Wednesday, September 7, 2016

የወረደ ፖለቲካ :- የሕሊና እስረኞች መፈታት ብስራት በቂሊንጦ በእሳትና በጥይት የተገደሉ እስረኞችን ግፍ ኣያካክሰውም። ሕዝብን ማታለል ክፉ እርግማን ነው::


የወረደ ፖለቲካ :- የሕሊና እስረኞች መፈታት ብስራት በቂሊንጦ በእሳትና በጥይት የተገደሉ እስረኞችን ግፍ ኣያካክሰውም። ሕዝብን ማታለል ክፉ እርግማን ነው:
 ወያኔ ያልገባው ነገር ቢኖር ኣሁንም ሕዝቡ ቀድሞ መሄዱን እና የፖለቲካ ሂሳቡ የተነቃበት የበላ እቁብ መሆኑን ነው፤ ዛሬም እንደ ድሮው ለመኖር የሚፈልገው ወያኔ እንደቀድሞው በተጭበረበረ ፖለቲካ ለመግዛት የሚታታረው ወያኔ የሰራው ግፍ የሚካካሰው ስልጣን ለቆ ሌላውን በከተተበት ጉድጓድ ሲገባ ነው። በኦሮሚያና በኣማራ ክልል የሰራው ግፍ እንዲሁም በኣደራ ከኣማራ ክልል የመጡ እስረኞችን በጥይት ለመፍጀት ሲል የለኮሰው የቂሊንጦው እሳት ተፈርዶባቸዋል የተባሉትን ሳይቀር ያጠቃ ጉዳይ ሲሆን ኣስከሬን ለመስጠት እንዲሁም ስም ዝርዝር ለመናገር ያልደፈረበት ምክንያቱ ኣደጋው ራሱን እንደ ጦስ ዶሮ እንደሚያሽቀነጥረው ያውቃል፤ ስርዓቱ መውደቁ ለማይቀር የሚሰራው ግፍ በርትቷል።
የሕሊና እስረኞች መፈታታቸው እሰየው ሲያሰኝ ባልሰሩት ወንጀል እንደታሰሩ በፈጠራ ክስ እንደተሰቃዩ ኣደባባይ የሚያውቀው ሃቅ ሆኖ ሳለ ወያኔ ራሱን እንደሆደ ሰፊ ማየቱ ምን ያህል ሞራለ ቢስ እንደሆነ ያሳያል፤ድሮም ሞራል የሌለው ወያኔ የካድሬዎችን ባዶ ጭንቅላት በተስፋ ሞልቶ ሞራላቸውን ለመገንባት የሚያደርገው ሩጫ ሽንፈት እየገጠመው ይገኛል።በኣለማችን በትልቁ የከሰረ ኣገዛዝ ቢኖር የሕወሓት ኣገዛዝ ነው።ሕዝብን ማታለል ክፉ እርግማን ነው በኣስቸኳይ የኣስከሬኖቹን ማንነት ይፋ ኣድርጋቹ ለቤተሰቦቻቸው ኣስረክቡ ከዛም ስልጣን ልቀቁ ዋናው ጥያቄ ነው።ለተፈቱ እስረኞች እና ቤተሰቦቻቸው መልካሙን ደስታ እና የትግል ዘመን እመኛለሁ:: ሞት ለወያኔና ኣሾክሻኪዎቹ !!! 
Image may contain: text

No comments:

Post a Comment