማለት ጸንተው በመቆም፤ ከአሥራ ሁለት ዓመታት የፓትርያሪክነት አገልግሎት በኋላ ግንቦት ፳፰ ቀን ፲፱፻፹ ዓ.ም. በተወለዱ በ፸ ዓመት ዕድሜያቸው መላ ዘመናቸውን በጸሎት፣ በጾም፣ በሰጊድ አሳልፈው፤ የሰውነታቸው ክብደት ፳፭ ኪሎ ግራም ደርሶ፤ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ጀግና ናቸው።
ብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ አቡነ ተክለ ኃይማኖት የወር ደመወዛቸውን ለህጻናት ማሳደጊያ የሚሰጡ፤ከጸሎት መጽሃፍ፣ ከአንድ የሚቀይሩት ወይባ፣ ከደረት ሰዓትና ከነጠላ ጫማቸው በስተቀር ሌላ ንብረት ያልነበራቸው፤ህይወታቸውን ለአገራቸው የሰጡ፤ሙሉ ጊዜያቸውን በጾምና በጸሎት የሚያሳልፉ መናኝ መነኩሴ ነበሩ። በዘመናት የተነሱ ኃይሎችን ተቋቁመው በመስዕዋት ያቆዩዋትን ቤተክርስቲያን አደራ ተቀብለው፤ለቤተ ክርስቲያናቸው የገቡትን ቃለ መሃላቸውን ጠብቀው ሳያስደፍሯት መስዕዋት ሆነዋል።
Image may contain: 1 person, standing, shoes, sunglasses, shorts and outdoor
ታዲያ ዛሬ የዚህ እውነተኛ አባት መቃብር በግፈኞቹ ተቆፍሮ አጽማቸው ሜዳ ተጥሏል። መስዕዋት የሆኑላት ቤተ ክርስቲያን ለመቃብር ያህል እንኳ ሁለት ክንድ መሬት ነፈገቻቸው።
ቤተ ክርስቲያኗን ያዋረዷት ወያኔዎቹ እነ አባ ገብረ መድህን ወይንም አቡነ ጳውሎስ በየ አደባባዩ ሀውልት ሲቆምላቸው፤ ቤተ ክርስቲያኗን ያስከበሩት አቡነ ተክለ ኃይማኖት ግን ለቤተ ክርስቲያን ፍቅር ሞተው ለመቃብር የሚሆናቸው መሬት እንኳን አላገኙም።
የሚገርመው ለመቃብር የሚሆን መሬት ሳያገኙ መስዕዋት የሆኑት የአቡነ ተክለ ኃይማኖት መቃብር የሚቆፈረው አንድም የመቃብሩን መሬት በሊዝ ለመቸብቸብና ለመድለብ ነው፤
አሊያም የባንዳ ልጆችንና አገርና ቤተ ክርስቲያን የሚያዋርዱትን ባለጊዜዎች ባለመሬት ለማድረግ ነው። ጻድቁ አቡነ ተክለ ኃይማኖት የሞቱላት የቤተ ክርስትያን ልጆች የት ናችሁ? «ቤተ ክርስትያን በማንም ስር አትሆንም» ብለው ስለ ቤተ ክርስትያን ክብር የሞትን ጽዋ ተቀብለው መስዕዋት የሆኑት አባታችሁ መቃብር ሲፈነቀል ዝም ብላችሁ ማየትን ከማን የተማራችሁ ነው? ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት በልባችሁ ወስጥ የሉም ማለት ነው? የበቁትና የህያዉ የብፁዕ ወ
ቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት ልጆች ነን ብላችሁ ታምኑ የለም? ህያውነት ምንድን ነው? የሞትን እርምጃ ያለፍራት መራመድን የፈራ እንዴት የህያው ልጅ ሊሆን ይችላል? እናንተ የምታወግዟቸው ዮዲት ጉዲትና ግራኝ አህመድ ወያኔ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት መቃብር ላይ ካደረገው በላይ ምን አደረጉ? አይናችሁ እያየ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት መቃብር በወያኔ ሲፈርስ ዮዲት ጉዲትና ግራኝ አህመድ ቤተ ክርስቲያንን አወደሙ ብላችሁ የማውገዝ ሞራሉ ይኖራችሁ ይሆን? እዚያ ቅዱስ አባት በለበሱት ስጋ ውስጥ ሁነው የዘሩት የተግባር ፍሬ በእውነተኛው አለም ውስጥ ሆነው ፍሬ አልባ ሆኖ ሲያቱት ምን ይሰማቸው ይሆን?
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም «መቀበር አልፈልግም፤ ሕይወቴን በሙሉ ተቀብሬ ኖሬአለሁ! ወይም በመቃብር ውስጥ ኖሬአለሁ፤ ድንጋይ እየተደራረበ ተጭኖብኝ አምላክ ድንጋዩን አፈር አድርጎ እያቀለለልኝ ሳልጨፈለቅ ቆይቻለሁ» በማለት «ኑዛዜ» በሚለው ግጥማቸው ከህይወት በኋላ ፍላጎታቸው እንዲህ ሲሉ የገለጹት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ኃይማኖት እጣ ታይቷቸው ይሆን?
Image may contain: 1 person
የሕይወት ጽዋዬ ጥንፍፍ ብሎ ሲያበቃ፤
ሲቀር ባዶውን፣ የቆየ ባዶ
ዕቃ፤
ሲበቃኝ፤ በቃህ ስባል፣
ትንፋሼ ሲቆም በትግል፣
ስሸነፍ ተሟጦ ኃይል፣
ሰው መሆኔ ቀርቶ፣– አስከሬን ስባል፣
እወቁልኝ ይህን ብቻ፣– የገባኝን ያህል
ሞክሬ ነበር ሰው ለመሆን፤
ሰውነት በከፋበት ዘመን፤
መሬት አልነበረኝም በሕይወቴ
መሬት አልፈልግም፤ አሁን በሞቴ
አቃጥሉልኝ ሬሣዬን፤
አመድ እስኪሆን፤
አዋሽ ውስጥ ጨምሩልኝ አመዴን፤
ከአዋሽ ይቀላቀል ከዘመዴ፤
ይቺን አትንፈጉኝ አደራ፣
አመዴ እንኳን እንዲኮራ።

No comments:

Post a Comment