በገዥው ፓርቲ በኢህአዴግና በሃገር አቀፍ ተቃዋሚዎች ፓርቲዎች መካከል ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ድርድር ላይ ድርድሩ የሚካሄድበትን የሥነ ስርዓት አማራጭ ሃሳብ ስድስት ተቃዋሚዎች ፓርቲዎች ለመንግሥት ማስገባታቸውን አስታወቁ፡፡
ተቃዋሚዎቹ ከገዥው ፓርቲ ጋር የሚደረገውን ድርድር በጋራ እና በመስማማት እንዲያከናውኑም ለሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥሪ ቅርበዋልም ተብሏል፡፡
ድርድሮቹን እንደዚህ ቀደሞ ለሚዲያ ፍጆታ፣ ለጊዜ መግዣና ለማስመሰል ከማድረግ እንዲቆጠብም ፓርቲዎቹ መንግሥትን አሳሰቡ፡
የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፣ መላው ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (መኢዴፓ) ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢፕአፓ ) ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ ( ኢራፓ) በጋራ በሰጡት መግለጫ በጊጊው ፓርቲ እና በተለያዩ ተፎካካሪ ፓርቲዎች መካከል ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ድርድር የተሳካ እንዲሆን የተለያዩ አካላት ድርሻቸውን እንዲወጡ ለማሳሰብ እንደሆነ ከመግለጫው ርእስ መረዳት ይቻላል ተብሏል በዘገባው፡፡
ፓርቲዎቹ ባለፈው አንድ አመት ተቀስቅሷላ ባሉት የህዝብ አመጽ ያስተላለፈው መልእክት ስርዓቱ ከልክ ያለፈ አምባገነን ስርዓት እንደሆነ ነው ሲሉ በጋራ መግለጫቸው ተናግረዋልም ተብሏል፡፡
በዚህም ምክንያት ሀገሪቱ ከፍተኛ የህልውና ስጋት ውስጥ ወቅዳለች ብሏል መግለጫው፡፡
ይህ ከመሆኑ በፊት መንግስት በሩን ለድርድር ክፍት እንዲያደርግ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በተደጋጋሚ ሲያስሳቡ እንደነበር እና ገዢው ፓርቲ ጥር 10 ቀን 2009 ዓ.ም ለተቃዋሚዎች ያቀረበው ጥሪ የረፈደ ጥሪ ቢሆንም ፓርቲዎቹ ለድርድሩ ዝግጁ መሆኑን መግለጫው ያስረዳል፡፡
መግለጫውን ያነበቡት የመኢአድ ዋና ጸሃፊ አቶ አዳነ ጥላሁን ገዢው ፓርቲ ባቀረበው የድርድር ጥሪ መሰረት የድርድር ቅድመ ውይይት መደረጉን እና በውይይቱም ፓርቲዎ ተገናኝተን በነአራት ነጥቦች ላይ አማራጭ ሃሳቦች እንድናቀርብ ከስምምነት ላይ ደርሰናል ፡፡
በዚህ መሰረት በውይይቱ ላይ ከተሳሰፍነው ፓርቲዎች መካከል የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ፣ መላው ኢትዮጵያዊያን ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (መኢዴፓ) ፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢፕአፓ ) ሰማያዊ ፓርቲ እና የኢትዮጵያ ራእይ ፓርቲ ( ኢራፓ) በጋራ ተወያይተን እና ተስማምተን ድርድሩ የሚካሄድበትን የስነምግባር አማራጭ ሃሳብ ለመንግስት በጋራ እስገብተናል ብለዋል፡፡
ውይይቱ የተሳካ እንዲሆን መደረግ አለባቸው ያላቸውን ነጥቦች የደረደረ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ስድስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ብቻ ሳይሆኑ ሌሎች ፓርቲዎችም በድርድሩ ላይ በጋራ እንዲቆሙ የቀረበ ጥሪ ይገኝበታልም ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ድርድሩ ውጤታማ እንዲሆን መንግስት እንደ ከዚህ ቀደሙ ለሚድያ ፍጆታ ፣ ለግዜ መግዣ እና ለማስመሰል ከማድረግ ተቆጥቦ ከድርድሩ የሚገኘው ውጤት ሀገር እና ህዝብን እንደሚጠቅም አምኖ እንዲንቀሳቀስም ፓርቲዎቹ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከገዚው ፓርቲ ጋር ያልጠመጣጠነ ሃይል ኖሯችሁ የተሳካ ድርድር እንዴት ማድረግ ትችላላችሁ የሚል ጥያቄ የቀረበላቸው ፓርቲዎቹ በየመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት ፕሬዝደንት ዶክተር በዛብህ ደምሴ አማካኝነት በሰጡት ምላሽ መንግስት ከእኛ ጋር ለመደራደር የወሰነው የትግላችን ውጤት ነው ፣ መሳሪያ ባይኖረንም ህዝን አለን መንግስትም ይህን አውቆ ነው የሚደራደረው ፣ የህዝብ ተወካዮች ስለሆንን ነው መንግስት ከእኛ ጋር የሚደራደረው ሲሉ በዘገባው ተደምጠዋል፡፡
No comments:
Post a Comment