Wednesday, September 14, 2016

ለስር ነቀል ለውጥ ከአናቱ የገማው የሕወሓት ስርዓት ላይነሳ መመታት አለበት።


ለስር ነቀል ለውጥ ከአናቱ የገማው የሕወሓት ስርዓት ላይነሳ መመታት አለበት።
 ስርዓቱ የገማው ከአናቱ ነው:: አናቱ ካልተመታ አምባገነንና ሌባ መፈልፈሉን አያቆምም::አስገራሚው ነገራችን፤ ትላንት የተበላውን ዛሬ በቦታው የተቀመጠው ጠንቅቆ ለማስተዋል አለመቻሉ! “የማስጠንቀቂያውን ደወል” እንኳን ሳያይ፣ ያለፈውን መራገምና ራሱን መልዐክ ማድረግ፣ ነው ፈሊጡ፡፡ አልፎም ተፈጥሮዬ ነው እስከማለት ደርሶ ወንበሩን ሙጥኝ ማለቱ፡፡ቀጥሎም በራሱ ጊዜ “አወዳደቄን አሳምርልኝ!” ሳይል የቀደመው ባለስልጣን በወደቀበት መንገድ መንኮታኮቱ ነው፡፡ ስለ ምን አንዱ ካንዱ አይማርም? አካሄዱንስ ስለ ምን አይለውጥም? ኢ-ፍትሐዊነትን፣ ኢ-ዲሞክራሲያዊነትን፣ ሙስናን እንቋቋማለን ተብሎ በተነገረ ማግስት፣ እዚያው ጥፋት ውስጥ ተዘፍቆ መገኘት እጅግ አሳዛኝ ብቻ ሳይሆን እጅግ አናዳጅም ነው፡፡ለገዳይ ኣካላት ለኣሳሪው ክፍል ትእዛዝ የሚሰጡ የወያኔ ቱባ ሌቦች ኢትዮጵያ እንደ ሶሪያ እንዳትሆን ይሉናል ከፊታቸው ኣጣብቂኝ ሲይዛቸው መላወሻ ሲያጡ ኣንዴ ኢንተርሃሞይ ኣንዴ ሶሪያ በማለት ይቀባጥራሉ፤ ደርግም ሲንገዳገድ ስለ ላይቤሪያና ሶማሊያ ትርምስ ይሰብክ ነበር፤የኣምባገነኖች መጨረሻ እንግዲህ እንዲህ ነው።ያልተፈጠረና የማይፈጠር ዲስኩር ማሰማት መጮኽ።
“በልቼ ልሙት” የማለት ፈሊጥ፤ ተጠናውቶናል፡፡ የሸጥኩትን፣ የሸቀልኩትን በተለያየ ስም ያስቀመጥኩትን፣ ንብረትና ገንዘብ ብታሰርም እየበላሁ እኖራለሁ የሚለው አስተሳሰብ በሰፊው የተንሰራፋ ይመስላል፡፡ ገንዘብን በሺዎች መቁጠር ከቀረ ሰንብቷል፡፡የሕዝብ ጠላቶችን እና ሙሰኞችን ኣደራጅተው የሚመሩት የወያኔ ቱባ ሌቦች በዚህ ሰሞን ስለ ሙስና ስለ መልካም ኣስተዳደርና ስለ ሰብዓዊ መብት ጥሰት ስለ ሕዝብ ጠላቶች ስለ ሰላም ስለባለስልጣናት ብልግና ሊነግሩን ይፈልጋሉ ኣያፍሩም፣ነውር ኣያውቁም፤የዚህ ሁሉ ጉድና ችግር ፈጣሪ ሃገርን ያራቆቱት በኔትወርክ በመንደርተኝነትና በጥቅም የተደራጁት ራሳቸው ቱባዎቹ ባለስልጣናት ሆነው ሳለ እጃቸውን የሚቀስሩት ግን ራሳቸው በፈጠሯቸው ሰዎች ላይ መሆኑን የሞራላቸውን ዝቅጠት እንዲሁም ስለተጠያቂነትና ስለ ሃላፊነት ያላቸውን ግንዛቤ ባዶ መሆኑን ያመለክታል።
እርስ በርስ የመበላላት ባህል የተለመደ ነገር ሆኗል፡፡ ከታሪክ እስከ ዛሬ፡፡ ወይ በፖለቲካ ሽኩቻ፣ ወይ በኢኮኖሚ ድቀት አሳቻ፣ ወይ በባህል ልምሻ ዛቻ፣ ወይ በሶሻል ቀውስ ውድቀት አቻ፤ …አገር መበላላትን መቀበል ከጀመረችና ካመነች ቆይታለች፡፡ አያሌ የፖለቲካ ድርጅቶችን አይታለች፡፡በተለይ ስለመልካም አስተዳደር መበላሸት በሰፊው እየተወራ፣ እዚያው ብልሹነት ማጥ ውስጥ በፊት ለፊት ተውጠው የሚታዩ የበላይ ኃላፊዎች ለሀገርም ለህዝብም ጠንቅ መሆናቸው አያጠያይቅም፡፡ መነሳትም አለባቸው፡፡ ህዝብ በኃላፊነት በሰጣቸው ቦታ ላይ ነውና ምዝበራውን ያካሄዱት፣ በከፍተኛ ደረጃ ነው መጠየቅ ያለባቸው፡፡የመጀመሪያው የሰንሰለት (Network) ጉዳይ ሲሆን፤ ሁለተኛው አንቱ የተባሉ ሰዎች ተጠያቂ ያለመሆናቸው ጉዳይ ነው፡፡ስርዓቱ የገማው ከአናቱ ነው::አናቱ ካልተመታ አምባገነንና ሌባ መፈልፈሉን አያቆምም:: ስር ነቀል ለውጥ ያስፈልጋል የሁልግዜ መልእክት ነው። 
Image may contain: 13 people , text

No comments:

Post a Comment