ከተሳፈርኩበት መኪና ላይ ሆኜ የሜዳውን ጅረት የተዋቡ ተራሮችንና ኮረብቶችን እያየሁ በሐሳቤ ርቄ በምናቤ ወደ አገሬ ነጐድኩ ማን ይሆን ለምለሚቱ አገሬ ብሎ የዘፈነው። ወዲያው የሀገራችንን ውበት የተዘፈነለንትና የተቀኝንለትን ያህል እንደሚገባ ያላጣጥምነው ለምን ይሆን ብዬ ድንገት እራሴን ጠየኩ የምዕራቡ አገራት ተፈጥሮ በለገሳቻቸው ውበታቸው ውስጥ አንድች ታላቅ ምስጢር እንዳለ ያስታውቃል መቼም ስብዓዊ ፍጡርና ተፈጥሮ የሚታረቀው ሰላምና ዕውነት ፣ፍትህና በጎ ህሊና ሲዋሀዱ ነው። ይኸው በኢትዩጵያ እንደሚታየው ልጓም ያጣ አምባገነንነት በተንሰራፋበት፤ መንግስት ብሎ ራሱን የሚጠራው ወንበዴው የወያኔ ቡድን እና ህዝብ ተለያይተው ነፃነትና ሰላም የሚናፍቅበት አገር ላይ ውበትን ማየት ፈፅሞ አይታለምም። ተፈጥሮ ጠረንዋንና መአዛዋን የሚያሽትላት ፣ ውበትና ለዛዋን የሚያይላት ገፅታዋን የሚጋራላት ትሻለች ሰባዊ ፍጡራንን፣ህዝብን ትፈልጋለች።
የአንድ ሀገር ትልቁ ሀበት ህዝብ ነው ማለዳ በስላም ወጥቶ አምሽቶ ወደ ማደሪያው የሚገባ ወገን ነው ያኔ ሀገር ማለት ተፈጥሮ፤ተፈጥሮ ማለት አገር ይሆናል። ኑ ራሱ ወደ ሰማይ የሚያደርስ ግንብ እንስራ በምደርም ላይ ሳንበተን ስማችንን እናስጠራ ብለው እንዳሎት ባቢሎናዊያን ፈጣሪ ግንቡ እንዳይሰራ የፈለገው ከተማ እንዳያድግ ወይስ የሰው ሥልጣኔ እንዳይኖር እስቡ ይሆን የሚል ጥያቄ ሊጭርብን ይችላል ነገር ግን የፈጣሪ ሐሳብ ያ ኣይደለም እርሱ የተመለከተው ሰዎች የተነሱበትን ፍላጉት እና ክፉ ሀሳብ ነበር ።
ታዲያ ከባቢሎን ዘመን ሐሳቤን ወደ አገሬ መልስ አድርጌ አገሬ ያለውን የወንበዴውን አገዛዝ ሥርዓት ማሰብ ጀመርኩኝ ዛሬ በኑሮ ውድነት በቀን አንድ ግዜ እህልን መቅመስ ላቃተው በአይኑ ብቻ የሚያየው ህንፃ እንደ ባቢሎን ብትገነቡለት ለሱ አንዳች ረብ የለውም መንግስት በባቢሎናዊ አይነት ትምክቱ ተይዞ ካልሆነ በስተቀር ከህንፃው በለይ በርካታ የተራቡ አንጀቶች ያልሞሉ ጐተራዎች የደረቁ ጉሮሮዎች አገር እያላቸው እንደሌላቸው የበላይ ገዢ የሆነው ዘር የፈለገበት ቦታ እንደፈለገው ሲያገኝ ከዚያም አልፎ የውጭ ባለ ሀብቶች መሬቱን ሲቆራመቱት ከቀየው ሲያባርሩት የህዝብ ልብ እንደደማ እንኳን ወያኔ ዓለም ጠንቅቆ ያውቃል።
