Tuesday, September 20, 2016

በአዲስ አበባ የመምህራን እና የወያኔ ፍጥጫ እየተጋጋለ ነው።


 በአዲስ አበባ የተጀመረው የመምሕራን ስልጠና ተብሎ በወያኔ ባለስልጣናትና ካድሬዎች የተጀመረው ስብሰባ በመድረኩ መሪዎችና በመምህራት መሃከል የተጀመረው ዝምታ እየጠበበ በንትርክና በፍጥጫ እየተጋጋለ መምጣቱን ተሳታፊ መምሕራን ተናግረዋል።
Image may contain: 2 people , crowd and text
በኣዲስ ኣበባ ዩንቨርስቲ ዛሬ ጠዋት በነበረው ስብሰባ ዶ፨ር አብርሃ በተባለ ግለሰብ ዕአንድ የኢኮኖሚ እና የፓለቲካ ማህበረሰብ መመስረትዕ በሚል ርዕስ አሰልቺ በሆነ የአቀራረብ ዘዬ ፕረሰንታቲኦን በመቅረብ ሂደት ላይ ስለ ትምክህተኝነት እና ጠባብነት ዙሪያ ማጠንጠን ሲጀምር ተሰብሳቢ ምሑራን በጭብጨባ ገለፃውን እንዲያቆም ጠየቁ፣ አቅራቢው ልጨርስ እያለ ቢለማመንም ጭብጨባው በመቀጠሉ ሳይጨርስ ለማቆም ተገዷል፥፥ መድረኩን የሚመራው ካሣ ተ፨ብርሃን ዕገለፃው እየተጠናቀቀ ነበር፣ ቸኮላችው፣እንዲያው ዝም ብላችው ነው ዓመላችሁን ያወጣችሁትና ከእናንተ የማይጠበቅ ነገር የፈፀማችሁትዕ በማለት በመናገሩ ምሑራኑ በከፍተኛ ጭብጨባ ተቃውሞአቸውን ደግመዋል።
በኣዲስ ኣበባ በተለያዩ ኣደራሾች እየተካሄደ በሚገኘው ስልጣና\ስብሰባ ላይ በስፋት የኦሮሚያ እና የኣማራ ክልል ጉዳዮችን መነጋገሪያ መሆናቸውም ለወያኔ ሰዎች በፍጹም ሊመቻቸው ኣልቻለም። የሕዝብን ጥያቄ በሻእቢያና በውጪ ሃይላት ላይ ኣትላኩ በማለት በሰሜን ኣዲስ ኣበባ ባለ ኣንድ ኣደራሽ የተነሳው ጥያቄ ኣንድ ሁለት ሲባል እስከ ዘለፋ ኣድጎ የወያኔ ሰዎች ለድብድብ ሲጋበዙ ተስተውሏል።እንደተለመደው የወልቃይት ጥያቄ በክልሎች ስምምነት ይፈታል በሚል ሊያዘናጉ ቢፈልጉም ፌዴራሉ በክልሎች ጉዳይ ኣይገባም በሚል ሽፋን ቢደረግም ሕዝቡን እየገደለ ያለው ግን የፌዴራሉ ጦር ነው ሲሉ ተችተዋል፥የትግራይ ክልል ጠባቦች የማራ ክልል ትምክተኛ ባለስልጣናት ችግር እየፈተሩ ነው የሚል ሰበብ የሚፈጥረው ማእከላዊ መንግስት ነው የሚገደለው ግን ጥያቄዬን መልሱ የሚለው ሕዝብ ነው ምን ኣይነት በዽብና የተሞላ ኣስተዳደር ጉዳዩን እንደሚመራው ያሳያል በማለት ወንጀለኛው የክልሉ ባለስልጣናት ሳይሆኑ የፌዴራል መንግስት ሰዎች ናቸው ሲሉ መምህራኑ በቁጣ ገልጸዋል።
የኮንሶ ሕዝብን በተመለከተ የተነሳው ጥያቄ የወያኔ ሰዎች በኪራይ ሰብሳቢዎችና በጫካ የመሸጉ ኣንጃዎች ናቸው በሚል ሊሸፋፍኑ ቢሞክሩም ነገሩ ከሮ ክርክር ቢያስነሳም ኣይናቸውን በጨ ኣጥበው ሲከራከሩ ተስተውሏል። የሕዝብን ጥያቄ ለማድበስበስ የምታደርጉት ጥያቄ ዋጋ ያስከፍላቹሃል ሲሉ መምህራኑ ኣጥብቀው ተናግረዋል። የሚዲያዎችን ጉዳይ በተመለከተ የመንግስት ሚዲያዎች የሚያስተላልፉት ሁሉ የሃሰት ፕሮፓጋንዳና እጅግ ርካሽ ሲሆን በዚህ ላይ ሕዝቡ ምንም ኣይነት የፖለቲካ ጉዳዮች ኣማራጭ እንዳያገኝ ለተቃዋሚ ድርጅቶችና ለሲቪክ ማህበራት ዝግ ነው ለሃገሪቱ የሚጠቅሙ ምሁራን ጋዜጠኞች ጦማሪያን ይታሰራሉ ይገደላሉ ይሰደዳሉ ይህ ሁሉላ የመንግስት ስራ ሲሆን ሕዝብ እየተራበ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ ከተለያዩ ሃገራት ተቋሚዎች ይታፈናሉ የተለያዩ ኣፋኝ ሌክኖሎጂዎች ተገዝተው የሕዝብን መብት ለመርገጥ ይውላሉ ሲሉ በምሬት ተናግረዋል።
