Saturday, September 3, 2016

ሕዝቡ በወያኔ ላይ ለምን ተነሳ ??


ሕዝቡ በወያኔ ላይ ለምን ተነሳ??
የስርአቱ አመራሮች የወጣቱን የጎልማሳውን የአዛውንቱን የሴቱን ብሶት አሳንሰው ለማቅረብ ይፈልጋሉ. የጥቂት የመንግስትን ስልጣን ለግል መጠቀሚያ ያዋሉ ባለስልጣኖች ችግር ያስመስሉታል. ይሁንና ችግሩ ስርአቱ አገሪቱን ለረጅም ግዜ መግዛት ይመቸው ዘንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነት ለመያዝ አስቦና ተዘጋጅቶ የሰራበት የረጅም ግዜ እቅድና ትግበራ ውጤት ነው. የጥቂት ትግራይ ኤሊቶች ጥቅም ይከበር ዘንድ የሌላው ኢትዮጵያዊ ጥቅም የተነካበት የጥቅም ግጭት ውጤት ነው.
1. ተቃዋሚን -ተችን – በጸረ- ሽብር/ጸረ ሙስና ህግ አጥምዶ መያዝ መብቱን የሚጠይቅ ዜጋን በማእከላዊና በደህንነት ቢሮዎች መደብደብ -ማሰቃየትና- መግደል
2. የህዝብ ድጋፍ ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ማዳከምና ማፈራረስ አመራሮቹንና ተሰሚነት ያላቸውን አስሮ ማሰቃየት -ማስረጃ ሲያጡ ከአመታት እስራት በሁዋላ በነጻ መልቀቅ
3. ህዝብ የሚያከብራቸውን አርቲስቶች በተቀነባበረና በሃሰተኛ ምስክሮች በተደገፈ ክስ ማሰርና ማሰቃየት/መደብደብ -ለምሳሌ ቴዲ አፍሮ -ፋሲል ደሞዝ
4. በንግድና በአስተዳደር የተዋጣላቸውን ተጽእኖ ፈጣሪ የሌላ ብሄር ሰዎች ከሃገር ማሰደድ-ታክስ አጭበርብረዋል ብሎ ማሰር-ንብረታቸውን መዝረፍ -መግደል. ለምሳሌ ብርሃነ መዋ/ስማቸው ከበደ(ኢንተርኮንቲኔንታል)- ዶ/ር ፍቅሩ(አዲስ ልብ ሆስፒታል)
5. በሌሎች ክልሎች ሳይቀር የአንድ ብሄር ሰዎች ብቻ በየመስሪያ ቤቱ ከፍተኛ የሃላፊነት ስፍራ መያዝ
6. ከፍተኛ ወታደራዊና ደህንነት ስልጣን በአንድ ብሄር ሰዎች ብቻ መያዝ -የአገሪቱ ጀነራሎች በሙሉ ከአንድ ብሄር የበቀሉ መሆን
7. ንግድ በመቆጣጠርና በህጋዊ ቀረጥ ከፍሎ የሚሰራውን ያለቀረጥ እቃ በማስገባት መጣልና ተስፋ ማስቆረጥ
8. እንደ መስፍን ኢንጂነሪንግ-አልመዳ ጨርቃጨርቅ-መሶቦ -ጉና አምባሰል መሳሰሉት የንግድ ድርጅቶች ተቀናቃኞቻቸውን እየደቆሱ የራሳቸው ኢምፓየር መስራት.
9. የሃላፊነት ቦታዎች ያለእውቀት በአንድ ብሄር ታማኝነት በመያዛቸው ለሁዋላ ቀር አሰራር ለመጉላላት ለሃብት ብክነት መዳረግ
10. የፋይናንስ ተቁዋማትን በመቆጣጠር የውጭ ምንዛሪን በማውጣት የመኪና -የኮንስትራክሽን ማሽኖችን -ኮምፑተር-መለዋወጫዎችን …ወዘተ ንግድ በመቆጣጠር መበልጸግ
11. በአምራች/በሆቴሎች/በአስመጭና ላኪ …ወዘተ የሚሰማሩ ባለሃብቶችን ሸር ካላስገባችሁን አትነግዱም በማለት ሰርቶ እንዳይበላ ማድረግ
12. አንድ ሰው በአእምሮ ለፈጠረው የምርምር ውጤት ፈቃድ የባለቤትነት መብት ሲጠይቅ ሳምፕሉን ተቀብሎ ለስርአቱ ደጋፊ በመስጠት እውነተኛውን ፈጣሪ ተቀድመሃል በማለት ማባረር
13. በስብሰባና በስልጠና ስም የታክስ ከፋዩን ገንዘብ ለፖለቲካ ትርፍ ለታማኞቻቸው በአበል ስም ማባከን
14. የከተማ ቦታዎችን የገጠር የእርሻ መሬቶችን በዘመድ አዝማድ በመቆጣጠርና ህንጻዎችንና ትልልቅ እርሻዎችን በመስራት ያለአግባብ መበልጸግ
15. የኮንዶሚኒየም ቤቶች ላይ ለስርአቱ ደጋፊዎች የተለየ እደላ -በመንግስትና ቀበሌ ቤቶች ላይ እነሱን መሰግሰግ
16. ለስርአቱ ደጋፊ ኮንትራክተሮችና አገልግሎት ሰጭዎች የመንግስት ስራን ያለጨረታ ወይም በተጭበረበረ ጨረታ ኮንትራት መስጠት
17. በአገራችን በያመቱ ብዙ ወጣቶች ተመርቀው እያለ ብዙ የስራ እድል ባለባቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አየር መንገድ/ቴሌ/ገቢዎች/ጉምሩክ የአንድ ብሄር ወጣቶች እየተመረጡ መቀጠር
18. በስፖርት በዋና /በብስክሌት/በኦሎምፒክ …ወዘተ ኮሚቴዎች ሳይቀር በማህበራዊ ተቁዋማት ስልጣንን በመያዝ ሁሉን የመቆጣጠር ስግብግብነት
እነዚህ ጉዳዮች ህዝቡን በአገሩ ላይ ሁለተኛ ዜጋ አድርጎ የሚያስቆጥር ብቻ ሳይሆን ተወልዶ ባደገበት ቀየ መጤ ሰው ሲያሰቃየውና የኢኮኖሚው ተጠቃሚ ሲሆን መመልከት አይወድም.

No comments:

Post a Comment