Friday, September 9, 2016

አዲስ የተቋቋመዉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰራተኞችን የሚመድበዉ ዘር እየቆጠረ መሆኑ ተደረሰበት


Shenkut Ayele
አዲስ የተቋቋመዉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰራተኞችን የሚመድበዉ ዘር እየቆጠረ መሆኑ ተደረሰበት
———————————–
ቀደም ሲል በአራት ልዩ ልዩ መስሪያ ቤቶች ስር የነበረዉ የአቃቤ ህግ አወቃቀርን በአንድ አመጣለሁ በማለት በቅርቡ አዲስ የተቋቋመዉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ሰራተኞችን የሚመድበዉ ዘር እየቆጠረ መሆኑን ከስራ የተቀነሱ ባለሞያዎች በምሬት እየገለጹ ነዉ::
በፍትህ ሚኒስቴር: በጸረ-ሙስና : በግሙሩክ እንዲሁም በንግድና እንዱስትሪ መስሪያ ቤቶች ስር በተናጠል ይመራ የነበረዉ የአቃቤ ህግ ስራን በአንድ በማምጣት የተሻለ የአቃቤ ህግ ስራን በሀገሪቱ ለማስፈን ተዋቅሪያለሁ ሲል የተነሳዉ አዲሱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገና ከመነሻዉ በዘረኝነት እና በወንጀለኛ አሰራር ተተብትቧል::
ከአራቱ መስሪያ ቤቶች ይሰሩ የነበሩ አቃቤ ህግ ሰራተኞችን ብዙሃኑን አግልሎ ከአንድ አናሳ ጎሳ ብቻ ነጥሎ (የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ አባላትን ብቻ) የመዉሰድ ስራ እየተሰራ ነዉ::በተለይም አሁን በሀገሪቱ ከተነሳዉ የህዝባዊ ተቃዉሞ እና ተጋድሎ ጋር ተያይዞ የኦሮሞ እና የአማራ አቃቤ ህግ ባሌሞያዎችን አናምናቸዉም በማለት ቀጥተኛ የማንሳፈስ ስራ እየተሰራ መሆኑን በደሉ የደረሰባቸዉ ባለሞያዎች ገልጸዋል::
በህግ ጉዳይ: በስለላ ጉዳይ: በጸጥታ ጉዳይ: በወታደራዊ ጉዳይ: በዲፕሎማሲያዊ ጉዳይ በአጠቃልይ ቁልፍ በሆኑ የፖለቲካ አቅም ባላቸዉ ጉዳዮች ላይ ወያኔ 95 % የሚሆነዉን የኢትዮጵያ ማህበረሰብ አያምንም:: በመሆኑም በነዚህ ዘርፎች ላይ ዘር እየመረጠ ይመድባል:: ብዙሃኑን የማህበረሰብ አካላትን ያገላል::
ስለሆነም የጠቅላይ አቃቤ ህግ መቋቋምም ዋና አላማዉ ከብዙሃኑ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ የተገኘዉን የአቃቤ ህግ ባለሞያ ለማግለል እና የአቃቤ ህግ ስራዉን በአንድ አናሳ ጎሳ አባላት ብቻ (የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ አባላትን ብቻ) ለመሙላት እንደሆነ አሁን ግልጽ ሆኗል:: ልክ የኢትዮጵያ ቴሌኮሚኒኬሽንን በማፈራረስ የብዙሃኑን ኢትዮጵያዉያንን ማህበረሰብ ባገለለ መልኩ በአንድ አናሳ ጎሳ ብቻ በመሙላት በአዲስ መልክ እንዳዋቀሩት አሁን ደግሞ ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሚል አካሄድ የአቃቤ ህግ ዘርፉን በአንድ አናሳ ጎሳ ብቻ ለመቆጣጠር ወስነዋል::
ከዚያም በንጹሃን ኢትዮጵያዉያን ላይ ያለወንጀላቸዉ ወንጀለኛ እያሉ የሚከሱ ህሊናቢስ እና ወንጀለኛ አቃቤ ህግ ባለሞያዎች እንዳሰኛቸዉ ወንጀል ለመፈብረክ እና ያለ ነቃሽ ህዝቡን ሁሉ ለመወንጀል ይችላሉ ማለት ነዉ:: ይሄዉ ነዉ የወያኔ እጥር ምጥን ያለ የፖለቲካ ቁማር እና ወንጀል::

No comments:

Post a Comment