Monday, September 5, 2016

ኤልፎራ በሽታ የተጠቁ ዶሮዎችን ለአዲስ ዓመት ገበያ ለያቀርብ ነው

ኤልፎራ በሽታ የተጠቁ ዶሮዎችን ለአዲስ ዓመት ገበያ ለያቀርብ ነው
No automatic alt text available.
ላምበረት በሚገኘው የሚድሮክ ኢትዮጵያ ኤልፎራ የዶሮ ተዋፅኦ ማምረቻ ውስጥ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ዘንድሮ ለአዲስ ዓመት ለገበያ ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ ሚቀርቡት ዶሮዎች መካከል ምርመራ የተደረገላቸው ከአንድ መቶ ሰባ በላይ በሳልሞኔላ ባክቴሪያ የተጠቁ ዶሮዎች ተገኝተዋል።
ይህ ባክቴሪያ ወደሰው ልጆች ተላልፎ ሳልሞኔሎሲስ የተሰኘ በሽታ የሚያሲዝ ሲሆን በበሽታው የተጠቃ ግለሰብ እስከ 7 ቀን የሚደርስ ከፍተኛ ትኩሳት እና ማስመለስ የሚያጋጥመው ሲሆን በሽታው ከሰው ወደሰው የሚተላለፍም ነው፤ በቶሎ ካልታወቀ በሽታው እስከሞት ያደርሳልም ተብሏል።
ይህ ባክቴሪያ ዶሮዎቹ ላይ መገኘቱ እየታወቀ ዶሮዎቹ ለገበያ ይቀርባሉ ተብለን ጉዳዩን የምናውቅ ሰዎች ተጨንቀናል ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ ያልፈጉ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

የመረጃ ምንጮቻችን አክለውም እናም እባክህ መልእክቱን ለኢትዮጵያ ህዝብ በማሳወቅ የኢትዮጵያን ህዝብ ከሳልሞኔሎሲስ እንታደገው ዘንድ በአጽንኦት ጠይቀዋል

No comments:

Post a Comment