በመሬት ቅርሚያና በኢኮኖሚ ብዝበዛ ላይ የተሰማሩ የውጪ ድርጅቶች በባህርዳር ሕዝብ ከባድ ተቃውሞ ገጠማቸው
በኢትዮጵያ የተስፋፋውን የሕዝቦች የመብትና ነጻነት ንቅናቄ ተከትሎ በሰሜን ኢትዮጵያ ኣማራ ክልል የሚገኘውና በኢንቨስትመት ስም ከደሃው ገበሬ ተነጥቀው ለውጪ ባለሃብቶች በተሰጡ መሬቶች ላይ በተለያዩ ኣገራት ካምፓኒዎች የሚመራው የኣበባ ኣምራች ኩባንያ የወያኔን ኣገዛዝ በሚቃወሙ ሕዝቦች ተቃውሞ እንደደረሰበት ታወቀ።
በሃገሪቱ በሚካሄደው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ኢኮኖሚያዊ ብዝበዛ የተቆጡ የባህር ዳር እና የኣከባቢው ነዋሪዎች ከባህርዳር በስተደቡብ ፩፫ ኪሎሜትር ላይ የሚገኘውን የኣበባ ካምፓኒ በመውረር በገዛ መሬታቸው እነሱ በድህነት ሲኖሩ የውጪ ባለሃብቶች የኢኮኖሚ ብዝበዛ ማካሄዳቸውን በመናገር ካምፓኒው ክልሉን ለቆ እንዲወጣ ማድረጋቸው ታውቃል። ሕዝቡ ኩባንያውን ሲወር ወታደሮችና ፖሊሶችን ሲተባበሩ እንደነበር የኣይን እማኞች ተናግረዋል።ይህ ተቃውሞ ለሶስት ቀን ያህል ቀጥሎ በኣከባቢው የሚገኙ የተለያዩ ኣገራት እስራኤል ጥሊያን ሕንድና ቤልጄም ካምፓኒዎች ለቀው እንዲወጡ መደረጉን ታውቃል ሕዝቡ በመቆጣቱ የመጣ በውጪ ካምፓኒዎች እየተደረገ ያለው የኢኮኖሚ ብዝበዛ እና በገዛ ኣገሩ ሳይሰራ የበይ ተመልካች መሆኑ ለዚህ ችግር መንስኤ ነው።
No comments:
Post a Comment