Tuesday, September 6, 2016

በኢትዮጵያ የተከሰተው የባንኮች ቀውስ እና በኦሮሚያ ክልል የሚደረገው የገበያ ማቆም አድማ በታቀደለት መልኩ ተጀምሯል።


በኢትዮጵያ የተከሰተው የባንኮች ቀውስ እና በኦሮሚያ ክልል የሚደረገው የገበያ ማቆም አድማ በታቀደለት መልኩ ተጀምሯል።
ከኦሮሞ ተቃውሞ ኣስተባባሪዎች በተደረገ ጥሪ መሰረት የገበያ ማቆም አድማ በመላው ኦሮሚያ ነገ ጷግሜ 1 እንደሚጀምር አስቀድመን መግለጸችን ይታወቃል።፡ ይህ አድማ እስከ መስከረም ሁለት ይቀጥላል። በዚህ ኣድማ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ክልሎች ለሽያጭ እቃዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ማስገባት ክልክል ነው።በጥሪው መሰረት እህልና ሸቀጣሸቀጦች ከኦሮሚያ ክልል ወደአዲስ አበባ እንዳይገቡ የተጀመረውን የገበያ ማቆም አድማ ለማሳካት በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች መንገዶችን በዚህ መልክ መዘጋጋት ተጀምሯል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ በበርካታ የደቡብና የኦሮሚያ ክልሎች ገንዘብ የለም የተባሉ ደምበኞች “ያስቀመጥነውን ገንዘባችንን እንፈልገዋለን፣ ለልጆቻችን ትምህርት ቤት ወጪና ለአዲሱ ዓመት ያስፈልገናል፣ ገንዘባችን ካልተሰጠን አንሄድም” ስላሉ በፖሊስ ድብደባ ደርሶባቸዋል።የባንኮች ቀውስ ወደ አዲስ አበባ እየተቃረበ ሲሆን፣ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ አበባ ዋና ባንኮች ነጋዴዎችና ባለሀብቶች ከወትሮ የበለጠ ገንዘባቸውን በቦርሳና ሻንጣዎች ስያወጡ ተስተውለዋል።ቀድሞ ከብሄራዊ ባንክ መረጃ የሚደርሳቸው የህዋሃት ባለስልጣኖች ገንዘባቸውን በገፍ እያሸሹ ነው። በነገው እለት እስከ መጪው አርብ በርካታ ባንኮች ሊጨናነቁ ይችላሉ። Read More 
Image may contain: text, outdoor and one or more people

No comments:

Post a Comment