Tuesday, September 6, 2016

የኦሮሚያ ክልል ውሎ እና የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ ስኬት


የኦሮሚያ ክልል ውሎ እና የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ ስኬት
Minilik Salsawi's photo.
 በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ::ለኣንድ ሳምንት በኦሮሚያ ክልል የተጠራው የግብይት ማቆም ኣድማ በሻሸመኔ ኣዲስ ኣበባ ቡራዩ በኣምቦ በነቀምት በደንቢዶሎ በባሌ ጎባ በሃረርጌ ደደር ጋራሙለታ በኣወዳይ በድሬዳዋ እና በኣብዛኛው የኦሮሚያ ክልሎች በተሳካ ሁኔታ ሲካሄድ የምስራቅ ኢትዮጵያዋ ጅጅጋ እና በጫት ተቀባይነቷ የምትታወቀው ጅቡቲ ጫት ሳይላክ መቅረቱ ሲታወቅ ድሬዳዋም ጭር ብላ ውላለች ::
በተልይ የትራንስፖርት ኣገልግሎት የሚሰጡ ኣውቶብሶች መናሕሪያዎችን ጭር ያደረጉ ሲሆን ትራፊኮች ታርጋ በመፍታት ሲወስዱ ተስተውለዋል። ከዚህም በተጨማሪ የሕወሓት ንብረት የሆነው ሰላም ባስ ጨምሮ የተለያዩ በስራ ላይ ለመሰማራት ሲያሽከረክሩ የተገኙ አውቶብሶች እርምጃ የተወሰደባቸው ሲሆን መንገዶች በተለያዩ ኣከባቢዎች ተዘግተው መውጫና መግቢያ ኣልነበረም፥ የግብይት ማቆም ኣድማው ለሚቀጥሉት ቀናት እንደሚካሄድ ይታወቃል::
Minilik Salsawi's photo.
ስለዚህ በዚህ ኣድማ ጊዜ ውስጥ ከሌሎች ክልሎች ለሽያጭ እቃዎችን ወደ አዲስ አበባ እና ሌሎች የኦሮሚያ ከተሞች ማስገባት ክልክል ነው። እቃዎችን ጭነው በሚገቡ ተሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድም አቀናጆች አስታውቀዋል። የመኪና ባለንብረቶች፣ አሽከርካሪዎች እና ነጋዴዎች ይህንኑ አውቀው ይህን የአድማ ወቅት በማክበር ለህዝብ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ እና ንብረታቸውንም ከውድመት እንዲያድኑ ደግመን እናሳስባለን። #ምንሊክሳልሳዊ
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.
ሻሸመኔ
ሻሸመኔ
No Kchat in Jijiga City

No comments:

Post a Comment