Wednesday, February 15, 2017

በዳያስፖራው የተያዙ የባንክ አክሲዮኖች ለሽያጭ ቀረቡ

በዳያስፖራው የተያዙ የባንክ አክሲዮኖች ለሽያጭ ቀረቡ


(BBN News) በትውልደ ኢትዮጵያውያን የተያዙ የባንክ እና የኢንሹራንስ አክሲዮኖች ለሽያጭ መቅረባቸው ተገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የሌላ ሀገር ዜግነት ያላቸውን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሀገር ውስጥ የባንክ እና የኢንሹራንስ ገበያ ውስጥ ለማስወጣት ካቀደ ቆየት ብሎ ነበር፡፡ በዚህም መሰረት ሰሞኑን የዳያስፖራዎች የባንክ እና የኢንሹራንስ አክሲዮኖች ለሽያጭ ቀርበዋል፡፡

ከ350 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ንብረት በባንክ እና በኢንሹራንስ ገበያ ውስጥ ይዘው የቆዩት 700 የውጭ ዜግነት ያላቸው ትውልደ ኢትዮጵያውያን፣ አክሲዮኖቻቸውን ለኢትዮጵያውያን ለማስተላለፍ ጨረታ ወጥቶባቸዋል፡፡ በተለያዩ የግል ባንኮች ውስጥ ያላቸው አክሲዮኖች ለሽያጭ መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎቹ ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ሆኖም ጉዳዩ ለብሔራዊ ባንክ ሪፖርት ከተደረገ በኋላ የአክሲዮኖቹ ሽያጭ ውሳኔ ተላልፎበት ለሽያጭ እንዲቀርብ ተወስኗል፡፡
በኢትዮጵያ ህግ መሰረት ከፋይናንስ ተቋማት አክሲዮን መግዛት ለውጭ ዜጎች የተከለከለ መሆኑን ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ 34 የግል ባንኮች እና የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ሲኖሩ፣ ከነዚህም ውስጥ ከ140 ሺህ በላይ የሚሆኑ አክሲዮኖች የተያዙት የውጭ ሀገር ዜግነት ባላቸው ኢትዮጵያዊያን ነው፡፡ የውጭ ዜግነት ያላቸው ባለ አክሲዮኖች ድርሻም ከ350 እስከ 400 ሚሊየን ብር እንደሚገመት መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment