Thursday, September 22, 2016

አቶ ጁኔዲን ሳዶ ለመጀመሪያ ጊዜ ህወሓት ላይ ቦምብ ወረወረ።


Image result for junedin sado

አቶ ጁኔዲን ሳዶ ለመጀመሪያ ጊዜ ህወሓት ላይ ቦምብ ወረወረ።
“የኦሮሞ ህዝብ ይህ ስርዓት የኛ ስርዓት አይደለም እያለ ሲጮህ አሳምኜ እንዲቀበሉ ማድረጌ የኦሮሞን ህዝብ እጅና እግሩን አስሬ እሳት ውስጥ እንደጨመርኩ ይሰማኛል፣ ይህን በማድረጌ የኦሮሞን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ።
ኦህዴድ ስልጣን የለውም፣ የራሱ አጀንዳ የለውም፣ የኦህዴድ ፕሮግራም የተፃፈው በህወሓት ነው። የኦህዴድ ፕሮግራም የህወሓት ፕሮግራም ኦሮሚኛ ቅጂ/version ነው። የኦሮሞ ጥያቄ በኦህዴድ ሊፈታ አይችልም። ማስተር ፕላን የኦህዴድ አይደለም።
የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄ ራስን በራስ የማስተዳደር ነው። የኦሮሞ ጥያቄ የሀገር ባለቤትነት ጥያቄ ነው። የኦሮሞ ጥያቄ የነፃነት ጥያቄ ነው።
ግንዱን ትቶ ቅርንጫፎቹን ማራገፍ ፋይዳ የለውም። ችግሩ ያለው ግንዱ ላይ ነው። የህወሓት ስርዓት መወገድ አለበት።”

No comments:

Post a Comment