በኮንደሚንየም ስም ኑሮዬ ብሎ ከሚኑርበት ከቀኤው እያፈናቀላችሁ እና ከጣራው እየበተናችሁ ማደሪያ ሰጠነው ከምትሉት ማደሪያውን የቀማችሁትን መብለጡ ግልፅ ሆኖ ሳለ በየመገናኛው ብዙሀኑና በየአደባባይ ቤት ሰጠንህ እያላችሁ ታደርቈታላችሁ። የሰረቁት ሥጋ ያስይዛል መረቁ እንዲሉ እንደ በዓል ቅርጫ የሰፊውን ደሀ መሬት ለባዕድና ለራሳችሁ ስዎች ቸብችባችሁ የገነባችሁት የግል መኖሪያና ድርጅት እንዲሁም በየባንኩና በየኪሳችሁ በየውጭ አገር ባንኮች ያከማቻችሁት ገንዘብ ወትሮም ተስርቆ የተበላ ነውና ቀኑ ሲደርስ ተመልሶ ወደ ሰፌው ህዝብ መግባቱ አይቀሬ መሆኑን እየገጠማችሁ ያለው ህዝባዊ ትግል በዋቢነት ልታውቁት ይገባል።
ከብሔር እና ዘሬ ይልቅ ኢትዩጵያነቴን አበክረው የነገሩኝ ወላጆቼ አገር ዘሬን እንጂ ዘርሽ አገርሽን ይቀድማል ብለው ከቶም አላስተማሩኝም ። የአሁኖቹ ገዚዎች ለሌብነታቸው ይመች ዘንድ አባትሽ ኦሮሞ እናትሽ ደግሞ አማራ እያሎ ኢትዩጰያነቴን ሲያላግጡበት ማየቱ በእጅጉ ያሳዝናል። እንዲህ እንደ አሁኑ
ዘርን ቆጥሮ የአንድ ብሔር የበላይነት ሳይንሰራፋ ታግሎ ለስልጣን ያበቃው ኢትዬጵያዊ ነኝ ያለ ህዝብ እንጂ አንድ በሔር አልነበረም በመሆኑም ዛሬ እንዲህ ድምፁን ሊያስማ የውጣውን የአማራን የኦሮሞ ወጣት በየጕዳና እንዳበደ ውሻ በጥየት የምትቆሎት ለትግሎ መቀጣጠል ነዳጅ እንጅ ውሀ አለመሆ ልብ ልትሎትም ይገባል ። ከኛ በላይ ፎጨት አፍን ማሞጥሙጥ ነው እንዲሎ ወያኔ የዲሞክራሲ እድምታ ተንሸዋሮበት እኔ በቆፈርኩልህ ጉድጓድ ብቻ ሂድ እኔ በጠረኩልህ ጉዳና ንጎድ ይለናል ዜማውም የእኔ ፎጨቱም የኔ ጆሮውም የእኔ ነው ካለን ሰነበተ። ህዝቡ ምንን ይፈልጋል ምንንስ ይጠቃል ብሎ ከማለት ይልቅ የአምባ ገነን ጉዞ እንቅፋቶችን በጥይት አፈሙዝ መልቀሙን መርጧል ውጤቱ ምንኛ የከፋ መሆኑን ከማስተዋል ይልቅ መግደሉንም በእጅጉ ተያይዞታል ሩቅ እንኳን ሳንሄድ በዚሁ በ አህጉራችን አፍሪካ በ ክ/ዘመን መጨረሻና መጀመሪያ ላይ የነበሩት ህዝባዊ አመፆቹ የተከፈለባቸው ዋጋና የፈሰሰው ደም እጅግ አሳዛኝ ቢሆንም የነ ማሊን ሴራሊዪን ዲክሞክራትክ ኮንጎን የመንግስት ለውጥ ማየት የቅርብ አብነት ነው የተባ ጆሮና የሚያስተውል አይን ካለ እውነተኛ ትግል በቆሰቆሱት ቁጥር ይብሳልና የሰውን ላብን ጉርሶ የት ደርሶ እንዲሉ ይህ ሁሉ የክፋት ግንባችሁ በጠንካራው የህዝብ ኃይል እንደ ባቢሎን ግንብ የሚፈርስበት ግዜ እሩቅ አይሆንም። ትግሉን አሁን ካለበት ደረጃ ከፍ ማድረግ ከተቻለ፤ በአጭር ጊዜ ውስጥ አንድ ዕመርታ ማሳየት ይቻላል። ለዚህ ተግባራዊነት መሳካት ሁላችንም ሀገር ወዳድ ኢትዩጵያዊያን ወያኔን በመቃወም ባለንበት ስፍራ ሁሉ በሁሉም አቅጣጫ እንታገል !
ኢትዮጵያ በሕዝቧ ተከብራ ትኖራለች !!
No comments:
Post a Comment