Wednesday, September 14, 2016

የስርአቱን የገቢ ምንጭ በማንጠፍ እንዋጋው:: አስራትና በኩራት ስለትም ለገዳዮች መስጠት ይቁም


አስራትና በኩራት ስለትም ለገዳዮች መስጠት ይቁም ለቤ/ክ የሚሰጠው አስራትና በኩራት የስለት ከፍተኛ ገቢም ወደማን እንደሚገባ ያውቃሉ ??
ወደመንግስት ካዝና ገብቶ እኛኑ ለሚገድሉ አጋዚ-ፌደራል – ፖሊስ ደሞዝ አበልና እንክብካቤ እኛኑ ለመጨፍጨፍ ጥይት መግዣ ይውላል::
የተረፈው ስርአቱ ቆብ ቀሚስ አልብሶ በ17 ቱም የኦርቶዶክስ መምሪያ በደብር በሰበካ ጉባኤ ወዘተ ባሰማራቸው ነጣቂዎች ይዘረፋል ይበላል:: ከእንግዲህ ሌባ ስርአትን በገንዘብ በመደገፍ የራሳችንን መግደያ በገንዘብ አንደግፍም:: አስራትና በኩራት ስለትም መስጠት መጽሃፍ ቅዱሳዊ ቢሆንም ሃላፊነት ለጎደለው የቤ/ክ ካድሬ መስጠት ግን ግዴታ አይደለም:: በም ትኩ በገጠር ላሉ ቀሳውስትና ካህናት እንላክ:: በከተማ ላሉ ችግረኛና ረጂ ላጡ ምስኪኖች አረጋዊያን መጦሪያና ህጽናት ማሳደጊያ ድርጅቶች በስጦታ እናበርክት::

No comments:

Post a Comment