Thursday, September 1, 2016

የትግራይ ጸረ – ሕወሓት ነን ባይ ኣክቲቭስቶች ፡ የለውጥ ሃይሉን የተላመዱ እባቦች


የትግራይ ጸረ – ሕወሓት ነን ባይ ኣክቲቭስቶች ፡ የለውጥ ሃይሉን የተላመዱ እባቦች
 ጥሩ እንዳለ ሁሉ መጥፎ ኣለ መጥፎ እንዳለ ሁሉ ጥሩ ኣለ ይህ ኣባባል ግን በትግራይ ውስጥ የሚሰራ አይመስልም፤ ጸረ ሕወሓት ኣቋም ኣለን የሚሉን ኣክቲቭስት ነን ባዮች ሁሉ የህዝብን ንቅናቄ ተከትለው ሚናቸውን የለዩ ሲሆን ከእስር እስከመፈታትም ደርሰዋል፤ከእስርም የተፈቱት የሕዝቡን ንቅናቄ ኣደፍርሰው ለመከፋፈል እስከሚያስመስልባቸው ድረስ እጅግ ኣደገኛ ዘረኝነትን በመርጨት ወደ ለየለት የሕወሓት ደጋፊነት በማዝመም ሚናቸውን ለሚሽቆጠቆጥላቸው ሁሉ ማፈሪያ ሆነው እያየናቸው ነው።
ከኣሁን ቀደም ሕወሓት የለውጥ ሃይሉን ትኩሳት ለመለካትና ሰብስቦ ለመውቀጥ ያስቀመጣቸው የኣገዛዙ የደህንነት ቢሮ መጣቀሚያ ናቸው በማለት ስንናገር ጭራሽ እናኑ ወያኔዎች የወያኔ ተላላኪዎች ተባልን ጫናውን ስናበረታው እስር ቤት ከተቱላቹ ይሕው በማለት ሲላዘን ኣብረው እስር ቤት የገቡት እንደሃብታሙ ኣያሌው የመሳሰሉት ለከፍተኛ ኣደጋና ሕመም ቶርች እና የስነ ልቦና ቀውስ ተዳርገው ሲወጡ የትግራይ ኣክቲቭስቶች ግን ኣንድም ዱላ ሳይነካቸው ኣምሮባቸው ወጡ ይህ የተደረገው በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነታቸው እንዲጎላና ሲለቀቁ በሚሰጣቸው ተልእኮ የለውጥ ሃይሉን እንዲከፋፍሉ ስከትን ለመጎናጸፍ ነው፤እንደታሰበውን ያንቆለጳጰሷቸው እስኪያፍሩ ድረስ በተለያዩ ትፋቶች ብሄሮችን ለመጋጨትና ለማናከስ እየተራወጡ ይገኛሉ።
የኦሮሞ ሕዝብና እና የኣማራ ሕዝብ በሕወሓት ወታደሮች ሲገደል ዝምታን የለበሱት የሕወሓት የኣረናና የትግራይ ተወላጆች የኦሮሞና የኣማራ ሕዝብ ተባብሮ ኣገዛዙን ልመጣል ሲነሳ የበሉበትን የሕወሓት ወጪት ላለመስበት ሲታገሉ የሕዝቦች የትግል ኣንድነት ሲቃወሙ ቁሳዊ እና የንዋይ ፍቅራቸውን የዘረኝነት ታርጋቸውን ለጥፈው ሊነዱብን ሞከሩ፤ይህም ኣልበቃ ሲላቸው ያልተጻፈ ታሪክ በማንበብ ሕዝቦችን ለማበጣበጥ ኣንዱን ተገን ኣድርጎ ኣንዱን ለመምታት በመቧጠጥ ላይ ሲሆኑ እሱም ኣልሳካ ሲላቸው ያልተነካውን የትግራይ ሕዝብ እንደተነካ ኣድርገው መሳል ጀመሩ የሚያፈቅሩት ኣገዛዝ የፖሊስ ኮሚሽነር ብሄርን ለይቶ ጥቃት ኣልተፈጸመም ሲል ሲናገር እነሱ ግን ስለሌሎች ኢትዮጵያውያን መሞት ሳያሳስባቸው የዘርኝነት ዲስኩራቸውን በመርጨት ላይ ይገኛሉ፤ በኦሮሚያ ሺዎች ሲገደሉ የት ነበሩ
