(ዘ-ሐበሻ) በየዓመቱ በሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያውያንን በአንድ መድረክ የሚያገናኘው የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል የዘንድሮው የ2017 በዓል በዋሽንግተን ስቴት ሲያትል እንዲደረግ ማምሻውን መወሰኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታወቁ::በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን ላለፉት ሳምንታት ለመጨረሻ ፉክክር የቀረቡትን ዳላስ እና ሲያትል ከተሞችን ለመለየት ከፍተኛ ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ያስታወቁት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ዛሬ በተደረገ ጠቅላላ ቴሌኮንፍረንስ በሙሉ ድምጽ የዘንድሮው የ2017 እግር ኳስ ውድድር ሲያትል እንዲደረግ መወሰኑን አስታውቀዋል::
እስካለፈው ሳምንት ድረስ ዳላስ እና ሲያትል አስራ አምስት እኩል ድምጾችን በማግኘት ሲፎካከሩ የነበረ ሲሆን ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው ስብስባ ግን ሁሉም ድምጾች ወደ ሲያትል እንደሄዱና የ2018 ኳስ ደግሞ በዳላስ እንዲደረግ መስማማታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጮች አስታውቀዋል::
ፌዴሬሽኑ ለ34ኛ ዓመት በ2017 ከጁላይ 2 እስከ 9, 2017 በሲያትል የሚያደርገው ቶርናመንት በጉጉት ይጠበቃል:: ይህ የስፖርት መድረክ በዓለም ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ላይ ያገናኛል::
ዘ-ሐበሻ ሲያትሎችን እንኳን ደስ ያላችሁ ትላለች
No comments:
Post a Comment