Sunday, September 25, 2016

ህውኃት የመስቀልን በዓል ለከሰረ የፖለቲካ ትርፍ ለማዋል አቅዷል።


ህውኃት የመስቀልን በዓል ለከሰረ የፖለቲካ ትርፍ ለማዋል አቅዷል።
በተለይም በአዲስ አበባ ቁጥራቸው እጅግ የበዙ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ እናቶች፣ ወጣቶችና አዛውንቶች ተመልምለው ከፍተኛ በጀት ተመድቦ በደህንነት መ/ቤቱ፤ በፌደራልና በአዲስ አበባ ፖሊስ ኃላፊወች በየክፍለ ከተማው ሚስጥር በሚመስል መልኩ ስልጠና ተሰጥቷቸዋል። በስልጠናው ሂደት እንደታወቀው፤ ሰላዮቹ ሁሉም ሲብል ለብሰው፣ ተመሳስለው፣ ተደራጅተውና ቀጠና ተከፋፍለው ከታጠቁ ኃይሎች ጋር ተቀናጅተው እንደሚሰሩ ተገልፁኣል። ሰላዮቹ ሁሉንም እንቅስቃሴ እንዲቀርፁና የመግባቢያም ኮድም እንደሚዘጋጅላቸውና ቀድሞ እንደሚሰጣቸው ተነግሯቸዋል።

ለስለላ ውለታቸውም ጠቀም ያለ ገንዘብ እንደሚከፈላቸውና ከበዓሉ ፍፃሜ በኃላም በተለያዩ ሆቴሎች ፓርቲ እንደሚዘጋጅላቸው ቃል የተገባላቸው ሲሆን፤ ለመልካም ስራችሁ ምስክር ወረቀት እንሰጣችሁኣለን በቀጣይም አብራችሁን ትሰራላችሁ በማለት የትግራይን ተወላጆች በብዛት በስለላ ስራ ለመመደብ ያላቸውን እቅድ አስታውቀዋል።

ህዝባዊ ወያኔ ኃርነት ትግራይ፤ ህዝበ ክርስቲያኑ ከጥንት ከጠዋት ጀምሮ ታሪካዊና ኃይማኖታዊ ስርዓተ ወጉን ተከትሎ በየአመቱን ሲያካሂድ የኖረውን ባህላዊና ኃይማኖታዊ ስነ-ስርዓት አፈፃፀሙ ላይ ጣልቃ ከመግባቱም በላይ በስርዓተ ባዕሉ ላይ ፈንጅ በማፈንዳት ጭምር የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሌላ የጥፋት ዕቅድ እንዳዘጋጀ ስለታወቀ ህዝቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ ያስፈልጋል።

No comments:

Post a Comment