በኣውሮፓ እና ኣሜሪካ የሚኖሩ ተጋሩ ነን ባዮች ኣንድም ቀን ሕወሓት ሲገድል ያላወገዙ በሺዎች የሚቆተሩ ሕዝቦች ሲረሸኑ ነጻ እርምጃ ሲገደልባቸው ይቁም ያላሉ ኣንድ ሰላም ባስ ቢመታ ያዙ ልቀቁኝ በማለት በየሰዉ ሃገር በየስብሰባቸው ሲደነፉ ከረሙ፤ በተለያዩ አረብ ሃገራት ኢትዮጵያውያን ሲሞቱ ሲሰቃዩ እንደ ወገን አንድም ቀን ድምጻቸውን ሳያሰሙ ለቁሳቀስ ግን በግንባር ቀደምትነት ሲያላዝኑ እያየን ሲሆን ነገን ዋጋ ሊያስከፍላቸው እንደሚችል ግን ዛረ ላይ ቆመው ማሰብ ተስኗቸዋል፤እንዲሁም ሕዝቡ ለትግራይ ተወላጆች ያለው ኣመኔታ መውረዱና የትግራይ ተወላጆች በጥላቻና በዘረኝነት የተሞሉ እንደሆኑ ራሱን ከሚታዘበው ከሚያየው አንጻር እያሳመነ መሆኑን ተጋሩዎች ዘንግተውታል።
ኣብዛኛው የተጋሩ ኣክቲቭስቶች ጸረ ወያኔ ኣቋም ኣለን የሚሉ ቢሆንም ሕወሓት ግን ዋና ተጠቃሚ ካደረገቻቸው የትግራይ ተወላጆች ግንባር ቀደመኞች ሲሆኑ በነጻ ትምህርት እድል በስራና በሃብት ማፍራት ረገድ ሩቡን የሕወሓት ድርሻ የተሰጣቸው እነዚሁ ተቃዋሚ ነን ባይ ተጋሩዎች ሲሆኑ ኣሁን እያላዘኑብን ያሉ እነዚሁ ጸረ ሕወሓት ነን ባዮች የትኩሳት መለኪያ የሕወሓት መሳሪያዎች ናቸው።እያንዳንዳቸው በስማ በሃገር ውስጥና በውጪ ያገኙትን ጥቅም የሚጠቁሙ ጥቆማዎች በጃችን ይዘናል።ኣስመሳይ ተቃዋሚ መሰል ኣደናጋሪ መሆናቸው ግን እኛ ሳንናገር ራሳቸው እያፍረጠረጡት መሆኑ እሙን ነው በቅርቡ ደሞ ያልገመቷቻቸው ተጋሩዎች ወያኔን ደግፈው ሲፈናጠጡ ትመለከታላቹ።
ከኣስር ኣመት በኋላ ለመገንጠል እስከዚያም ኢትዮጵያን በዝብዞ ሕዝብ ኣበጣብጦ ለመውጣት ያለመው ሕወሓት ኣላማውን የሚያኮላሽ ጉድ በመወለዱ ያልደነገጠ ተጋሩ የለም ሁሉም ያላሰቡትና ያልገመቱት ጉዳይ በመከሰቱ ክ ውብለው ስለደረቁ የምነዙት ፕሮፓጋንዳ ሁሉክ የዘረኝነት ክራር ያጀበው ነው፤በኣጠቃላይ በውጪና በሃገር ውስጥ የሚገኙ ጸረ ሕወሓት ኣቋም ኣለን የሚሉ አክቲቭስቶች የምናየው በጥርጣሬ ሲሆን ከዚህ በፊትም የትኩሳት መለካያ ናጩ ብለን በግልጽ የነገርናቸው ኣሁን ራሳቸው እያረጋገጡልን መሆኑ ጠቅሞናል ከሕወሓት የኣደባባይ ኮካዎች ጎን ቀንደኛ የኢትዮጵያ ሕዝብ የለውጥ ትግል ጠላቶች የሆኑት ተጋሩ እባቦችን ካሰለጠናቸው ሕወሓት ጋር ኣብረው እንዲቀበሩ ትግላችን ይቀጥላል። 
Image may contain: text

No comments:

Post a Comment