Friday, September 2, 2016

ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለአስቸኳይ ስብሰባ ፓርላማዉን ጠሩ


ሃይለማሪያም ደሳለኝ ለአስቸኳይ ስብሰባ ፓርላማዉን ጠሩ
ከትላንትና ወዲያ በአማራው ክልል ህዝብ ላይ ምሀረት የሌለው እርምጃ እንዲወስድ “ትእዛዝ ሰጥቻለሁ” ያሉት አቶ ሃይለማሪያም በጥቅምት ፓርላማው ሲሰበሰብ አንዳንድ ለውጦችን እንደሚያቀርቡ መናገራቸው ይታወሳል።
ሆኖም እርሳቸው ያንን ባለ በሁለት ቀናት ዉስጥ አገሪቷ ወደ ከፍተኛ ቀዉስ ውስጥ ተሸጋገረች። ወደ ጎንደር እና ጎጃም የተሰማራው ከፍተኛ የወታደር ስምሪት በመቄት ወሎና እና ጋይንት ጎንደር መስመር ላይ በሕዝብ ታገደ። በደሴ አድርጎ፣ መርጦ ለማሪያም ከዚያ ግንደወይን ለማለፍ የታሰበው አልተቻለም። ወታደሮች በአይሮፕላን ወደ ባህር ዳር መዉሰድ ብችኛ አማራጭ ሆነ። እንደዚያም ሆኖ ግን የሕዝቡ ተቃዉሞ አልበረደም።
እንደዉም ከጥቂት ቀናት በኋላ በደሴና በኮምቦልቻም የሥራ ማቆም አድማ ተጠርቷል። እነ ገነት ዘዉዴ ወደ 5000 የብአዴን አባላት በደሴ የመምህራ ኮሌጅ ሰብሰበው ከ3500 በላይ ብአዴኖች ስብሰባው ረግጠው ወጥተዋል።
አክራሪ ህወሃቶችም እንደጠበቁት ስላልሄደላቸው ወደ ማፈግፈጉ ላይ ሳይሆኑ እንዳልቀረ ነው። ከትላንት ወዲያ የጦርነት አዋጅ ነጋሪት ሕወሃቶች ሲያሰሙ ፣ “በመከላከያ ወይም ፖሊስ ሃይል የሚፈታ ነገር የለም፤ ህዝቡን ማዳመጥ ያስፈለጋል” የሚሉትን አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አስረው እንደነበረ አንዳንድ ዘገባዎች ወጥተው ነበር። ሆኖም ግን በአንድ ቀን ዉስጥ ታሪክ ተቀይሮ አቶ ገዱ ሽማግሌዎች እንዲያናገሩና ነገሮች ለማረጋጋት እንዲሞክሩ ለማድረግ የተሞከረበት ሁኔታ ነው ያለው። የአማራው ክልል የኮሚኒኬሽን ክልፍ ሃላፊው፣ አቶ ንግሱም፣ ለአሜሪካ ድምጽ፣ ብአዴን ህዝቡን ለማረጋጋት እየሞከረ እንደሆነ ነው የገለጹት። (አቶ ሃይለማሪያም እና ሕወሃት ያደፈረሱት ብአዴን ለማጥራት እየሞከረ ማለት ነው)
አቶ ሃይለማርያም ፓርላማዉን ለምን እንደጠሩ ማወቅ አይቻልን።ከአገዛዙ አባላት ቅርበት ያለው አፍቃሪ ሕወሃት ጦማሪ ዳንኤል ብርሃኔ ” a legislation to implement Oromia’s especial interest on Addis Ababa will be issued by by the parliament in October.” እንዳለው ግን በሕወሃቶች ዘንድ፣ የኦሮሞ ተቃዉሞ አስነስቷቸው ለነበሩ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠትና ኦሮሞዉን በማቀፍም በኦሮሚያ ያለውን እንቅስቃሴ ለዘለቄታ ለማርገብ አስበው ሊሆን እንደሚችል አንዳንድ ተንታኞች ይናገራሉ።

No comments:

Post a Comment