መጀመሪያ ደረጃ በሃገራችን የተነሳውን የሕዝብ ተቃውሞ የሚመራው የፖለቲካ ድርጅትም ይሁን የፖለቲካ ግለሰብ የለም፤ ሕዝብ የፖለቲካ ተጽእኖ የኢኮኖሚ ብዝበዛ ሰልችቶት በገዛ ኣገሩ የመኖርና የመስራት ሕልውና ስላጣ የበይ ተመልካች ኣልሆንም የማፊያ ቤተሰባዊ ቡድን ዘረኛ ኣገዛዝ በቃን ብሎ ራሱ እየመራ በመታገል ላይ ነው።ህዝብን እያታገሉ እየመሩ ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ይሁኑ ተቋማት የሉም ውይይቱ ታዲያ ማን የማን ወኪል ማንስ የማን ሞግዚት ሆኖ ነው ለንግግር የሚቀመጠው ???
በኣንድ በኩል ስለ ሰላምና ስለ ደህንነት ወቅታዊ ጉዳዮች እንወያይ የሚለው ሃሰተኛው የሕወሓት ኣገዛዝ በሌላ በኩል ንጹሃንን እየገደለና እያሰረ የሚገኘው ዘረኝነት የሚረጨው ኣገዛዝ የሕዝብን ትግል ለማኮላሸት ግድያ ስራው ባደረገ ኣገዛዝ ለውይይት የሚቀመጡ ታማኝ ተቃዋሚዎችን ከተጠያቂነት እንደማያመልጡ ማወቅ ኣለባቸው። በምን ኣይነት ውክልና ከማፊያው ኣገዛዝ ጋር ማንን ወክለው እንደሚወያዩ ተቃዋሚ ነን ባዮች ራሳቸውን ሊጠይቁ ይገባል፤ የሕዝብ ብሶት ታምቆ ሳይፈነዳ በፊት የሕዝብን ችግር ለመፍታት ያልተጉ ለምርጫ ማድመቂያ ብቻ የሚኖሩ ሆዳም ተቃዋሚዎች ከሕወሓት እኩል በሕዝብ ላይ እየደረሰ ላለው ግፍ ዋጋ ይከፍላሉ።
ሕወሓት በስልጣን እንዲቆይ ቡራኬ ለመስጠት ካልሆነ በስተቀል የሕዝብን ችግር የሚፈታ ኣንድም የተቃዋሚ ፓርቲ ማግኘት በከበደበት በዚህ ዘመን ላይ ሕዝብ የሚፈልገው ስር ነቀል የሆነ የስርዓት ለውጥ መሆኑን ደጋግመን ተናግረናል።እንናገራለንም።የሕወሓት ኣገዛዝ እስካልተወገደ እስካልተለወጠ ድረስ ለውጥ ይኖራል ብሎ የሚያስብ ፖለቲከኛ በሞራል የወደቀ ሆዳም ብቻ ነው።
No comments:
Post a Comment