የጎንደርና ጎጃም ህዝብ ሕልውና አደጋ ላይ ነው – # ግርማ_ካሳ
ሕወሃቶች በአማራዉ ክልል መብራት አጥፍተው ከፍተኛ የሆነ የዘር ማጽዳት ወንጀል እየፈጸሙ ነው። በብዙ ሺሆች የሚቆጠሩ ወጣቶችን የፍርድ ቤት ሆነ የፖሊስ ማዘዣ ሳይዙ፣ ቤት እየገነደሱ፣ ከፍተኛ የጭካኔ ተግባራትን እየፈጸሙ ነው። ከአካባቢው የምንሰማው ሁሉ በጣም ልብ የሚሰበርና የሚሰቀጥጥ ነው።
ደብረጽዩን በአማራው ክልል መሳሪያ ማስፈታታ አለብን ማለቱ ይታወሳል። መሳሪያዎችን ብዙ ገንዘብ በመስጠት ለመሰብሰብ የተደረገው ሙከራ ስላልተሳካላቸው ፣ አሁን በሃይል ከገበሬው መሳሪያ ለመንጠቅ እየተንቀሳቅሱ ነው።
ሰዎቹ የሕዝብን ጥያቄ አክብሮ ለብሄራዊ እርቅ ከመዘጋጅት ይልቅ በጎንደር እና በጎጃም ህዝብ ላይ በበቀል የተነሱ ነው የሚመስለው። አመጸብን ያሉትን ይህን ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ፣ ከዚህ በኋላ ለአምሳ አመት እንዳያንሰራራ፣ አይቀጤ ቅጣት ለመቅጣት መወሰናቸውን ነው ድርጊቶቻቸው የሚያመለክቱት። ሕዝቡን ቢያከብሩ ኖሮማ የሕዝቡ ልጆች እያፈኑ አይወስዱም ነበር። ሰላማዊ ዜጎችን በጭካኔ አይደበድቡም ነበር።
እንግዲህ ወገኖች፣
ወያኔዎች ለጥፋት ይሄን ያህል ሲተጉ ፣ እኛ ግን ለምን እንዘናጋለን። ይህ ትልቅ ስህተት ነው። እያንዳንዳችን በአዲስ መንፈስ፣ በአዲስ ጉልበት በዚህ አዲስ አመት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የግፍ አገዛዝን ለማስቆም መስራት አለብን።
በጎጃምና በጎንደር ያለው ማህበረሰብ ፣ የነብርን ጭራ ከያዙ መልቀቅ አይገባም እንደሚባለው፣ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ትሥሥሩን ማጠናከር አለበት። የተሳሰረ ሕዝብ አይፈታም። አይሸነፍም። በየቀበሌው፣ በየወረዳው ራሱን በጎበዝ አለቃ እያደራጀ፣ አካባቢዉን መጠበቅ አለበት።
በወሎና በሰሜን ሸዋ የምንኖር፣ የጎንደር እና የጎጃም ወገኖቻችምም ማገዝ ይኖርብናል። ሰብረን መዉጣት መቻል አለብን። ከጎጃምና ከጎንደር ሕዝብ ጋር በመሆን የወያኔዎች የጥፋት ተልኮን የማስቆሙን ትግል መቀላቀል አለብን።
በወሎና በሰሜን ሸዋ የምንኖር፣ የጎንደር እና የጎጃም ወገኖቻችምም ማገዝ ይኖርብናል። ሰብረን መዉጣት መቻል አለብን። ከጎጃምና ከጎንደር ሕዝብ ጋር በመሆን የወያኔዎች የጥፋት ተልኮን የማስቆሙን ትግል መቀላቀል አለብን።
ይሄ የቅንጦት፣ ጉዳይ አይደለም። ይሄ የዲሞክራሲም ጉዳይ አይደለም። ይሄ የሕልዉና ጉዳይ ነው !!!!!!!!!!!!! ሰዎቹ (ሕወሃቶች) በተለይም በአማራው ክልል ሕዝብ ላይ ከድሮም ከፍተኛ ጥላቻ ነው ያላቸው። ለምን እንደሆን አላውቅም።
No comments:
Post a Comment