Thursday, September 1, 2016

ህወሀት ለእኔ እና ለአባቴ ቤት ዘላለማዊ ጠላት ናት

ወያኔ በ1982 ወልቃይትን ወረረ ፣ አመፅ ሊያስነሱ ይችላሉ ብሎ ያሰባቸውን ወጣቶች ወደ ትግራይ ባዶ ባዶ ስድስት ወደተሰኘው እስር ቤት ወረወራቻው እና አንድም ቀን ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ በሞት ቀጣቸው / አንዳንዶች በፀሀይ ብርሀን ማጣት አይነስውር ሆነው ከየት እና እንዴት መጣችሁ የሚላቸው ሳይኖር ትግራይ ጎዳናወች ለማኝ ሆነው ቀሩ / የተቀሩትን በግፍ እየገደለ ቀበራቸው ይህን ለማረጋገጥ አዲግራት ከአይነስውር ለማኞችን አንዱን መጠየቅ ይቻላል ።
ታሪክ አዋቂ የተባሉትን አዘውንቶች እየሰበሰቡ በጠላ ውስጥ በሚጨመር መርዝ በከላቸው አንዳንዶቹንም ተኩሶ ገደላቸው / የታማኝ በየነን የአውስትራሊያ ወልቃይት ቅሪቶችን ቃለ መጠይቅ ማዳመጥ ይቻላል /
ሴቶችን በግፍ እና ኢሰባዊነት በተሞላ ሁኔታ የማያውቁት የትግሬ ወንድ በወታደራዊ መኪና እየመጣ ሁሉንም ተራ በተራ ያስረግዟቸው ነበር / በቀላሉ አብዛኛውን ከ25 አመት በታች እድሜ ላይ ያለን የወልቃይት ተወላጅ ጠይቁ አባቱ ትግሬ ነው /የሚገርመው ዛሬ ግን ጠላት ሁኗቸው ተሰለፈ /
ያኔ እድሜየ 6 አመት ገደማ ነበር……..ብዙ የማላስታውሰው እና አባቴ ሲነግረኝ በደንብ ያልተረዳሁት ብዙ ነገር አለ ፡ እሱም እንዳልፈራ ሁሉንም አይነግረኝም ።
እንዲያ በግፍ ስንጠፋ እና ስንጨፈጨፍ ድረሱልን የምንልበት ምንም ነገር አልነበረም ስለዚህ ሞትን ዝም ብለን ሞትናት ።
ህወሀት ለእኔ እና ለአባቴ ቤት ዘላለማዊ ጠላት ናት ፤ መላ የኢትዮጵያ ህዝብ ብሎም መላ የአማራ ህዝብ ከህወሀት ጋር ቢታረቅ እንኳ እኔ በግሌ ሳልታልረቃት እቀራለሁ ።
~~~~የሰሜን ኮከብ~~~~

No comments:

Post a Comment