ወያኔ በማእከላዊ የሚፈጽመው ግፍ እና ሰቆቃ በመምህራኑ ተነስቶ ከፍተኛ የሆነ ጭቅጭቅ ፈጥሯል።በማእከላዊ የማሰቃያ ካምፕ ውስጥ መንግስት ከፍተና ወንጀል በዜጎች ላይ ይፈጽማል ያሉት መምህራን ታስረው የወጡትን ዜጎች አንድ በኣንድ ጠቅሰው ኣስቀምጠዋል። ስለ መምህራን የሙያ ፈቃድ ተነስቶ ወያኔ ላይ መምህራኑ ወርደዉበታል። የሙያ ፈቃድን በተመለከተ መምህሩን ለማታለልና ለማጨናነቅ ሆን ተብሎ የታቀደ የፖለቲካ ፊሽካ ሲሆን ወያኔ እኔ ኣውቅላቹዋለው የሚሉ ኣጉል ፈሊጥ በመምህራኑ ተቀባይነት እንዳሌለው ኣስረግጠው የተናገሩ ሲሆን ጠባብ ትምክህተኛ የሚለው የወያኔ ወንጀል የራሱ ስራ እንጂ የዜጎች ስራ ኣይደለም ሲሉ ገልጸዋል መምህራኑ።በኣንዳንድ ኣደራሾች መምህራን ሲሰላቹና ሲያንቀላፉ ተስተውሏል።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ስልጠናውን ለመካፈል ከመንግስት ት/ቤት የሄዱ መምህራን በቀን ለአበል 150 ብር ለሻይ ቡና ደግሞ 20 ብር፣ በድምሩ 170 ብር እየተከፈላቸው ስልጠናውን በመውሰድ ላይ ናቸው::የግል ት/ቤት መምህራን ስልጠናው ከሙያቸው ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ ከመሆኑም በላይ ለመንግስት ት/ቤቶች መምህራን የሚሰጠው የአበል ክፍያ የማይታሰብላቸው በመሆኑ ስልጠናውን አንካፈልም በማለት ጥለው ወጥተዋል ተብሏል፡፡ “ስልጠናው ባይኖርም ሥራ ላይ መሆናችሁ አይቀርም ነበር፡፡ ስለዚህም አበል ሊከፈላችሁ አይገባም” መባላቸውን የሚናገሩት መምህራኑ፤ ከሥራችን ጋር ፈፅሞ የማይገናኝ ስልጠና ለመውሰድ አዳራሽ ውስጥ ቁጭ ብለን ከምንውል መደበኛ ሥራችንን ብንጀምር ይሻለናል፡፡ ይህ ስልጠና ከመደበኛ ስራችን ውጪ በመሆኑ ተገቢውን የአበል ክፍያ ሊሰጠን ይገባል ብለዋል፡፡ በአንድ ህግና መንግስት በምትተዳደር አገር ላይ ሆነን አንድ አይነት ስልጠና ለመውሰድ እየተጠራን የግል ት/ቤት መምህራን በመሆናችሁ ስልጠናውን የምንሰጣችሁ ያለ አበል ክፍያ ነው መባሉ ህጋዊ ተግባር አይደለም” ሲሉም ተችተዋል፡፡
በስልጠናው ለመካፈል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ገልፀው ከስልጠናው አዳራሽ ከወጡት መምህራን መካከል ያነጋገርናቸው ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ መምህር፤ “የስልጠናው ዋንኛ አጀንዳ ሆኖ የቀረበው የፌደራሊዝም ጉዳይ ከመምህርነት ሙያ ጋር ፈፅሞ የማይገናኝና ለመምህራኑ አቅም ግንባታም ሆነ ክህሎት ማሣደጊያ አንዳችም ፋይዳ የሌለው ፖለቲካ ነው፡፡ ለአመታት በመምህራኑ ውስጥ ሲነሳ የቆየውን የፈቃድ አሰጣጥ ጉዳይ አጀንዳ አድርገው ያቀረቡትም ይህንኑ ፓለቲካዊ ይዘት ያለውን የፌደራሊዝም ጉዳይ ለመሸፈን እንዲረዳ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡ስልጠናውን ለመካፈል ከመንግስት ት/ቤት የሄዱ መምህራን በቀን ለአበል 150 ብር ለሻይ ቡና ደግሞ 20 ብር፣ በድምሩ 170 ብር እየተከፈላቸው ስልጠናውን በመውሰድ ላይ ሲሆኑ በከተማዋ የሚገኙ አብዛኛዎቹ የግል ት/ቤት መምህራን ስልጠናውን ለመካፈል ፍቃደኛ ሳይሆኑ በመቅረታቸው ተበትነዋል፡፡ መምህራኑ ይህንኑ ጥያቄአቸውን በተደጋጋሚ ቢያቀርቡም ምላሽ አለማግኘታቸውንና በትናንትናው ዕለትም ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረቡ መምህራን ስልጠናውን ባለመካፈል ውሳኔያቸው የፀኑ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡#

No comments:

Post a Comment